>

«የጅብ ምርጫ ውስጥ ገብተን በጦርነት ውስጥ እየዳከርን ነው.....!!!» (መአዛ መሀመድ)

«የጅብ ምርጫ ውስጥ ገብተን በጦርነት ውስጥ እየዳከርን ነው…..!!!»

መአዛ መሀመድ

ጠሚ አብይ  አህመድ ምርጫ ባደረገ ማግስት የጦርነቱን ሜዳ ወደ አማራ ክልል ቀየረው። መንግስት  መሰረትኩ ባለ ማግስት ” ታጠቅ ዝመት” የሚለውን ማቆም እንዳለብን ነገረን። እስካሁን ድረስ የጦርነቱ ዓላማ ምን እንደሆነ እንኳ ግልፅ አድርጎ ተናግሮ አያውቅም። የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ በማያምንበት ጦርነት የምታሸንፉት እንዴት አድርጋችሁ  ነው?
ቤት ዘግቶ መምከር እና መፍትሔ ማበጀት፥ የጋራ አቋም መያዝ ለዚህም በተግባር ዋጋ መክፈል( ፎቶ እየለጠፉ መሸቀጥን ነውር አድርጎ)የአባት ነው። ሌሎች ባቀዱት እና በሚወስኑት ጦርነት ገብቶ መንከላወስ ግን የህዝብን ሲቃይ ያራዝም እንደሆን እንጅ አሸናፊ አያደርግም።
የግርጌ ማስታወሻ: “የጅብ ምርጫ” ውስጥ ገብተን በጦርነት እየዳከርን ነው።
ይህንን ጦርነት ከጅምሩ ብቃወመውም ከእኛ ቁጥጥር ውጭ ሆኖ ከተገባበት በኋላ ግን ከማይከድራ እስከ ሁመራ ከወገል ጤና እስከ ዞብል ከንፋስ መውጫ እስከ ጭና ከወልቃይት እስከ ደሴ ዞሬ የንፁሃንን መከራ ተጋርቻለሁ አቅሜ  በሆነውም ሁሉ አንብቻለሁ የገቡበትን የህልውና ፈተናም አይቼ ተብከንክኛለሁ። ይህ ህዝብ ወደ መደበኛ ህይወቱ የሚመለስበት ቀን ይናፍቀኛል። መንገዳችን ደግሞ የሚያደርሰን ስላልመሰለኝ  ያቀረብኩት ሃሳብ ሊያንጫጫችሁ አይገባም።
Filed in: Amharic