የአማራ ህዝብ ላለፉት ሰማንያ አመታት ጠላቶቹ እንዲጠፋ ፈርደውበት በሚሊዮኖች እየተሰደደ፣ በሚሊዮኖች ከሃብት ንብረቱ እየተፈናቀለ፣ በሚሊዮኖች እያለቀ ይገኛል። በተለይም በዚህ በኛ ዘመን አማራ በመሬት ብቻ ሳይሆን በእናቱ ማህጸን እንኳን ረፍት አጥቶ መውጫ መግቢያው ተዘግቶበት፣ በመሬትም በማህጸንም ሞት እንዲጋት ተፈርዶበት ከሰማይ በታች ያለ መከራን ሁሉ እየተቀበለ ይገኛል። ሌላው ቀርቶ አማራ ከልጆቹ አሳዳጊ ላሞቹና በሬዎቹ ጋር ስጋው እኩል እየተበላ ነው።
በተለይ በዚህ ጊዜ ለ 27 አመታት መንግስት ሆኖ አማራን ጠልቶ ያስጠላው፣ ገድሎ ለገዳይ የሰጠው፣ አርዶ ያሳረደው ህወሃት፣ የኦሮሞ ህዝብ ነጻነት ግንባርና የጉምዝ ሽፍቶችን የመሰሉ የመንፈስ አጋሮቹ በቅርብ እና እሩቅ ብሄራዊ ጠላቶቻችን እየታገዙ የተቀናጀ ይፋዊ ጦርነት ከፍተውበት ሚሊዮኖች ከበቀሉበት ቀዬ እየተፈናቀሉ ነው፤ ሚሊዮኖች በጥይት አረር፣ በረሃብና ቸነፈር እያለቁ ነው። ይህን ግፍ እና ፍዳ ለማስቆምም የአማራ ልጆች በተለያዩ አደረጃጀቶች ታቅፈው በግንባር እየተዋደቁ ነው።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የአማራ ፋኖን ወቅቱን በሚመጥን ስፋትና ጥልቀት፣ ዓላማና ስምሪት እንደገና አደራጅቶ የህልውና ዘመቻውን መቀላቀልና ዘለአለማዊ ጠላቶቻችን ለዘለአለሙ መንቀል እጅግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የአማራ ህዝባዊ ሃይል (አማራ ፋኖ) ነሐሴ 06 ቀን 2013 አም በፍኖተሰላም ከተማ መመስረቱ ይታወቃል።
ላለፉት ሶስት ወራትም በእሳት ባህር ውስጥ እየዋኘ ህዝቡን የማንቃትና የማደራጀት ስራ ሲሰራ፣ በብዙ ሽህዎች የሚቆጠሩ ፋኖዎችን ሲያሰለጥንና ሲያዘጋጅ፣ መዋቅሩን በሁሉም አካባቢዎች ሲዘረጋ ቆይቷል።
በዚህ ወቅት ከጠላት ጋር ለመተናነቅ የሚያስችለውን ሙሉ ቁመና ፈጥሯል ተብሎም ይታመናል። በመሆኑም በሙሉ ሃይልና ወኔ ወደ ግንባር ለመንቀሳቀስ ከየአካባቢው አስተባባሪዎችና አመራሮች ጋር ቁጭ ብሎ መክሮ የዘመቻ ስትራቴጅና ታክቲክ መንደፍ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በዛሬው እለት ጥቅምት 13 ቀን 2014 ዓ.ም በደጀን ከተማ ተሰብስቦ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ጨምሮ ታሪካዊ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
1/ የሕዝባዊ ሃይሉን ህገደንብ እና የትግል ስትራቴጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
2/ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሁሉም ግንባር በይፋ ለመዝመት በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
