>

አንረሳውም....  !! አልረሳነውም...!!!   (ዘመድኩን በቀለ)

አንረሳውም….  !! አልረሳነውም…!!!  

ዘመድኩን በቀለ

… አንድም ትግሬ ይሄን አረመኔያዊና አስፀያፊ ድርጊት ሲያወግዝ ሰምቼ አላውቅም። አንድም ትግሬ ይሄን የሃገር ክህደት በስህተት እንኳ ሲቃወም ሰምቼ አላውቅም። አንድም ትግሬ በዚህ ጉዳይ ላይ በስህተት ሲተነፍስ አይቼው አላውቅም። እነሱ ራሳቸው በራሳቸው በቴሌቭዥናቸው ቀርበው ያመኑትን ወንጀል ሲያወግዙ ሰምቼ አላውቅም። ለ20 ዓመታት ሙሉ ቀን ከሌሊት ከጠላት ሲጠብቃቸው የነበረን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ባላሰበበትና ባልጠበቀው ሰዓት በድንገት በተኛበት ከጀርባው ማረዳቸውን እንዲህ በኩራት ሲናገሩ እንኳን አላፍሩም ነበር። አለማፈር ብቻ ሳይሆን የተቃወመ አንድም ትግሬ አልነበረም።
… ይሄን ድርጊት፣ ይሄን ጭካኔ መፈፀሙን ዐቢይ አህመድ አይደለም የነገረን፣ ዐቢይ ቢነግረን አናምነው ሊሆን ይችላል። ብርሃኑ ጁላም አይደለም የነገረን፣ ባጫ ደበሌም አይደለም የነገረን። ይሄ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ መፈጸሙን የነገረን ራሱ ጨፍጫፊው አካል አረመኔው ህወሓት በገሌው በሴኮቱሬ ጌታቸው በኩል ነው። አንድም ትግሬ ግን ይህንን ክፉ ድርጊት ሲያወግዝ አልታየም።
…እርግጥ ነው በወቅቱ ሰራዊቱ እንደሚታረድ የሚያውቁ ሦስቱ የኦሮሞ ጄነራሎች የተበከለ፣ የተመረዘ ምግብ በልተናል በሚል ምክንያት ቀድመው ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ እንዲሄዱ ተደርገዋል። ሰራዊቱ ቀን አንበጣ ሲያባርር ውሎ፣ የትግሬ ገበሬን እርሻ እህል ሲያጭድ ውሎ ማታ በተኛበት በዚያው በትግሬ ሰራዊት ተጨፍጭፏል። መኪና በላዩ ላይ ተነድቷል። ይህ ከሆነ ዛሬ አንደኛ ዓመቱ ሆነ።
…ይሄ በልቶ ካጅነት ነው። ይሄ ያጎረሰን እጅ መንከስ ነው። ይሄ አረመኔያዊነት ነው። ይሄ ከሃዲነት ነው። ይሄ ፍጹም ሰይጣናዊ ድርጊት ነው። ልቡሳነ ሥጋ አጋንንት ብቻ የሚፈጽመው ድርጊት ነው። የታረዱት የሰሜን ዕዝ አባላት ኢትዮጵያውያን ናቸው። ዐማራ፣ የዐማራ መኮንኖች በብዛት በዚያ እንዲከማቹ ተደርጎ ነው በጅምላ እንዲረሸኑ፣ እንዲታረዱ የተደረጉት። ሌሎች ኢትዮጵያውያንም አብረው ታርደዋል። ተጨፍጭፈዋል። ይሄ የፈጠራ ወሬ አይደለም። ራሷ ህወሓት እንደጀብዱ አደባባይ ወጥታ በምታዩት መልኩ በኩራት ደረቷን ነፍታ በግልጽ ያመነችው የወንጀል ድርጊት ነው። ድርጊቱ ከተፈጸመ ዛሬ አንድ ዓመት ሞላው። ጥያቄው የእነዚያ በግፍ የተጨፈጨፉ ምስኪን የኢትዮጵያ ወታደሮች ደም በከንቱ ፈስሶ ነው የሚቀረው? የሚለው ነው።
• ድል ለሃገሬ መከላከያ ሠራዊት።
• ሞትና ውድመት ለኢትዮጵያ ነቀርሳ ለህወሓት።
• ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።
• ክብር በየበረሃው ሃገሬን ከጭራቆች ለመከላከል ደፋ ቀና ለሚሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ።
• በግፍ በትግሬ ምድር ያታረዳችሁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንረሳችሁም።
• ነፍሳችሁ በሰላም ትረፍ።
Filed in: Amharic