>
5:13 pm - Tuesday April 19, 8146

ዐቃቤ ሕግ ምስክሮቼን ማግኘት ስላልቻልኩ በፍርድ ቤት መጥሪያ ይጠሩልኝ አለ ! ባልደራስ

ዐቃቤ ሕግ ምስክሮቼን ማግኘት ስላልቻልኩ በፍርድ ቤት መጥሪያ ይጠሩልኝ አለ !
ባልደራስ

     የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ ዐቃቤ ሕግ አሉኙ ካላቸው እና ካስመዘገባቸው ዘጠኝ ምስክሮች ውስጥ የስድስት  ምስክሮች የመሰማት ሂደት በዛሬው ዕለተ ተጠናቀቀ ።
   ቀሪዎቹ ሦስት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በችሎት ቀርበው እንዲመስክሩ ዳኞች ቢጠይቁም፣ ” አራተኛ ምስክር በኮሮና ስለታመመ መምጣት አልቻለም፤ 8ኛ እና 9ኛ ምስክሮችን ደግሞ ማግኘት አልቻልኩም። በመሆኑም ፍርድ ቤት የመጥሪያ ትዕዛዝ በማውጣት እንዲያስጠራልን እንጠይቃለን፤ስለሆነም ምስክሮቼ እስከሚገኙ ተለዋዋጭ ቀጠሮ ይሰጠኝ።” በማለት ዐቃቤ ሕግ ለፍ/ቤቱ አቤቱታ አቅርቧል ።
  የእነ እስክንድር ጠበቆች በበኩላቸው  በዐቃቤ ሕግ ለቀረበው አቤቱታ በሰጡት ምላሽ ” ዐቃቤ  ሕግ አስቀድሞ 4ኛ፣8ኛ እና9ኛ  ምስክሮቹን ያስመዘገበው መጥተው እንደሚመሰክሩ እርግጥኛ በመሆኑ ነው ፤ ዐቃቤ ሕግ የምስክሮቹን አዳራሻ ባላወቀበት ሁኔት በፍርድ ቤት በመጥሪያ ይጠሩልኝ ማለት እና በዚህም ምክንያት ተለዋጭ ቀጠሮ መጠየቅ አግባብ ባለመሆኑ ምስክሮቹን ማቅረብ እንዳልቻለ ይቆጠርልን። በተጨማሪ በኮሮና ታመመ ስለተባለው 4ኛ ምስክር አቃቤ ሕግ ያቀረበው የህክምና ማስረጃ የለም በመሆኑም ደምበኞቻችን ላለፋት 15 ወራት ያለፍትህ ስለቆዩ ፣ፍ/ቤቱ እስካሁን ባደመጣቸው ምስክሮች መሰረት ፍትህ እንዲሰጠን እንጠይቃለን።” በማለት ለዐቃቤ ሕግ ምላሽ ሰጥተዋል ።
በተጨማሪም እስካሁን ድረስ ማንነታቸው ስላልታወቁት ሌሎች 12 ምስክሮች ጉዳይ እንዲሁም  4ኛ ተከሳሽ ወ/ሪት አስካለ ደምሌ ባቀረቡት ከቤተሰብ ጋር የስልክ ግንኙነትን በተመለከተ ብይን ለመስጠት ፍ/ቤቱ  ለነገ ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ጧዋት 4፡00 ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ።
Filed in: Amharic