”ችግሩን በፈጠረው ኣስተሳሰብ ችግሩን መፍታት ኣይቻልም”!!
የትግራይ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰሙናዊ መልእክት
የኣብይ ኣሕመድ ፋሽስት ቡድን በኣራት ግንባሮች በኣጠቃላይ በዋነኛነት በደቡብ ወሎ ግንባር በተለይም በደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ከሚሴና ሌሎች ከተሞች በትግራይ ሰራዊት የደረሰበትን ከፍተኛ ሰብአዊና ማተርያላዊ ኪሳራ ፋሽስት ቡድኑ የሙጥኝ ብሎ የያዘው ወንበር ተነቃንቆ መወዛወዝ መጀመሩ ኣረመኔው ቡድኑ ለኣንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ ከመንበረ ዙፋኑ የሚሰናበትበት ቀን ቅርብ መሆኑ በገሃድ በመታየት ላይ ይገኛል።
በየኣውደ ግንባሩ በሽንፈት ላይ ሽንፈት እየተጎነጨ ውርደት የእለት ቀለቡ የሆነው የፋሽስት ኣብይ ቡድን ማለትም ከምርኮኛ ሞት ያመለጠው ቅጥረኛ ታጣቂ ሃይሉ እንደ 100 ሜትር ሯጭ ያለ እረፍት የኋሊት እየሸመጠጠ ከኣዲስ ኣበባ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል። ሆኖም ይህ ፈርጣጭ ቅጥረኛ ታጣቂ ለጊዜው ሸሽቶ ያመለጠ ቢመስለውም የትም ኣይደርስም። ስለዚ ያለው ኣማራጭ ኣንድ እና ኣንድ ብቻ ነው። ይሀውም የታጠቀው የጥፋት የጦር መሳርያው የኢትዮጵያ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት የሆነውን የፋሽስት ኣብይ ኣሕመድ ቡዱን እድሜ ለማሳጠር እና የበደለወን ህዝብ ለመካስ ኣፈሙዙን ወደ ኣረመኔዎቹ ኣዙሮ ታሪካዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ከተጠያቂነት ሊድን ይባል። ካልሆነም ከነ መሳርያው እጁን ለትግራይ ሰራዊት ሰጥቶ ህይወቱን ማትረፍ ኣለበት። ኣሻፈረኝ ካለ ግን የማታ ማታ እጣ ፈንታው ከንቱ ሞት መሆኑ ራሱ ታጣቂው ሃይል እንዲሁም ወዳጅ እና ጠላትም ሊያውቅ ይገባል።
ቅጥረኛ ሰራዊቱ ያለ ማቛረጥ እግሩ ወደ መራው እየሸሸበት ያለው እንዲሁም የበሬ ወለደ ብቱቶ የሃሰት ፕሮፖጋንዳው እንደ ኣሮጌ ጎማ ከተነፈሰ ዋል ኣደር ያለበት የፋሽስት ኣብይ ቡድን በየኣውደ ግንባሩ የደረሰበት ሽንፈት ለማካካስ ማለትም ኣህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንዲሉ ሰሞኑ ከትግራይ ውጭ በተለያዩ የኢትዮጵያ ኣከባቢዎች በጠቅላላ በዋነኛነት በኣዲስ ኣበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በጅምላ ኣፍሶ በማይታወቁ ካምፖች ኣጉሮ እያሰቃያቸው ይገኛል። የሚበዙት ደግሞ ከስራ ገበታቸው በማባረር ላይ ነው። በኣጭሩ ይህንን እና ሌሎች መሰል ሰይጣናዊ እና ኣረመንያዊ የጀኖሳይድ ግፎች በትግራይ ተወላጆች ላይ መውሰድ ከጀመረ ሶስት ኣመት ተኩል ኣስቆጥረዋል። ሰሞኑ እየተወሰደው ያለው ጭካኔ የተሞላበት ኣስነዋሪ ኣፈሳ ለየት የሚያደርገው ባልና ሚስት ኣፍኖ በመውሰድ ምንም የማያውቁ ህፃናት ልጆች ኣውላላ ሜዳ ላይ ተጥለው በቁማቸው እንዲሰቃዩ መደረጋቸው ነው። እዚ ላይ ይህንን ሰብኣዊነት የጎደለው ኣረሜንያዊ ኣፈና ላይ ያቀዳቹ የመራቹ የፈፀማቹ እና ያስፈፀማቹ የኣመራራር ኣካላትና ኣባላት የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ከትግራይ ሰራዊት እጅ እንደማታመልጡ ልታውቁት ይገባል። ስለዚህ ኣሁንም ከዚህ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊታቹ እጃቹን እንድታነሱ ደግመን እናሳውቃለን።
ነገር ግን የፋሽሽስት ኣብይ ኣሕመድ ቡድን ያለ ምንም ሃጥያት የትግራይ ተወላጆች በመሆናቸው ብቻ ግፍ እያደረሰባቸው መሆኑ የተገነዘቡ ኣንዳንድ ርህሩህ ኢትዮጵያውያን የጅምላ ኣፈናው ሰለባ ገፈት ቀማሽ የሆኑ ልጆቹን በኣደራ ተቀብለው እየተንከባከብዋቸው ይገኛሉ። በዚ ኣጋጣሚ የትግራይ መንግስት የኣብይ ኣሕመድ ፋሽስት ቡድን እያካሄደው ባለው ጀኖሳይድ ሰለባ በሆኑ ቤተሰቦች እንዲሁም በኣጠቃላይ በትግራይ ህዝብ ስም ለበጎ ኣድራጊ ኢትዮጵያውያን ያለው ምስጋና የላቀ መሆኑ ሲገልፅ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም የናንተን ኣርኣያነት ተከትሎው የድርሻቸው እንደሚጫወቱ ተስፋ ያደርጋል።
በኣጭሩ የፋሽስት ኣብይ ኣሕመድ ቡድን ባለፉት ሶስት ኣመታት ተኩል በሆያ ሆየ ህዝቡን የሚያማልሉ እንዲሁም ያለማቀፉ ማህበረሰብ ውዥንብር ውስጥ የሚከቱ ቃላት በመጠቀም ለማደናገር ጥረዋል። ሆኖም ይህ ኣረመኔ ቡድን ለሃገር የሚጠቅም ራእይ እና ኣላማ እንደሌለው በተግባር ኣሳይተዋል። ለዚህም ነው የፋሽስት ቡድኑ ኮምፓስ እንደሌለው መርከብ መጨረሻው የታይታኒክ መርከብ ኣይነት እጣ ፈንታ ለመቀበል ሞት ኣፋፍ ላይ ደርሶ ያለው።
በመጨረሻ ታላቁ ሳይንቲስት ኣልበርት ኣንስታይን ”ችግሩን በፈጠረው ኣስተሳሰብ ችግሩን መፍታት ኣይቻልም”!! እንዳለው የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ የዓለም ማህበረሰብ ኢትዮጵያን ገደል ኣፋፍ ላይ ኣድርሷት ባለው የፋሽስት ቡድን የተወሳሰበ ችግርዋ ፈፅሞ ሊፈታ እንደማይችል ተገንዝቦ የፋሽስት ኣብይ ኣሕመድ ቡድንን በቃህ በማለት የድርሻው ሊጫወት ይገባል።
ህልውናችን እና ደህንነታችን በፈርጣማ ክንዳችን!!
ትግራይ ታሸንፋለች!!
የትግራይ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
ጥቅምት 26/2014 ዓ/ም