>

የእስክንድር ነጋ ጠበቆች መስቀለኛ ጥያቄ…         ለወ/ሮ መንበረ በቀለ ሲሻው   (በዘመድኩን በቀለ)

የእስክንድር ነጋ ጠበቆች መስቀለኛ ጥያቄ…
        ለወ/ሮ መንበረ በቀለ ሲሻው  
በዘመድኩን በቀለ

… እንደምን አደራችሁ ጎዶኞቼ? አሁን ደግሞ  ከሁለተኛዋ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ከወ/ሮ መንበረ በቀለ ሲሻው ጋር የእስክንድር ጠበቆች ያቀረቡላትን መስቀለኛ ጥያቄዎች አቀርብላችኋለሁ። ጠበቆች መጠየቃቸውን ቀጥለዋል። (አዴ መንቢኮም) አጭር መልስ እንዲሰጡ ሲጠየቁ ያልተፈለገ ማብራሪያ በመስጠት ሲያስቸግሩ ነው የዋሉት። 
 
ወደ ጥያቄና መልሱ… 
• ጠበቃ፦  ማንነትዎን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘዋል?
… ምስክር፦ አዎ
• ጠበቃ፦ ለፍርድ ቤቱ ያሳዩልኝ። የአያት ስም ማን ይላል?
… ምስክር፦ ሲሻው
• ጠበቃ፦ ዕድሜዎን ሲናገሩ 37 ዓመቴ ነው ብለው ነበር። መቼ ነው የተወለዱት?
… ምስክር፦ አላውቀውም።
• ጠበቃ፦ የማስታወስ ችግር አለብዎት?
… ምስክር፦ የለብኝም።
• ጠበቃ፦ ከሌለብዎት አስበው ይንገሩኝ።
‼ ዐቃቤ ሕግ ፦ ተቃውሞ
• ጠበቃ፦ መታወቂያዎ ላይ 1974 ዓ.ም ተወለዱ ይላል። ስናሰላው 4ዐ ዓመት ሆኖዎታል። ትክክል ነው?
… ምስክር፦ አይ 37 ዓመትሽ ነው ተብያለሁ። መታወቂያውን አላየሁትም።
• ጠበቃ፦ የእርስዎ መታወቂያ አይደለም?
‼ ዐቃቤ ሕግ፦ ተቃውሞ (ጥያቄውን አስቀየሰው)
• ጠበቃ፦ የት ነው የሚሠሩት?
… ምስክር፦ ወረዳ 5 የቤቶች አስተዳድር ጽሕፈት ቤት ሓላፊ ነኝ።
• ጠበቃ፦ ከወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር ምን አገናኝዎት?
… ምስክር፦ አይ . . . እ እ እ እ
• ጠበቃ፦ መታወቂያ የሚፈልግ ሰው በአንድ ቀን ጨርሶ ይሄዳል?
… ምስክር፦ አላውቅም።
• ጠበቃ፦ አቶ ፈንታሁንን በዓይን ከማየትዎ በተጨማሪ ከመገናኘታችሁ በፊት ስለ እርሱ የሚያውቁት ነገር ነበር?
… ምስክር፦ የለም።
• ጠበቃ፦ እስክንድር ሊያስገድልዎት እንደሆነ በምን አወቁ?
… ምስክር፦ የፈንታሁን ባለቤት ነግራኝ።
• ጠበቃ፦ ስሟ ማን ይባላል?
…ምስክር፦ አላውቅም።
• ጠበቃ፦ በሥራ ይገናኙ ነበር?
… ምስክር፦ አንገናኝም።
• ጠበቃ፦ የፈንታሁን ባለቤት መሆናቸውን በምን አረጋገጡ?
…ምስክር፦ “የፈንታሁን ባለቤት ነኝ” ስላለችኝ።
• ጠበቃ፦ ከማን ጋር ነበር በዕለቱ ምሳ የበሉት?
…ምስክር፦ እእእእእ ዮርዳኖስ አለች። የፅዳት ሠራተኛዋም አለች።
•ጠበቃ፦ ፈንታሁን ከ2ዐ ደቂቃ በኋላ  መጣ ብለዋል። ከየት እንደመጣ ያውቃሉ?
… ምስክር፦ አላውቅም።
• ጠበቃ፦ ስንት ሰዓት ይሆናል?
… ምስክር፦ በግምት 8
• ጠበቃ፦ ስልክ ይዞ ነበር?
… ምስክር፦ አዎ እርሱም እኔም ይዘናል።
• ጠበቃ፦ አቶ እስክንድርን ከዚህ በፊት ያውቋቸዋል?
… ምስክር፦ አላውቀውም።
• ጠበቃ፦ ፖሊስ ጣቢያ ሄደው ያውቃሉ?
