ባሻዬ ጭንቁ
• ቅኔው ልዩ እንደሆነ ለተነገረለት ምልዕክታዊ የእስረኞች ፍቺ ፤
ከጅምላ አፈሳ ከእስር እንዲለቀቅ ለእያንዳንዳቸው የተጠየቀውን የ1ሺህ ብር የማስያዣ ዋስትና ፤ በአጠቃላይ
42 ሺህ ብር እና ተጨማሪ 10ሺህ ብር በድምሩ 52 ሺህ ብር አቶ ኤርምያስ ለገሰ Ermias Legesse Wakjira ድጋፍ አድርጓል ።
ከዚህ ቀደም እንደሚታወቀው ፤በመለስ ትሩፋት ባለቤት አልባ ከተማ መፅሀፍ ከተገኘ የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበር አቶ አንዱአለም አራጌ ከመፅሓፉ ከተገኘው ገቢ ሃያ በመቶው እሱ በእስር ቤት እያለ ለሁለት ልጆችህ የተወሰኑ ወራት የትምህርት ቤት ወጪ እንዲሆን 90 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጉ የሚታወቅ ነው።

እንዲሁም ፤ ” ጥላሁን ያረፈ ቀን” ከሚለው መፅሀፍ ሽያጭ 50 በመቶ ክንፈሚካኤል ደበበ( አበበ ቀስቶ) ህክምና እንዲሆን ስጦታውን አበርክቷል። በመጀመሪያው ዙር ለአበበ ቀስቶ 120 ሺህ ብር በወቅቱ እንደደረሰው ለማወቅ ተችሏል ።
አሁንም ለነጻነት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ደጋፊዎቹና ለነጻነት የሚቆረቆሩ ወገኖች ደጋፋቸውን ለመግለጽ በ አካባቢው ብቻ ስለተገኙ በአፈሳ ያለምንም ምክን ያት ከሶስት ቀን በላይ በ እስር ላይ ቆይተው ፍርድ ቤት እያንዳንዳቸው አንድ ሺ ብር ዋስ አስይዘው ወይም ከፍለው እንዲወጡ ያዘዘውን መሰረት አድርጎ ነው ድጋፉን ያደረገው።