>

አስደሳች ዜና፡-እውነትን ለምትወዱ ለፍትሃዊ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ!! አሌክስ ሸገር

አስደሳች ዜና፡-እውነትን ለምትወዱ ለፍትሃዊ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ!!
አሌክስ ሸገር

እነሆ ዛሬ  ለአምስት ቀን የፈጀው የአቃቤ መንግስት የሃሠት ምስክር  የሆነው የስድስተኛው የወርቁ ታደሠ ቶላ የምስክር ሂደት የተጠናቀቀ ሲሆን ከመጀመሪያው ወንጀለኛ የሃሠት ምስክር አቶ ይባስ ጀምሮ እስከ ዛሬው ስድስተኛ ምስክር ወርቁ ታደሠ ቶላ ድረስ አንድም ምስክር በአቃቤ መንግስት ተደርሶ የተሠጠውን የሃሠት እስክሪብት አጥንቶ በእነ እስክንድር ላይ ሊመሠክር በፍፁም አልቻለም በተለይም አቃቤ መንግስት ያቀረባቸው የሃሠት ምስክሮች እጅግ አደገኛ ወንጀለኛ እና አብዛኞቹም ከዚህ በፊት በሃሠት የመመስከር ልምድና ብቃቱ ያላቸው ቢሆንም እነሡን በውሸት ያሠለጠናቸውና ያስጠናቸው አካል
 (አቃቤ መንግስት) የሃሠት እስክሪብቱን ሲፅፍ ብዙ ነገሮችን በማጉደሉና የፃፈውንም የውሸት ድሪቶ በደንብ ማስጠናት ባለመቻሉ እንዲሁም   የአጠኑትንም ውሸት ለእውነትና ለሃቅ የቆሙት ጀግኖቹ ጠበቆቻችን ሄኖክ አክሊሉ ቤተማሪያም አለማየሁ እና ሠለሞን በመስቀለኛ ጥያቄ እያፋጠጡ እርቃናቸውን ስላስቀሩአቸው ተዋርደውና ተሸማቀው ከችሎት አንገታቸውን አቀርቅረው ሊወጡ ተገደዋል።
በዚህም ምክንያት እጅግ የተደናገጡት አቃቤ መንግስቶች በዳኛ ትዕዛዝ ሌሎች ምስክር አቅርቡ ቢባሉም ሠባተኛው ምስክር ኮረና ይዞት ማገገሚያ ገብቱአል ሌሎቹ ሶስቱ ምስክሮቻችን ደግሞ ሊቀርቡልን  ፍቃደኛ ስላልሆኑ ፍ/ቤቱ በግድ መተው እንዲመሠክሩ መጥሪያ ይፃፍልን ብለው ግዜ ለመውሠድ ሞክረዋል።
ከአቃቤ መንግስት ጥያቄ በኃላ ጀግኖች ጠበቆቻችን ለችሎቱ አቃቤ መንግስት ምስክር ማቅረብ ስላልፈለገ እና ስላልቻለ ፍ/ቤቱ የምስክር ሂደቱን እዚህ ላይ አቁሞ እስከዛሬ በተሠማው ላይ ውሳኔ ይስጥልን ብለው ተገቢ ጥያቄአቸውን ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር አዳምጦ
ምስክር ይቀጥል ይቁአረጥ ለሚለው ውሳኔ ለመስጠብ ለነገ ቀጠሮ ይዙአል።
እውነት ያሸንፋል ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!
#
 ከኢትዮጵያ ዋና
#ከተማ አዲስ አበባ
Filed in: Amharic