>

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከወሎ የተፈናቀሉትን   ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ እግዶ እየመለሰ ነው!  (ጎበዜ ሲሳይ) 

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከወሎ የተፈናቀሉትን   ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ እግዶ እየመለሰ ነው!

 ጎበዜ ሲሳይ 

*… የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከወሎ ና አቅራቢያዋ ካሉ ከተሞች የተፈናቀሉትን ዜጎ ወደ
አዲስ አበባ እንዳይገቡ እግዶ እየመለሰ ነው!
ይህ ትልቅ ጭካኔ  ነው! 
ትልቅ ዘረኝነትና ተረኝነት ነው! 
ትልቅ ኢሰብአዊነት ነው!
 
ከሰሜን እና ከደቡብ ወሎ  ደሴ እና ኮምቦልቻ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ መንገደኞች ጣፎ ሲደርሱ በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና በመንገድ ትራፊክ ፖሊሶች  መንገደኖቹ  ወደ መጡበት እንዲመለሱ መደረጉን መንገደኞቹ ለየኛ ቴሌቪዥን ተነግሩ።
መንገደኞችን የጫኑ አውቶብሶች እና ሚኒባሶች  ከምሽቱ  አስራ ሁለት ሰዐት ጀምሮ  ወደ አዲስ  አበባ ለመግባት ጣፎ ሲደርሱ  በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ  እና በመንገድ ትራፊክ ፖሊሶች እንዲያልያልፉ ተደርገው መንገድ ላይ ማደራቸውንም መንገደኞቹ ለየኛ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 13 /02/ 2014 ዓ/ም  መንገደኞቹን የጫኑ ተሽከርካሪዎች በፖሊስ ታጅበው እስከ ሰንዳፋ ከተማ ድረስ ተሸኝተዋል።
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የመንገድ ትራፊክ ፖሊሶች ሲጠየቁ  ተፈናቃዮች ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዳይገቡ የሚል ትዕዛዝ ደርሶን ነው የሚል  ምላሽ እንደሰጧቸው ተናግረዋል።
የኛ ቴሌቪዥንም ይህንኑ ለማጣራት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን  ደውለን ነበር የማውቀው ነገር የለኝም ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
ከመንገደኞቹ አብዛሀኛዎቹ ሕጻናት እና እናቶች መሆናቸውን ለየኛ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
ታዲያ እነዚህ ተረኞች ከህወሃት የባሱ የከረፉ አይደሉምን?
Filed in: Amharic