… ምስክር፦ አላውቅም።
• ጠበቃ፦ ታክሲ ውስጥ የፈንታሁንን ስልክ ቁጥር የተቀበሉት እርስዎ ነዎት። እርሱስ የእርስዎን ወስዷል?
… ምስክር፦ አልወሰደም።
• ጠበቃ፦ ከዚያ በኋላስ ማን ቀድሞ ደወለ?
… ምስክር፦ እርሱ
• ጠበቃ፦ ስልክ ቁጥርዎት እኮ የለውም። እንዴት ደወለ?
… ምስክር፦ እእእእእእእ ከባለቤቱ ጋር እንደዋወል ነበር።
• ጠበቃ፦ ስንት ጊዜ ተደዋውለዋል?
… ምስክር፦ አላውቅም። ስልክ ቁጥሩንም አላውቅም።
• ጠበቃ፦ አሁን ስልክ ይዘዋል?
… ምስክር፦ አዎ
• ጠበቃ፦ ቁጥሩን ሊነግሩን ይችላሉ?
… ምስክር፦ ዝምምምምምምም ( 09400747… ብዬ እኔ ዘመዴ ላስታውሳቸው ፈለግኩና ፈርቼ ዝም አልኩ። ኦኦ በኋላ ደግሞ ዐቃቤ ሕግ ከአገር አትወጣም ብሎ ጣጣ ቢያመጣብኝስ? ተደብቄ ዝምምም እኔም።)
‼ ዐቃቤ ሕግ፦ ተቃውሞ ይሄ ለደህንንታቸው ያሰጋናል።
(የደህንነት ጉዳይማ በምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 መሰረት ሲከራከሩበት ከርመው ዐቃቤ ሕግ ተሸንፏል። ዳግም መመለስ የለበትም)
‼ዳኛ፦ በወረቀት ጽፈሽ ቁጥሩን ከእነ ስልኩ አምጭ። እኛ እዚህ እንመዘግበዋለን። በዚያን ጊዜ ስትደዋወሉበት የነበረው ቁጥር መሆን አለበት)
• ጠበቃ፦ ከአቶ ፈንታሁን ባለቤት ጋር ከዚያ ቀን ውጭ ተገናኝታችሁ ታውቃላችሁ?
… ምስክር፦ አናውቅም።
(እዚህ ላይ የአዳራሹ መብራት ጠፋ። የመሀል
ዳኛው የእስከ አሁኑን በድምፅ የተቀዳ ክርክር ቴክኒሻኑ እንዲመዘግበው (save እንዲያደርገው) አዘዘ። በተጨማሪም ጀኔሬተር እስከሚበራ ችሎቱ ተቋርጦ ጠበቀ)
• ጠበቃ፦ ብሔርዎን ይነግሩናል።
… ምስክር፦ ኦሮሞ
‼ ዐቃቤ ሕግ፦ ተቃውሞ። ጥያቄወሰ ከእነ መልሱ ይሰረዝ።
• ጠበቃ፦ የክሱ ጭብጥ ብሔርን ከብሔር ማጋጨት የሚል ስለሆነ ብሔራቸው መጠየቁ ተገቢ ነው።
‼ ዳኛ፦ ጥያቄው ከእነ መልሱ ተሰርዟል።
• ጠበቃ፦ ከፈንታሁን ቤተሰብ ውስጥ የሚያውቁት አለ?
… ምስክር፦ የለም።
• ጠበቃ፦ ከፈንታሁን ጋር አብረው የሄዱባቸው ቦታዎች አሉ?
… ምስክር፦ ሁለት ጊዜ ሄደናል። አንድ ጊዜ ሲሸኘኝ፤ ሌላ ጊዜ ፖሊስ ኮሚሽን ስንሄድ።
• ጠበቃ፦ ሌላ ሰው አብሯችሁ ነበር?
… ምስክር፦ የለም።
• ጠበቃ፦ ከዚያስ መጨረሻው ምን ሆነ?
‼ ዐቃቤ ሕግ፦ ተቃውሞ።
• ጠበቃ፦ በእርስዎ ላይ ምን ጉዳት ደረሰ?
… ምስክር፦ ስጋት
• ጠበቃ፦ በስልክ ደውሎ የዛተብዎት ሰው አለ?
… ምስክር፦ አዎ
• ጠበቃ፦ ምን አለዎት?
… ምስክር፦ የዚያን ጊዜ የለም። አሁን ምስክርነት መስጠት ከጀመርኩ በኋላ ግን አዎ አለ።
• ጠበቃ፦ በወረዳው ብዙ ወጣቶችን ተጠቃሚ አድርጌያለሁ ብለዋል። ምን ያህል ናቸው?
… ምስክር፦ አላውቅም። የቤት ፈላጊ ሴቶችንና ወጣቶችን አደራጅተናል።
• ጠበቃ፦ አደራጅታችኋል?
