>
5:26 pm - Sunday September 15, 3044

የአሜሪካ ባለስልጣናትና የህወሃት ጋብቻ ፍፃሜበ H.Res.445 አዋጅ (እስሌማን ዓባይ)

የአሜሪካ ባለስልጣናትና የህወሃት ጋብቻ ፍፃሜ

             በ H.Res.445 አዋጅ
እስሌማን ዓባይ 

በአሜሪካ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ጉዳይ ውሳኔ አሳልፏል
የውሳኔው መግለጫ አሜሪካ የህወሃት ጉዳይ እንዳበቃለት መገንዘቧን የሚያንፀባርቅ ነው። “ጦርነቱ ቶሎ ካላበቃ የአጎዋ ገበያ ዕድልን ያስተጓጉላል እና መፍትሄው ድርድር ነው ከሚሉት በስተቀር በዲጂታል ዘመቻችን ደጋግመን ያስተጋባናቸውን መልዕክቶች የተቀበሉ ሆነው ነው ያገኘኋቸው።
በትላንትና ዕለት የፀደቀው H. Res 445፣ ኢትዮጵያ ለምትገኝበት ጦርነት መነሻው ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ መሆኑን  አምኗል።
ህወሓት ዕድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህጻናትን ለጦርነት መጠቀምን በአስቸኳይ እንድያቆም አሳስቧል።
ህወሓት በሀይል ወርሮ ከያዛቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ያለቅድመ-ሁኔታ ለቆ እንዲወጣም በአፅንኦት ጥሪ አቅርቧል።
አዋጁ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ለትግራይ የሚደርሰው ሰብዓዊ ርዳታ በተቀላጠፈ መልኩ እንዲደርስ ይጠይቃል። ህወሓት የሰብዓዊ ርዳታ ተሽከርካሪም ሆነ ርዳታውን ከመዝረፍ እንዲታቀብም ይጠይቃል።
ህወሓት ከኦነግ ሸኔ የፈጠረውን ጥምረት ያለቅድመ-ሁኔታ እንድያፈርስ በመግለጫው ተቀምጧል።
አሜሪካ በዚህ ደረጃ ላንፀባረቀችው የአቋም ለውጥ በካሊፎርኒያ ግዛት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጫና ከፍተኛ አበርክቶ እንደነበረው ከመግለጫው ይዘት መታዘብ ችያለሁ። ጦርነቱ በፖለቲካ በብሄርና በታሪክ ጓዞች ይበልጥ እንዲወሳሰብ ሆኗል የሚለው መግለጫው እዚህ ላይ የተጠቀሱ ጉዳዩች ከተለያዩ አካላት ውይይቴ የተገነዘብኩት ነው ያሉት ካረን ቤዝ ናቸው። ይኸውም አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ የተጫወተውን ጉልህ ሚና እንድናስታውስ ያደርገናል።
Filed in: Amharic