>

ወለጋ ላይ ያለውን ግጭት ለማስቆም መፍትሄ የምለውን ልጠቁም...!!! (ታድዮስ ታንቱ)

ወለጋ ላይ ያለውን ግጭት ለማስቆም መፍትሄ የምለውን ልጠቁም…!!!

ታድዮስ ታንቱ

በመጀመሪያ የኦሮሚያ መንግስት የአማራ ገበሬዎችን ትጥቅ የማስፈታቱን ጉዳይ ይተወው።
የአማራ ሊህቃን አኩርፈው ጫካ የገቡ ገበሬወችን አነጋግረው ወደ ቀያቸው ተመልሰው ከነ ጥትቃቸው እንዲኖሩ ያግባቡአቸው። በኦሮሚያ ሊህቃን ላይ ገበሬዎች እምነት አጥተዋል።
መንግስት ከኦነግ ሀይሎች እነዚህን ሰዎች በሰላም ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ የህግ ከለላ ይስጣቸው።
ከኦነግ ጋር ያበሩ የአካባበመው ባለስልጣናትን ተጠያቂ በማድረግ እና አውቀውም ይሁን ባለማወቅ ኦነግን የተቀላቀሉ የኦሮሚያ ወጣቶች ወደ ሰላም ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ማግባባት ቢደረግ።
አሻፈረኝ ባሉ የኦነግ አባላት ላይ መንግስት ቆራጥ እርምጃ ቢወስድ ወለጋ ወደ ሰላሟ ትመለሳለች።
ይህ መሆን የሚችለው በፌደራሉም ይሁን በክልሉ የተሰገሰጉ የኦነግ ባለስለሰጣናት ተለቅመው ሲወጡ ነው።
አሁን ያለው ያልተገባ አካሄድ የበለጠ ነገሮችን ስለሚያወሳስብ ቢቆም ጥሩ ነው። አማራውን የወከላችሁ ባለስልጣናት በወለጋ የአማራ ገበሬዎች ላይ የተከፈተ ጦርነት አግባብ እንዳልሆነ ልትመክሩበት ይገባል።
ፈጣሪ አገራችንን ሰላም ያድርግልን!
Filed in: Amharic