… ምስክር፦ ማደራጀት ሳይሆን የቤት አጥ የሆኑትን ለይተናል።
(ምስክሯ ከተጠየቀችው ውጭ እያብራራች ስላስቸገረች ጠበቆች ትዕዛዝ እንዲሰጥ ጠየቁ። ዐቃቤ ሕግም ተቃወመ። ዳኞች ተቃውሞውን ውድቅ አደረጉት)
• ጠበቃ፦ ከተደራጁት ውስጥ የአቶ ፈንታሁን ስም አለበት?
… ምስክር፦ የለም።
• ጠበቃ፦ ለእነ ፋንታሁን ብድር ሰጥተዋል።
… ምስክር፦ አልሰጠሁም።
• ጠበቃ፦ ፖሊስ ጠባያ ከፈንታሁን ጋር ያመለከታችሁት መቼ ነው?
… ምስክር፦ ሀምሌ፤ ማለቴ ነሐሴ ነው።
• ጠበቃ፦ ቀኑስ?
… ምስክር፦ አላውቀውም።
• ጠበቃ፦ ዓመተ ምህረቱስ?
… ምስክር፦ 2012 ነው። ከዚህ ወጥተን ቀጥታ ሄድን።
• ዳኛ፦ ከዚህ ማለት ከየት ነው?
… ምስክር፦ ወረዳ ስድስት ከቢሮዬ
(ከዚህ በፊት ቢሮዋ ወረዳ 5  መሆኑን ተናግራ ነበር)
• ጠበቃ፦ ቃል ሰጡ?
… ምስክር፦ አዎ
• ጠበቃ፦ ፈርመዋል?
… ምስክር፦ አዎ።
• ጠበቃ፦ ያመለከታችሁበት ጉዳይ ምን ላይ እንደደረሰ ያውቃሉ?
… ምስክር፦ 2013 ዓ.ም. ዐቃቤ ሕግ ደውሎ ለምስክርነት ጠየቀኝ።
• ጠበቃ፦ ለፖሊስ የሰጡት ቃል ምን የሚል ነው?
… ምስክር፦ ለምስክርነት ነው።
• ጠበቃ፦ በአቶ ፈንታሁን የግድያ ሙከራ ላይስ ቃል ሰጥታችኋል?
‼ ዐቃቤ ሕግ፦ ተቃውሞ ከፈንታሁን ጋር ምን አገናኛቸው?
‼ ዳኛ፦ ተቃውሞውን ተቀብለናል።
• ጠበቃ፦ መስቀለኛ ጥያቄያችንን ጨርሰናል።
እኔ፦ የዐቃቤ ሕግ ድጋሜ ጥያቄና የዳኞች ማጣሪያ ጥያቄ ይቀጥላል። እሱንም ጥጌን ይዤ ሁላቸውንም እያየሁ ቀረጻዬን ቀጥያለሁ።
• …የመስቀለኛ ጥያቄው ቀጥሏል። አሁን ደግሞ 2ኛ ምስክር መንበረ በቀለ ሲሻውን የመጨረሻ የማጣሪያ ጥያቄ ጠያቂው ምስክሯን ያመጣው ራሱ ዐቃቤ ሕጉ ነው። ተከታተሉት። 
‼ዐቃቤ ሕግ፦ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎ አሁን  ከሚመሰክሩበት ጉዳይ ጋር ምን ግንኙነት አለው?
…ምስክር፦ በሥራ ፈጠራ፣ በቤት ፈላጊ፣ በሴቶች ወጣቶቾ እናደራጃለን።
‼ዐቃቤ ሕግ፦ የፓርቲ አባላትን ያደራጁ ነበር?
…ምስክር፦ አላደራጅም
‼ዐቃቤ ሕግ፦ የምታደራጇቸው  ሰዎች ከየትፓርቲ ነው የሚመጡት?
…ምስክር፦አዎ ከተለያየ። ከኢዜማ
•ጠበቃ፦ ተቃውሞ። መሪ ጥያቄ ነው።
‼ዳኛ፦ ተቃውሞው ትክክል ነው። ዐቃቤ ሕግ ያስተካኮሉ።
‼ዐቃቤ ሕግ፦ከየት ከየት ፓርቲ እንደሆነ ይጥቀሱልን
…ምስክር፦የባልደራስ አለ።
‼ዐቃቤ ሕግ፦ እናመሰግናለን
ከሁለቱ ቀናት ውጭ ፈንታሁን ጋር ተገናኝተው ያውቃሉ?
…ምስክር፦አዎ በስልክ
‼ዐቃቤ ሕግ፦ማንነው ቀድሞ የደለው?
…ምስክር፦ እኔ ነኝ። ( አይ መንቢዬ ከላይ እኮ ፈንታሁን ቀድሞ ደወለ ብላ ነበር)
‼ዐቃቤ ሕግ፦ ጥሩ ! ጥቃት እንዴት እንዳልደረሰብዎት ያውቃሉ?
