>

ይድረስ ለጠቅላዩ (ዘምሳሌ)

ይድረስ ለጠቅላዩ


ዘምሳሌ

አረረም መረረም ወንበር ጨብጠሀል
ደግም ሆነ ክፉ ህዝብ ያለቅስብሀል
ለሚያልቀው ህዝብ ሁሉ
ተጠያቂው ሰው ነህ ሰዎችም ይላሉ

ስትወጣ ስትገባ ሀላፊነት ወስደህ
የመሪነት ድርሻ ስልጣን ተመርኩዘህ
ለህዝብ ራስ ሆነህ የፊታቸው ግንባር
በጥጋብ በእርዛት ልትሆናቸው ቀንበር

መግለጫ ስትሰጥ ሀላፊነት ወስደህ
በሄድክበት ሁሉ  ህዝብ አንተን እያየህ
ዘወትር ይወቅሱሀል በሁሉ ቦታዎች
ምርቃት ወይ መርገም እየሰጡህ ሰዎች

ጊዜህ እስኪያበቃ የስልጣን ዘመንህ
የተመረጥክበት የማልከው ኪዳንህ
እድሜው  ሳይገደብ የሀገር ሰው ሁሉ
ሚሊየን አይኖቹም  ወዳንተ ያያሉ

ባለንበት ዘመን በጎሳ ከታጠርክ
ፍርድንም ካዛባህ በስልጣን ከሰከርክ
ቀን ይመጣብሀል  ህዝብ ይፋረድሀል
እንደፊተኞቹ አውጥተው ይጥሉሀል
ላስታውስህ ሳዳምን
ላስታውስህ ጋዳፊን

ባንተ ላይ ሚደርሰው ከነርሱ ይብሳል
በግፍ መፍረድ አቁም ግፉ ይቀልልሀል!!!

Filed in: Amharic