>

የመጀመሪያው ክርክር ...!!! አበበ ገላው

የመጀመሪያው ክርክር …!!!

አበበ ገላው
የእኔና  የአቶ ኤርያስ የመጀመሪያው የፍርድ ቤት ክርክር አርብ October 29, 2021 10 am በ Fairfax Circuit Court ለመሰማት ቀጠሮ ተይዞለታል። በዚህ ኬዝ ላይ ቀደም ብሎ አሉታዊ ፕሮፓጋንዳ ቢነዛም እውነታው ለኮሚዩቲው ትልቅ ትምህርት ሊሰጥ የሚችል በአሜሪካን አገር ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትና የግለሰብን መብትና ስብዕናን በሚጥስ መልኩ ሃሰተኛ መረጃን ሆን ብሎ በሚድያ አማካኝነት ለህዝብ ማሰራጨት መካከል ያለውን ዳራ ይመለከታል።
ከዚህ በፊት ለመግለጽ እንደሞከርኩት በኢትዮ 360 ተዛብቶ ለህዝብ እንደተሰራጨው ሳይሆን አቶ ኤርሚያስ ለገሰ “የአብይ አህመድን ከባድ ሚስጥሮች” ስላጋለጠ ፈጽሞ አልተከሰሰም፤ ሊከሰስም አይችልም። የክሶች እውነተኛ ጭብጦች በአጭሩ የሚከተሉት ናቸው።
1ኛ/ አቶ ኤርምያስ ቴድሮስ ጽጋዬ ዩትዩብ ቻናል ላይ በመቅረብ የህወሃቱ ቁንጮ ደብረጽዮን ላይ ከዚህ በፊት የሰራሁትን የምርመራ ሪፖርት በመጥቀስ ደብረጽዮን ላይ “ፐርሶናል” የሆነ መረጃ አውጥቶበታል ከማለት አልፎ የግለሰቦችን ኢሜይል እንደምበረብር የሚያሳይ መረጃ [document] አለኝ በሚል በሃሰት በአደባባይ ስለወነጀለኝ፤
2ኛ/ ባለቤትነቱ የእኔ የሆነን የድምሽ መረጃ ጹሁፉ ግልባጭን

በመቀያየርና የHuman Rights Watch “ሪፖርት” በሚል ፎርጅ በማድረግ እኔን በሃሰት ለመወንጀል ሲል ብቻ ህዝብን በሚያሳስት መልኩ በሚድያና በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሃሰተኛ መረጃ ለህዝብ በማሰራጨት፤ [በነገራችን ላይ ይሄ ድርጊት በፎርጀሪ ወንጀል የሚያስጠይቅ ነው]፡፡

3ኛ/ ከእነ ጃዋር ሙሃመድና ሌሎች ሚኔሶታ ከሚኖሩ በስም ያልተጠቀሱ ግለሰቦች ጋር በመተባበር የትራንስፖርት ሚኒስትር የሆኑትን ወይዘሮ ዳግማዊ ሞገስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመመረቂያ ጽሁፍ ጋር በተያያዘ ስም ሊያጠፋ ሙከራ ሲያደርግ አስቆምነው በሚል በውሸት ስለወነጀለኝ [ጃዋርም ይሁን ሌሎች የሚኖሶታ ሶዎች የላኩትም ዶኩመንት ይሁም የሰጡት መመሪያ ፈጽሞ የሌለ ላም ባልዋለበት…አይነት ውንጀላ ነው።]
4ኛ/  ወ/ሮ ዳግማቲን በተመለከተ የተነሳው ጉዳይ ምንም እንኳን ከዘር ጋር ተያያዥነት የሌለው ከመመረቂያ ጽሁፍ ችግር [plagiarism] ጋር የተያያዘ ጉዳይ ቢሆንም እኔ አማራ ስለነሆነች ስሟን ለማጥፋት ጉዳዩን እንዳነሳሁ አድርጎ ከህዝብ ካር ለማቃቃር ሆን ብሎ በሃሰት ሚድያ ላይ ቀርቦ ስለወነጀለኝ፤
5ኛ/ በተደጋጋሚ እኔ በተመለከተ ሆን ብሎ ለህዝብ በሚድያ አማካኝነት ውሸት ማሰራጨቱን እንዲያቆም እንዲሁም ድርጊቱን በመተቸት የጻፍኩለትን መልክቶች “አስፈራራኝ” ቤተሰቤን አስጨነቀብኝ በሚል ከእኔ ባህሪም ይሁን ስብእና ተጻራሪ በሆነ መልኩ በሃሰት በአደባባይ ስለወነጀለኝ ነው። የክስ ፋይል ከከፈትኩ በሁዋላ የተጨመሩትን ሃሰተኛ ውንጀላዎች ሳይጨምር ክሶቹ እነዚሁ ናቸው!
በእኔ በኩል ይሄ ጉዳይ ፍርድ ቤት ባይደርስ እመርጥ ነበር፡፡ ይሁንና አቶ ኤርምያስ እኔን በሚመለከት ለህዝብ ያሰራጨውን ሃሰተኛ መረጃ እንዲያርም በተደጋጋሚ በአራት ደብዳቤዎች ጥያቄ ባቀርብለትም ምን ታመጣለህ በሚል ስሜት ስህተቱን ተቀብሎ ለማረም ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ በመሆኑም ጉዳዩ በፍርድ ቤት ውሳኔ እስከሚያገኝ ይቀጥላል።
በአርቡ ክርክር  አቶ ኤርሚያስ የፍርድ ቤት ጥሪና ክሱ [summons and complaint] በሰአቱ ቢደርሰውም ጊዚያዊ ጠበቃ ይዞ መልስ ለመስጠት 21 ቀናት ስላልበቃኝ መልስ የመስጫው ጊዜ በተጨማሪ 21 ቀናት ይራዘምልኝ ብሎ ጠይቋል። ችግሩ አሳማኝ ምክንያት [good cause] ማቅረቡ ላይ ነው፡፡ ክሱ እኔን ለማስተማር ወርቃማ እድል እንደፈጠረለት ሚድያ ላይ ሲያወራ ስለነበር በዚህ risky በሆነው ጥያቄ በጣም ተገርሚያለሁ፡፡ ፍርድ ቤቱ የሚቀርቡትን መረጃዎችና ክርክሮች አይቶና አዳምጦ ውሳኔ ይሰጥበታል። አቶ ኤርሚያስ ፍርድ ቤቱን በቂ ምክንያት አቅርቦ ካላሳመነ ክሱን በሙሉ እንዳመነ ተቆጥሮ ውሳኔ [default judgement] ይበየንበታል፡፡ የክሱም ሂደት በአጭሩ ይጠናቀቃል፡፡
እኔን በመወከል የምከራከረው እኔው ነኝ! ጉዳዩን ለመከታተል የሚፈልግ ማንም ሰው በቲቮዞ መንፈስ ሳይሆን በገለልተኛና ሚዛናዊ ህሊና ይከታተል፡፡
Filed in: Amharic