…ምስክር፦ አላውቅም። ግን ፈንታሁን “እኔ እጠብቅሻለሁ ስትወጭና ስትገቢ በአሳቻ ሰዓት ይሁን” ብሎኛል። (ፋንታሁን የሚጠብቃት እሱ ምንድነው እንዴ? ሆኦ)
‼ዐቃቤ ሕግ፦ ፈንታሁን የምቀበለው መሳሪያ አለ ያለዎት ምንድን ነው?
…ምስክር፦ መሳሪያ ከሰዎች እቀበላለሁ አለ።
‼ዐቃቤ ሕግ፦ ማነው የሚሰጠው?
…ምስክር፦ አላውቅም።
‼ዐቃቤ ሕግ፦ ለእነ ማን ነው የሚሰጠውስ?
…ምስክር፦ እንግዲህ መሳሪያ እስከምቀበል ጠብቂ አለኝ።
‼ዐቃቤ ሕግ፦ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምን ተባላችሁ?
…ምስክር፦ ከመጋረጃ ጀርባ ትመሰክራላችሁ አሉን።
…ዐቃቤ ሕግ ጨረሰ። የዳኞች የማጣሪያ ጥያቄ ይቀጥላል።
ይሄ የ2ተኛዋ ምስክር የዳኞች የመጨረሻ የማጣሪያ ጥያቄ ነው። ከዚያ ወደ ዛሬ መስካሪዎች ውሎ እንሄዳለን። የዛሬዎቹ መስካሪዎች 2 ናቸው። እስከአሁን ፎቶአቸው አልደረሰኝም። ቦሌ/ክ/ከ ወረዳ 10 በቤት ቁጥር 0929 ነዋሪው አቶ ቴዎድሮስ ለማ ተሾመ እና 3ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ሆነው የቀረቡት በቦሌ ክ/ከ/ወ 6 እንደሆነ የተናገረው ዋና ሳጅን ያየህ ብርሃኑ ግዛው ናቸው። ዝርዝሩን እመለስበታለሁ። 
‼ዳኛ፦የፋንታሁን ባለቤት ያሏት ሴት እርስዎን እንዴት አወቀችዎት?
…ምስክር፦አታውቀኝም።
‼ዳኛ፦እርሷ ስትገባ ቢሮ ውስጥ ሌሎች ሠራተኞች ነበሩ?
…ምስክር፦አልነበሩም።
‼ዳኛ፦ፈንታሁን ከ20 ደቂቃ በኋላ መጣ ያሉት በዚያው ዕለት ነው?
…ምስክር፦ አዎ።
‼ዳኛ፦ከፈንታሁን ጋር የተገናኙት 2ቀን ብቻ ነው?
…ምስክር፦አዎ።
‼ዳኛ፦ፈንታሁን ከእስክንድር ስም ውጭ የሌሎች ሰዎችን ስም ጠቅሶ ነበር?
…ምስክር፦አልጠቀሰም።
‼ዳኛ፦ከዚህ ያሉ ሌሎች ተከሳሾችን ያውቋቸዋል?
…ምስክር፦አላውቃቸውም። ስማቸውንም ሰምቼ አላውቅም።
‼ዳኛ፦ፈንታሁን ወደ ቢሮ ገብቶ ሲነግርዎት የጠየቁት ጥያቄ ነበር?
…ምስክር፦አልነበረም።
‼ዳኛ፦ ፖሊስ ጣቢያ ምን ብለው አመለከቱ?
…ምስክር፦የምገደል መሆኔን።
‼ዳኛ፦ፈንታሁን ከየት ነው መሳሪያ እቀበላለሁ ያለዎት?
…ምስክር፦ አልነገረኝም። አላውቅም።
‼ዳኛ፦መሳሪያው ከየት እንደሚመጣና ማን እንደሚያስመጣው የተገለፀልዎት አለ?
…ምስክር፦የለም።
‼ዳኛ፦የታክሲ ተራ አስከባሪዎች ወረፋ ሳትጠብቁ የሚያሳፍሯችሁ ከፈንታሁን ጋር ወዳጅነት ስላላቸው ነው?
…ምስክር፦አላውቅም።
‼ዳኛ፦አቶ እስክንድርን ያውቋቸዋል?
…ምስክር፦አላውቀውም።
‼ዳኛ፦ዛሬ ነው ያዩዋቸው?
…ምስክር፦አዎ።
‼ዳኛ፦በሚዲያስ ያውቋቸዋል?
…ምስክር፦ልገደል እንደሆነ ከሰማሁ በኋላ እንጂ ከዚያ በፊት አላውቀውም።
‼ዳኛ፦ጥያቄያችንን ጨርሰናል።
Filed in: Amharic