>
5:13 pm - Wednesday April 19, 1922

ነገሮቹ ቀስ በቀስ ፣ አንድባንድ ወደ ቀድሞ ሁኔታ እየተመለሱ ነው....!!! (ዳንኤል ሽበሽ)

ነገሮቹ ቀስ በቀስ ፣ አንድባንድ ወደ ቀድሞ ሁኔታ እየተመለሱ ነው….!!!

ዳንኤል ሽበሽ

*… ለቃላችሁን ኑሩ፣ ማሀላችሁን አክብሩ! ሕግ ይከበር! ሕግ አስከብሩ! ለግፉአን ርኀራኄን አሳዩ !!!
 
በሕግ ጥላ ሥር ያለ ዜጋ ሲደብደደብ ማየትና መስማት ከትላንት የቀጠለ ምዕራፍ ነው ። የመጣንበት ሰቅጣጭ መንገድ ነው! ፈጽሞ አንታገስም!
ነገሮቹ ቀስ በቀስ ፣ አንድባንድ ወደ ቀድሞ ሁኔታ እየተመለሱ መሆኑ እየታየ ነው ። ተጋግዘን ወደ ፊት ማስቀጠል የሁሉም ዜጋ ግደታ ነው ። ለመተጋገዝም እጆቻችንን  መዘርጋት ፣ በሮችን መቆርቆር ይኖርብናል ።
በመቀጠልም ጩሄቴ ፦
» ይድረስ ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣
» ይድረስ ለክቡር ጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ፣
» ይድረስ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣
» ይድረስ ለጠ/ፍ/ቤት ፕ/ት ለወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፤
ለቃላችሁን ኑሩ፣ ማሀላችሁን አክብሩ! ሕግ ይከበር! ሕግ አስከብሩ! ለግፉአን ርኀራኄን አሳዩ !!!
በአቶ #እስክንድር_ነጋ ላይ የተፈጸመው ድብደባ እንዲያው በዕለት ግጭት የተፈጸመ ነው ለማለት ይቸግረኛል ። በማረሚያ ቤቱ እስክንድር ሲደበድብ፣ ፖሊስ ደግሞ እሱ የሚዳኝበትን ችሎት ለመከታተል የሄዱ ዜጎችን በአፈሳ መልክ ሰብስቦ ማሰሩን አያይዘን ስናይ ነገሩ ወዴት፣ወዴት? እያመራ ነው እንድንል ያደርገናል ። አፈና እያቆጠቆጠ መሆኑን ፍንጭ የሚሰጥ ነው ።
ስለ አፈና ፦
“ሰው በአፉ እንዳይተነፍስ ከተከለከለ እጁን ለድንጋይ ይጠቀማል” ያለው ማን ነበር?
ከጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ድስኩሮች የሰማሁት መሰለኝ ። የትም ይሁን የት አፈና ይውደም!
በመጨረሻም «ሀገራችንን በህብረት፣ በተባበረ ክንድ እንገንባ እንጂ ወደ ቀድሞ ትግል ዘመን አትመልሱን!»
ቸር ያሰማን!
Filed in: Amharic