ሰለሞን አላምኔ
አብይ አህመድን ስርአትስ በአይነ ቁራኛ ነው ማየት…!!!
ፖሊስ ምን አለ!፦ ” በከተማው ውስጥ መንገድ በመዝጋት ሁከት አመፅ እና ብጥብጥ ለመፈጠር ሲንቀሳቀሱ ይዣቸዋለሁ። ” አለ በፍርድ ቤቱ ውስጥ! #ተከተለኝ
በእነዚህ ፎቶ ላይ ተመስርተህ ህዝቤ ፍርድህን ስጠኝ!! አንድም የያዙት ዱላ መሳሪያ ወይም ለሽብር ወንጀል ለመፈፀም የሚያበቃ ነገር አልያዙም። በፎቶው ላይ ሁሉም የምታያቸው ሰዎች ከአመት በላይ በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ህገ መንግስታዊ ጉዳዬችና ፀረ ሽብር ወልጀል ችሎት ፍትሕ አዳራሽ ቀርተው የማያወቁ ሰላማዊ ዜጎች ናቸው። በምርጫ ወቅት በመላ አዲስ አበባ ሰፈር ቀበሌ ድረስ በሚገባ የእስክንድር ነጋ ፎቶ የታተመ ቲሸርት ለብሰው ለምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩም ጭምር ናቸው።
በ2013 ዓ.ም አመቱን ሙሉ የእነ እስክንድር ነጋን መዝገብ በመሐል ዳኝነት ሲመሩ የነበሩት ዳኛ ሁላ ሳይቀር ፤ አቃቢ ህግ እኛን ለመክሰስ ከአንዴም ሁለት ሶስቴ የክስ ዶሴ ሲያዘጋጅ ዳኛው ግን እነዚህ የችሎት ታዳሚዎች አመቱን ሙሉ እዚህ ችሎት ሲመጡ አንድም የተለየ ነገር አላየሁም ያቀረብከው አቤቱቷ መሰረት የለውም #ፍፁም_ሰላማዊ ሰዎች ናቸው በማለት ለእኛ በቂ ምስክር መስጠቱ ይታወሳል። ሰላማዊ ሰዎች ነን።
ርግጥ ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ በግልፅ ቋንቋ ከእኛ ጋራ ያላቸውን ልዩነት የሚፈቱበትን መንግድ አስቀምጠዋል። እኛም በሰዓቱ በመሪያችን በኩል በቂ ምላሽ ሰጠናል። እንዲህ የሚል “ሀይል የእግዚአብሔር ነው !! ” የሀሳብ ጦርነት ከሆነ እኛ የትግል ቦታ እንመርጥ በሚል። ባለ አደራው ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬዋ ድርስ በባልደራስ ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩ የተናገሩትን “ግልፅ ጦርነት” እየፈፀሙ እዚህ ደርሰዋል እኛም በሰላማዊ ትግል ከመሪያችን ጀምሮ እስካሁን እየተፋለምን እንገኛለን። እንቀጥላለንም። በሰላማዊ ትግል እስከ ቀራኒዬ እንሄዳለን።
በመጨረሻም ህዝብ እና የህዝብ ድምፅ በማፈን ፣ የህዝብን መሪ በማሰር በማስደብደብ ፣ 4 ጊዜ የግድያ ሙከራ በማድረግ ፣ የባልደራስ አባላቶችን በመደብድብ በማሰር እና ከስራ በማባረር ፣ የአዲስ አበባን ወጣት በማሰዳደ የሚቆም የፖለቲላ ትግል የለም። በሰላማዊ ትግል ብቻ ህዝብ ያሸንፋል። የማይቀረው ሀቅ ይሄ ነው። እናሸንፋለን
ድል ለዲሞክራሲ
ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል
⇑ በፎቶው ላይ የሚታዩት ትላንት ከእነ እስክንድር ነጋ ችሎት መልስ ታፍሰው የታሰሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ናቸው።