ወንድወሰን ተክሉ
አንተ እና ባልደረቦችህ ይቅርታ ተጠይቃችሁ የምትፈቱ እንጂ አንተና ባልደረቦችህ ይቅርታ ጠይቃችሁ የምትፈቱ አይደላችሁም!!!!!
ታሪክ እራሱን ይደግማል እንደተባለው ጮርቃው የአባቱን ህወሃትን ስልትና ዘዴን በመድገም ጀግኖቻችንን እነ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ጃዋርና ሌሎችንም በምህረታዊ የይቅርታ ሂደት በመፍታት በቀጣይ ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለማገድ ማቀዱንና መዘጋጀቱን ለአቢይ ጽ/ቤት ቅርብ ከሆነ ሰው ሰምቻለሁ።
ታላቁ እስክንድር ነጋና ባልደረቦቹ አንዳችም ይቅርታ ለመጠየቅ የሚያበቃ ጥፋትና ክስ የሌለባቸው የፋሺስቱ አቢይ የፈጠራ ክስ ስለባ የሆኑ የህሊና እስረኞች ይቅርታ ሊጠየቁ ይገባል እንጂ ይቅርታ ለምነው እንዲፈቱ ማሰብ ፋሺስታዊ ድንቁርና ነው።