3/ አማራን ከፈጽሞ ጥፋት ለማዳን መላው የአማራን ህዝብ በተለይ ወጣቱን በማስተባበር በሁሉም ግንባሮች ከልዩ ሃይሉና መከላከያው ጎን ተሰልፎ እስከ መጨረሻዋ የደም ጠብታ ለመፋለም በከፍተኛ ወኔ ወስኖ ወደ ተግባር ገብቷል።
በመሆኑም ለመላው የአማራ ህዝብ እና የሚመለከታቸው ሁሉ የሚከተለውን ጥሪ ያደርጋል።
1. ለክልሉ መንግስት
የአማራ ህዝብ ሽህ ጊዜ ሰልጥኖ ሽህ ጊዜ ቢታጠቅ ሽህ ጊዜ ልክ ነው።ምክንያቱም ተቆጥረው የማያልቁ ጠላቶች እንዳሉት ፍጥረት ሁሉ ያውቃሉና።ስለዚህ ፋኖዎችን በየቦታው አሰልጥኖ ለማዝመት የጀመርነውን ጉዞ ላንድ ደቂቃም የሚያስተጓጉል ሃይል አንፈልግምና በዚህ ረገድ ታች ድረስ ያለው የመንግስትና የፖለቲካ መዋቅር የጥረታችን ተባባሪ እንጅ እንቅፋት እንዳይሆን ግልጽ መመሪያ እንዲሰጥ እንጠይቃለን። ትምህርት ቤቶችን እና መንግስታዊ ተቋማትን በመዝጋት እድሜውና ጤናው የሚፈቅድ አማራ በሙሉ ወደ ጦር ግንባር መክተት ይችል ዘንድ መንግስታዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ እያሳሰብን በየመጋዝኑ የተቆለፈባቸው የጦር መሳሪያዎች በሙሉ ወጥተው ፋኖውና ባጠቃላይ ህዝቡ እንዲታጠቃቸው በታላቁ ህዝባችን ስም ታሪካዊ ጥያቂያችን እናቀርባለን።
2. ለወጣቱ
ተነስ!ሰልጥን፥ ታጠቅ! ዝመት። ለእናትህ፣ እህትህና ለሴት ልጅህ ክብር ስትል ውጣና መክት። ለማንነትህና ለነገህ ማማር ስትል ውጣና ጠላት ተከላከል። ወስልቶ የሚቀር አንድም እንኳን እድሜውና ጤናው የሚፈቅድ ወጣት ቢኖር በትውልዱ የተጠላ በታሪክ ፊት የተናቀ ይሆናል።
3. ለቀድሞ የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት አባላት-
ጀግኖች የወርቃማው ትውልድ አባላት ሆይ የአማራ ህዝብ ወታደራዊ ልምዳችሁንና እውቀታችሁን አጥብቆ የሚፈልግበት ጊዜ አሁን ነውና ኑ ተቀላቀሉን እያልን ታናናሾቻችሁ ጥሪ እናቀርባለን።
4. ለአማራ ባለሐብቶች-
ኪስ የማይለይ ጠላት ወሮ ሰውንም ንብረቱንም፣፥ እንጨቱንም እንስሳውንም እያወደመ ይገኛል።ለህዝባችሁም፣ ለማንነታችሁም፣ ለክብራችሁም ስትሉ ትግሉን በማገዝ በኩል ያለባችሁን ዳተኝነት በፍጥነት እንድታርሙትና የእናንተም የንብረቶቻችሁም ዋስትና ዛሬ እየተገነባ ያለው ፋኖ መሆኑን አውቃችሁ ትግሉን በገንዘብም በሞራልም እንድታግዙ አደራ እንላለን።
5. ለመላው የአማራ ህዝብ
በአጠቃላይ ጠላቶቻችን እንደ ህዝብ መጠው እንደ ህዝብ ሊያጠፉን ነው እሳት የለኮሱት።ስለዚህ እንደ ህዝብ እንነሳ!ከዚህ በኋላ ቆሞ ለመሞት ጊዜ የለንምና ሆ ብለን ወጥተን እንደ ህዝብ እናሸንፋቸው! እናሸንፋቸዋለንም!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!
ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ!!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ጥቅምት 13 ቀን 2014 ዓ.ም
ደጀን