አቻምየለህ ታምሩ
ይህ ወቅት አጥልቆ ማሰብ ግድ የሚልበት ወቅት ነው። ፋሽስት ወያኔ የተከፈተብን ጦርነት እንደ ዓድዋና ማይጨው ዘመቻ ዘሎ በመግባት የምንመልሰው አይደለም። ለወራት የሰለጠኑ ተዋጊዎችን በትኖና ከፋሽስት ወያኔ ዘመን በፊት ወታደራዊ ጠበብት የነበሩ የጦር አዋቂዎችን አግልሎ ቆመህ ጠብቀኝ የታጠቁ ሚሊሻዎችን በማዝመት የፋሽስት ወያኔ የግፍ ወረራ መቀልበስ አይቻልም። የግፍ ወረራውን መቀልበስ የሚቻለው የሰለጠኑ ተዋጊዎች በማዝመት፣ ከፋሽስት ወያኔ ዘመን በፊት ወታደራዊ ጠበብት የነበሩ የጦር አዋቂዎች ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ በማድረግና አሁን ያለውን የክላሽ /ቆመህ ጠብቀኝ versus የዲሽቃ፣ የስናይፐር፣ የብሬንና መሰል ከባድ መሣሪያዎች ትጥቅ ብዛት ባፋጣኝ መቀየር ከተቻለ ብቻ ነው።
በወገን በኩል ያለው የክላሽ፣ የዲሽቃ፣ የስናይፐር፣ የብሬንና መሰል ከባድ መሣሪያዎች ምጥጥን ጠላት ከታጠቀው የመሳሪያ አይነትና መጠን ጋር የማይመጣጠን ነው። ፋሽስት ወያኔ እየወረረ ያለው በሚሊሻ፣ በገበሬ፣ በክላሽና በቆመህ ጠብቀኝ ታጣቂ አይደለም። የወገን ጦር የታጠቀው የክላሽና ከባድ መሳሪያ ትጥቅ ንጽጽር ሲበዛ ቢውል ከ50-ለ-1 አይበልጥም። ይህ ማለት ከሀምሳ የወገን ታጣቂ ውስጥ ክላሽና ቆመህ ጠብቀኝ ታጣቂው 49 ሲሆን ዲሽቃ፣ ስናይፐር፣ ብሬንና መሰል ከባድ መሣሪያዎችን የታጠቀው ቁጥር ግን አንድ ብቻ ነው።
በተቃራኒው የቆመውና የወረረን የፋሽስት ወራሪ አንበጣ ሠራዊት በተለይም አጥቂው ክፍል የታጠቀውን ስንመለከት በብዛት የሚያጠቁባቸው መሳሪያዎቻቸው ክላሽና ቆመህ ጠብቀኝ ሳይሆኑ እንደ ዲሽቃ፣ ስናይፐር፣ ብሬንና መሰል ከባድ መሣሪያዎችን ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ፋሽስት ወያኔ በፖለቲካ አመለካከቱ ወይም በትውልድ ዘመኑ ለይቶ ያላሳተፈው የጦር አዋቂ የሚባል ሰው የለም። ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት እስከ ፋሽስት ወያኔ ዘመን ድረስ በውትድርና መስክ ተሳታፊ የነበሩ የጦር አዋቂዎችን በሙሉ እየተጠቀመ ነው። በወገን በኩል ግን እንኳንና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና በደርግ ዘመን የነበሩ የጦር ጠበብቶችን የዘመቻው አካል ለማድረግ ቀርቶ በፋሽስት ወያኔ ዘመን ሳይቀር በውጊያ ተሳታፊ የነበሩ የጦር አዋቂዎች እንኳን በዘመቻው እንዲሳተፉ አልተደረጉም።
ይህ አለመሆኑና ክላሽና ቆመህ ጠብቀኝ መሳሪያዎችን የታጠቀው የወገን ጦር ዲሽቃ፣ ስናይፐር፣ ብሬንና መሰል ከባድ መሣሪያዎችን ታጥቆ ከሚያጠቃው የፋሽስት ወያኔ ወራሪ አንበጣ ሠራዊት ጋር እንዲዋጋ መደረጉ እስካሁን ድረስ ያየነውን “ውጤት” አስገኝቷል።
ስለዚህ የወገን ጦር ወራሪውን የፋሽስት ወያኔ አንበጣ ሠራዊት እንዲቋቋም ከተፈለገ ከሁሉ በፊት አሁን ያለው የክላሽ /ቆመህ ጠብቀኝ versus የክላሽ፣ የዲሽቃ፣ የስናይፐር፣ የብሬንና መሰል ከባድ መሣሪያዎች ታጣቂዎች ቁጥር ባፋጣኝ መቀየር አለበት። በዲሽቃ፣ በስናይፐር፣ በብሬንና መሰል ከባድ መሣሪያዎች የሚያጠቃን ወራሪ አንበጣ ሠራዊት ክላሽና ቆመህ ጠብቀኝ በታጠቀ ያልሰለጠነ ገበሬና ሚሊሻ መከላከል አይቻልም።
ባጭሩ ፋሽስት ወያኔ የተከፈተብን ጦርነት እንደ ዓድዋና ማይጨው ጦርነት ዘሎ በመግባትና ገበሬ በማዝመት ብቻ መቀልበስ አንችልም። እስካሁን እድል ያላገኙ የጦር ጠበብት ተሳታፊ መሆን አለባቸው። ከዚህ ሁሉ በላይ አሁን ያለውን የክላሽ /ቆመህ ጠብቀኝ versus የዲሽቃ፣ የስናይፐር፣ የብሬንና መሰል ከባድ መሣሪያዎች ታጣቂው ቁጥርና ስብጥር መስተካከል አለበት።