>

የተመድ ጸ/ም/ቤት በተባረሩት የተመድ ሰራተኞች ጉዳይ ባደረገው አስገራሚ ስብሰባ አገራት ምን አሉ....?!?  (ቅጣዉ ንጉሴ)

የተመድ ጸ/ም/ቤት በተባረሩት የተመድ ሰራተኞች ጉዳይ ባደረገው አስገራሚ ስብሰባ አገራት ምን አሉ….?!?    
 ቅጣዉ ንጉሴ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለፉት ሁለት ወራት ለአራተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ ካደረገው ስብሰባ የዛሬውን የመስከረም 26ቱን አጠናቋል።
ኬንያ፣ ቱኒዚያ፣….
****
ኬንያና ቱኒዝያን ጨምሮ 3 የአፍሪካ አገራትን ያካተተው ቡድን የተመድ የሰብአዊ ሰራተኞች የኢትዮጵያን ነጻነትና ሉአላዊነት አክብረው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው፣ ጉዳዩም በኢትዮጵያ መንግስትና በተመድ መካከል በሚካሄድ ግልጽ ውይይት ሊፈታ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ቻይና
****
የቻይናው ተወካይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ላይ የተጣለው የአንድ ወገን ማዕቀብ በፍጥነት እንዲነሳ ጠይቀዋል። የተመድ የሰብዐዊ እርዳታ ክንፍ የሚያደርገውን ስራ አድንቀው ከጀርባ የሚፈጸሙ የፖለቲካ ሴራዎችን ግን መፈተሽ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። የጦር መሳሪያና የመገናኛ መሳሪያ የሚያስታጥቁ የእርዳታ ሰራተኞች መኖራቸው አሳዛኝ ነው ብለዋል።
ህንድ
****
የህንዱ አምባሳደርም ኢትዮጵያ በሰብዐዊ ቀውሱ አብዛኛውን ሀብት የምትመድበው መሆኗን አድንቀው፣ አዲስ የተመሰረተውን መንግስትና ካቢኔውን እንዲሁም ኢትዮጵያውያውን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። በኢትዮጵያ ያለውን ውስብስብ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል። የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት ማክበር ግዴታ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሩሲያ
****
የሩሲያ ፌዴሬሽኗ አምባሳደር ኢትዮጵያ ላይ በጸጥታው ም/ቤትም ሆነ በአንዳንድ አገሮች የሚደረገው ጫና መፍትሄ እንደማያመጣ አሳስበዋል። የተመድ ኢትዮጵያን ማገዝ እንደሚገባው ከመንግስት ጋርም ተባብሮ መስራት እንዳለበት ከዚያ ውጭ ያለው ግጭት ማስፋት እንደሆነ አንዳንድ አገሮችንና አለም አቀፉን ተቋም ተችተዋል።
አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ አየርላንድ…
አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ አየርላንድ፣ ሜክሲኮ፣ ፈረንሳይና ሊቶኒያ የተጨበጠ ነገር ሳይዙ የተለመደ በእልህና ጠላትነት የተሞላ ስሞታ አቅርበዋል።
አምባሳደር ታዬ አዝቀስላሴ
****
በተመድ የኢትዮጵያው አምባሳደር ታዬ ህዝቀስላሴ የራሱን የተመድን ህግ በመጥቀስ ኢትዮጵያ የፈለገችውን አካልና ግለሰብ የመቀበልና ከአገር የማበረር መብቷን ከ7ቱ የተባረሩ የድርጅቲ ሰራተኞች የተደበቀ ዓላማ ጋር በተብራራ ቋንቋ አብራርተዋል። የኢትዮጵያ መንግስትም ይሄንኑ ለድርጅቱ በተደጋጋሚ ሁኔታዎች እንዲስተካከሉ በሪፖርት ጭምር መግለጹን ለጸ/ም/ቤት አብራርተዋል።
የአንቶኒዮ ጉተሬዝ አስገራሚ ንግግር
****
በአምባሳደሩ ማብራሪያ የተደናገጡትና የተደናበሩት ዋና ጸሐፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ አንድ ሀቅ ይፋ አድርገዋል። አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ጫና እያሳደሩባቸው እንደሆነ። ለኢትዮጵያ መንግስትና ለጠ/ሚኒስትሩ ታደላለህ እያሉኝ ኢትዮጵያን ለማገዝ ሞክሬያለሁ ባይ ናቸው።
ማጠቃለያ
****
በአጠቃላይ አሜሪካና ምዕራባውያን አጋሮቿ ድርጅቱን እንደመሳሪያ በመጠቀም ኢትዮጵያን ለማድከም የጠነሰሱት ሴራ ሰፊ እንደሆነ ከመቼውም ጊዜ በላይ የተጋለጠበትና አምባሳደር ታዬ የኢትዮጵያን እውነት ያሳዩበትና የነአሜሪካን ተንኮል ያጋለጡበት ነበር። የምስራቅ አገሮችና  አፍሪካውያን ወዳጆቻችን ከኢትዮጵያ ጋር መቆማቸውን የበለጠ ያሳዩበትና ድርጅቱ በመሰንጠቅ አደጋ ውስጥ እንደሆነ ፍንጭ የሰጠ ስብሰባ ነበር።
Filed in: Amharic