>

አዲስ አበባ፣ አዋጅ፣ ቁጥጥርና ሥጋት....!!! D.W

አዲስ አበባ፣ አዋጅ፣ ቁጥጥርና ሥጋት….!!!
D.W

ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)ና የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ጦር (ኦነጦ) ከአዲስ አበባ 250 ኪሎ ሜትር የምትርቀዉን ከሚሴ ከተማን መቆጣጠራቸዉን አስታዉቀዋል።ከገለልተኛ ምንጭ ግን ማረጋገጥ አልተቻለም።የኢትዮጵያ መንግስት ሁለቱንም  ቡድኖች በአሸባሪነት ፈርጇቸዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በበኩሉ የሐገሪቱ መንግስት ከትናንት በስቲያ ያወጀዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፅድቋል።አዋጁ ከተደነገገ በኋላ የአዲስ አበባ ፖሊስ በአሸባሪነት የተፈረጁት ቡድናት አባላት ወይም ተባባሪዎች በማለት የጠረጠራቸዉን ሰዎች ማሰሩን አስታዉቋል።ሮይተርስ ዜና አገልግሎት የፖሊስ ቃል አቀባይን ጠቅሶ እንደዘገበዉ የከተማይቱ መስተዳድር ባዘዘዉ መሰረት ነዋሪዉ ትጥቁን እያስመዘገበ ነዉ።በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የተወሰኑ ሠራተኞቹ እና ቤተሰቦቻቸዉ በፈቃዳቸዉ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ጠይቋል።የአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫም ለሥራ በጣም የማያስፈልጉ የአሜሪካ መንግስት ሠራተኞች እና በጣም የሚያስፈልጉ ሰራተኞች ቤተሰቦች ወደ ሐገራቸዉ እንዲመልሱ ፈቅዷል።
Filed in: Amharic