>

ሸዋ እና ህወሃት - የእውነት ጀምበር ስትዘልቅ...!!! ( ስሌማን አባይ)

ሸዋ እና ህወሃት – የእውነት ጀምበር ስትዘልቅ…!!!
 ስሌማን አባይ

መለስ ዜናዊ ስለ ሸዋ የተናገረውን በዚህች ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ላይ መለስ ብለን ማውሳት አስፈላጊ ነው። ወደ አዲስአበባ ለመግባት የአሜሪካን አደራዳሪነት የሚጠባበቀው የመለስ ዜናዊ ቡድን እኤአ1990 ላይ የዋሽንግተን ውስጥ አዋቂ ከሆኑት ፖል ሄንዝ ጋር ቆይታ ነበራቸው።
ከረጂሙ መጣጥፍ ውስጥ “ስለ ኢትዮጵያ ምንድነው ሐሳባችሁ?” በሚል የተጠየቀውን እናገኛለን።
MZ፦ እኛ ቅድሚያ ትግራይ አንደኛ ብለን ነው የተነሳነው። በዋናነት የሸዋ የበላይነት ነው ጠላታችን። ይህ የሚወገድ ከሆነ እንደ አገር መቀጠል እንችላለን። አማራ ላይ ማነጣጠር የሁሉም የትግል ድርጅቶች ዋነኛ ግብ ነው” ሲል ይመልሳል።
ፖል ይጠይቃሉ፦ “አማራ ስትል እንዴት? ግልፅ አርግልኝ። አሁን በያዛችሁት የአማራው መንዝ ላስታ መርሃቤቴ ወዘተ…ያሉ አማራዎች እየደገፏችሁ አይደል?”
MZ፦ “እኛ አማራ ስንል የሸዋ አማራን ማለታችን ነው። ሸዋ ባለፉት መቶ አመታት በአዲስአበባ ዙሪያ ፍፁም የበላይነትን አስፍኗል። ይህ የሸዋ ስነልቡና መፍረስ ያለበት ነው።” አሉ መለስ ዜናዊ።
በተዛማጅ አጀንዳ በትላንትናው ዕለት ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ ስለ ህወሃትና ሸዋ አንድ ፅሁፍ አስነብበውናል። በወሳኝ ሰዓት ነው የከተቧት። የፕራይም ቴቪ መስራች ስራ አስኪያጅና የመስኖ ፕሮጀክቶች ምኒስትር ዴታ ዶክተር ብርሃኑ “በወያኔ አገዛዝ እንደ ሸዋ የተዘረፈና የተበደለ አከባቢ አለ ማለት ያስቸግራል” ነው ያሉት።
የሸዋ ህዝብ ለውለታው አመድ አፋሽ ብቻ ሳይሆን የበደል መዓት ከህወሃት ሲወርድበት እንደነበር ብርሃኑ ሲጠቅሱ “መሬቱን ከመንጠቅ አንስቶ በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ላበረከተዉ ሚና ተቀጭ ሆኖ ነበር ሶስቱን አስርተ ዓመታት ያሳለፈዉ የሸዋ ህዝብ” ነበር ያሉት።
“ወያኔዎች መሪያቸዉ መለስ ዜናዊ የሞተ ጊዜ የሸዋ ፓለቲካ ተመልሶ ይመጣል በማለት ስጋታቸዉን በፅሑፍም ጭምር ያስቀመጡበት ወቅት ነበር” በማለትም ገልፀዋል።
የሸዋን ህዘብ ለማሸማቀቅና ሌላውም በሸዋ ላይ ጥላቻን እንዲያዳብር ህወሃት በትኩረት መስራቱን አስምረውበታል፤ ዶክተር ብርሃኑ። የኦሮሞ ጠላት አድርጎ መሳል አንዱ ዘዴ እንደተደረገ የገለፁት ብርሃኑ ይህ ለኦሮሙውም ጭምር ቀምበር ስለመሆኑ እንደሚከተለው ነው ያስቀመጡት “በሸዋዉ ላይ የነበራቸዉን የፖለቲካ አመለካከት በማደናገርያዎች አጅበው አስኪደውታል። ኦሮሞና አማራን ባላንጣ አርገዉ ስለዉ ቢቆዩም ከፖለቲካው ተገፍተው የቆዩት ግን የሸዋው ኦሮሞና የሸዋው አማራ ሁለቱም ነበሩ”
በፈንጅ ወረዳ ሰተት ብሎ ገብቶ የሞት ደወል የሚቆጥረው የህወሃት ስብስብ ከሰሞኑ ሸዋ ሸዋ ሲል ይሰማል። ሸዋ እዚህ ድረስ ሞኝ ይመስላቸዋል ማለት ነው። ሸዋ ጭቁን እንጂ ጀግንነቱን የውጭ ዜጋም ቢሆን ከሁለቱ ድርሳናት ብቻ መገንዘብ አያዳግተውም። የሸዋ ፋኖዎች ከባድ ዝግጅት ላይ ናቸው። ለ30 አመታት የቀበራቸውን ህወሃትን የሚቀብሩበት ታሪካዊ አጋጣሚ በእጃቸው ገብቷል። ይኸው ነው።
~ኢትዮጵያ ለህወሃት ቀብር እንጂ መንበር የላትም~
    እስሌማን ዓባይ
ዋቢ
Filed in: Amharic