>
5:13 pm - Monday April 20, 6899

ለወ*ያ*ኔ መሰንበት ድክመቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ነው!!! (ሙሉነህ ዮሐንስ)

ለወ*ያ*ኔ መሰንበት ድክመቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ነው!!!

ሙሉነህ ዮሐንስ

*…. ከጦር መኮንኖች ትእዛዝ እየተጠባበቅን ነው የተባለውስ?
 
ለምእራቡ ሃያላን እራሱን ይበልጥ እያጋለጠ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት ነው። እንዴት ቢባል የዚህ ሁሉ መጠቅለያ መፍትሄው ወያኔ የሰነዘረውን ወረራ መጠነ ሰፊ እና ሁለ ገብ ጥ*ቃ*ት በመሰንዘር ሕዝባችን እና ሃገራችን እፎይ እንዲል ማድረግ ሲገባ፤ >>>
ወያኔ የመደራጃ እና ተጨማሪ ግፍ በሕዝባችን ላይ እንዲያደርስ ግዜ ተሰጥቶታል።
በጦር መኮንኖች በተደጋጋሚ  ትእዛዝ እየተጠባበቅን ነው የተባለው ጉዳይ አሁንም በሚዲያ እየሰማነው ነው። በእርግጥ የአየር ኃይሉ የተሻለ ጥ*ቃ*ት እየሰነዘረ መሆኑ በአወንታ የሚታይ ቢሆንም፤ በወረራ በተያዞ ቦታዎች ላይ ጠላት ተጨማሪ ሃይል እያስገባ፣ ምሽግ እየቆፈረ መዘጋጀቱ በቸልታ የሚታይ አይደለም። በወረራ ስቃይ ውስጥ ያለው ብቻ ሳይሆን አዋሳኝ አካባቢ ያለው ሕዝብ ከፍተኛ ስጋት ላይ በድጋሜ ወድቋል። እነሱ ለማ*ጥ*ፋ*ት*ም ለመ*ጥ*ፋ*ት*ም ቆርጠዋል። ብቸኛው መፍትሄ የማያዳግም እ*ር*ም*ጃ ብቻ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን የጥፋት ቡድን በአጭር ግዜ ከ*ደ*መ*ሰ*ሰ የምእራባውያን መራወጥ ሲሆን ያቆማል ቢያንስ ጋብ ይላል። አሁን የሚሯሯጡት ተላላኪዎቻቸውን ለማትረፍ ነው። እነሱ ድ*ባ*ቅ ከ*ተ*መ*ቱ ይቆርጥላቸዋል። ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግሥት ቢሮ ለቢሮ የሚሽከረከረውን ነገር አቁሞ ቀዳሚ እና ዋናው ተግባሩ የሕዝቡን ደህንነት ማረጋገጥ፣ የሃገር አንድነትን ማስጠበቅ፣ ብሎም ሕግን አስከብሮ ወደ ሃገር ማረጋጋት መሄድ አለበት። ዝምታው ዳተኝነቱ በዝቷል!!!
ሁለገብ እና የማያዳግም እርምጃ አሁን!!!
Filed in: Amharic