>

ኢትዮጵያ የተጋረጠባትን የሽብርና የኅልውና አደጋ ለመቋቋም የወዳጅ አገር እገዛ መጠየቅ ግድ ይላታል.... !!!  (አቻምየለህ ታምሩ)

ኢትዮጵያ የተጋረጠባትን የሽብርና የኅልውና አደጋ ለመቋቋም የወዳጅ አገር እገዛ መጠየቅ ግድ ይላታል…. !!!
 አቻምየለህ ታምሩ

የሞዛምቢክ መንግሥት አስከፊ አሸባሪዎችን ለመደምሰስ ያግዘው ዘንድ ወዳጅ አገር ለሚለው ለሩዋንዳ መንግሥት ጥያቄ አቅርቦ የሩዋንዳ መንግሥትም ወታደሮችን ወደ ሞዛምቢክ በማሰማራት አስከፊውን አሸባሪ ኃይል አይቀጡት ቅጣት መቀጣቱ የዚህ ወር ክስተት ነው።
በኛውም አገር እየሰማነው ያለውን ወራሪው የፋሽስት ወያኔ አምበጣ ሠራዊት በግፍ በወረራቸው የጎንደር፣ የወሎና የአፋር አካባቢዎች በወጣቶቻችን ላይ እየፈጸመ ያለው የጅምላ ፍጅት፤ በእናቶቻችንና በእኅቶቻችን ላይ እየፈጸመው የሚገኘውን ዘግናኝ አስገድዶ መድፈርና ሌሎች አሰቃቂ መልክ ያላቸው የወሲብ ጥቃቶች፤ የንብረት ውድመትና ዘረፋ ለማስቆም የሞዛምቢክን መንገድ በመከተል ለወዳጅ አገር ጥያቄ ማቅረብ የግድ የሚልበት ወቅት ላይ እንገኛለን።
የሞዛምቢክ መንግሥት የጎረቤት አገር ጦር እርዳታ እንዲያደርግለት ጥሪ ሲያስተላለፍ በአሸባሪነት የፈረጀው ቡድን በአገሪቱ ያደረሰው ጉዳት አሸባሪው ፋሽስት ወያኔ ያደረሰው ጥፋት አንድ መቶኛ አይሆንም። ስለዚህ መንግሥት ነኝ የሚል አካል ካለ ሳይውል ሳያድር ወዳጄ ለሚለው አገር መንግሥት ይፋዊ የድረሱልኝ ጥሪ አቅርቦ የፋሽስት ወያኔ ወራሪ አንበጣ ሠራዊት በተለይ በወሎ ምድር ቤት ለቤት እያካሄደው ያለውን የንጽሐን የጅምላ ፍጅትና እልቂት እንዲቆም ማድረግ አለበት።
ሞዛምቢክ አሸባሪ ብላ የፈረጀችውን ቡድን የደቀነባትን ጥቃት ለመቋቋም የወዳጅ አገር ጦር ከጋበዘች [የሩዋንዳ ጦር አሁንም ሞዛምቢክ ውስጥ እየተዋጋ ነው] ሞዛምቢክ ካጋጠማት የሽብር ቡድን በላይ አደጋ፣ ውድመትና እልቂት የሚያደርስ አሸባሪ ያጋጠማት ኢትዮጵያ የተጋረጠባትን የሽብርና የኅልውና አደጋ ለመቋቋም የወዳጅ አገር መንግሥት ያግዛት ዘንድ ጥሪ የማታቀርብበት አንዳች ምድራዊ ምክንያት የለም።
———–
The hard, unpopular but necessary decision to stop the industrial-scale massacre of youth, the widespread gang rape, and the sexual violence carried out by the invading Tigre People’s Liberation Front must be made now!
Filed in: Amharic