>

የጦር ገበሬዎቹን፤  ጄነራሎቹን ወደ ኋላ እየገፉ  ኢትዮጵያን የመታደግ ጥሪ ፌዝ ነው...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

የጦር ገበሬዎቹን፤  ጄነራሎቹን ወደ ኋላ እየገፉ  ኢትዮጵያን የመታደግ ጥሪ ፌዝ ነው…!!!
አቻምየለህ ታምሩ

ዐቢይ አሕመድ በአደባባይ እየወጣ ሲናገር ኢትዮጵያን ለመታደግ ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ እያለ ጥሪ ያቀርባል።

ይህንን የሰሙ አገር ወዳድ የኢትዮጵያ ልጆች በተለይም “የቀድሞው ጦር” ከፍተኛ ጀኔራሎች አገራቸው ያጋጠማትን የኅልውና አደጋ ለማስወገድ ባላቸው ችሎታና እውቀት አገራቸውን ያገለግሉ ዘንድ እንዲፈቀድላቸው ፍላጎታቸውን በተደጋጋሚ መግለጽ ብቻ ሳይሆን እድሉ ይመቻችላቸው ዘንድ እስከመለመን የደረሱም  አሉ። ሆኖም ግን የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ እስካሁን ድረስ ፍቃደኛ ሆኖ አገራቸውን እንዲታደጉ እድሉን ሊያመቻችላቸው አይፈለገም።
 ጀኔራል ተስፋዬ ሀብተ ማርያም የማያውቅ ሰው በአለም ላይ አይኖርም። ጀኔራል ተስፋዬ ሀብተማርያም በአለም ላይ ወደር የማይገኝላቸው በራሪ ነብር ናቸው።

 “ደርግ” ብሎ  አስሯቸው የነበረው ፋሽስት ወያኔ እንኳን ከሻዕብያ ጋር በነበረው ጦርነት ጠርቶ ተጠቅሞባቸዋል። ዐቢይ አሕመድ ግን ፋሽስት ወያኔ ከሻዕብያ ጋር በሚዋጋበት ወቅት ብሎ ካሉበት ጠርቶ  አየር ኃይሉን እንዲቀላቀሉ ያደረጋቸውን ጀኔራል ተስፋዬ ሀብተ ማርያም በዚህ ኢትዮጵያ የኅልውና አደጋ ላይ በወደቀችበት ወቅት አገራቸውን እንዲያገለግሉ በተደጋጋሚ ቢጠይቁትም ፍቃደኛ ሊሆን አልቻለም።
ወደር የማይገኝላቸው እኒህ ጀኔራል በአደባባይና ሜዲያ ላይ ቀርበው ብቻ ሳይሆን የአገዛዙን በሮች ጭምር በተደጋጋሚ አንኳኩተው የሚያናግራቸው ሰው እንኳን ባለመኖሩ ባላቸው እውቀትና ችሎታ አገራቸውን መታደግ  አልቻሉም።
 በዚህም በሀዘን ላይ ናቸው። የሐረር አካዴሚው ጀግና ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳም እንዲሁ። እነዚህን ሁለት ታዋቂ የጦር ጠበብት እንደ ምሳሌ አነሳሁ እንጂ በአገርም ውስጥ ሆነ በውጭ አገር የሚኖሩ ጦር ጭምር መምራት እንችላለን የሚሉ በርካታ አገር ወዳድ “የቀድሞ ጦር” ከፍተኛ መኮንኖች ቢኖሩም አገራቸውን ለማገልገል ለዐቢይ አሕመድ አገዛዝ ያቀረቡት ልመና ተቀባይነት ባለማግኘቱ  እንዲሁ እየተቃጠሉ አሉ።
ዐቢይ አሕመድ በአደባባዩ በሚያደርገው ንግግር ኢትዮጵያን ለመታደግ ሁሉም የበኩሉን ሚና ይወጣ ዘንድ ጥሪ ሲያቀርብ እነዚህ የአገር ፍቅር የሚያቃጥላቸው የቀድሞ ጦር ከፍተኛ መኮንኖች አገራቸውን ይታደጉ ዘንድ በተደጋጋሚ ጠይቀውት የከለከላቸው አይመስልም።
Filed in: Amharic