>

መርጠን ጣት አንቀስር....!!! ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ

መርጠን ጣት አንቀስር….!!!

ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ

በዘመነ ካሴ፣ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ እና የአማራ ሕዝባዊ ኃይል በተመለከተ እነ አንዳርጋቸው ጽጌና ነዓምን ዘለቀን በጉያ አቅፎ ዓብይ አህመድንና የብአዴን ብልጽግናን መውቀስ ነውር ነው።
ባለፈው ሰሞን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ነዓምን ዘለቀ ባህርዳር ተገኝተው ለብአዴን ብልጽግና አመራሮች ሁለት ምክረ-ሃሳቦች አቅርበዋል።
አንደኛው ከባዕድ አገር ተሳትፎ ጋር የተያያዘ ሲሆን እነሱ እንደ አገናኝ(ደላላ) ሆነው መስራት እንደሚፈልጉ የገጹበት ነበር። የብአዴን የብልጽግና አመራሮች ንቀት ባዘለ ምላሻቸው ከባዕድ አገር ጋር ለሚፈጥሩት ግንኙነት ደላላ እንደማይፈልጉ በግልፅ ነግረዋቸዋል።
ሁለተኛው ከእነ ዘመነ ካሴና እየፈጠሩ ካሉት አደረጃጀት ጋር የተያያዘ ነበር ። እነ አንዳርጋቸው ጽጌ የሰጡት ምክረ-ሃሳብ ከብልፅግና እና መከላከያ ጠገግ ውጭ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል መደራጀት እንደሌለበትና አደራጆቹ እነ ዘመነ ካሴ በቁጥጥር ስር መዋል እንዳለባቸው ያሳሰቡበት ነበር። ለዚህም የአማራ ብልጽግና የሰጡት ምላሽ እነ ዘመነ ካሴን መንካት ከአማራ ሕዝብ ጋር በቀጥታ ስለሚያጋጫቸው ምክሩን ለፌዴራል መንግሥት ቢያቀርቡ የተሻለ እንደሆነ ነገረው አሰናብተዋቸዋል።
እናም መካሪዎቹን በጉያችን አዝለን ተመካሪውንና ትዕዛዝ ፈፃሚውን ብቻ አንውቀስ። መርጦ ጣት መቀሰር ነውር ነው።
በዚህ አጋጣሚ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና አቶ ነዓምን ዘለቀ በይፋ ወደ ሚዲያ ወጥተው የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲሰናበቱ ወንድማዊ ጥሪዬን አቀርባለሁ። አለበለዚያ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከኢሳት ስራ አስኪያጅነት ለምን ተገደህ እንድትለቅ እንደተደረገና በምትክህም በኢዜማ ውስጥ ያለው የግንቦት ስባት አመራር አቶ ደረጄ ተክሌን ለምን እንደመደበ ይፋ ለማድረግ እንገደዳለን።
Filed in: Amharic