>

ታላቁ እስክንድር ነጋ እንኳን ተወለድክ! (ጎዳና ያእቆብ)

ታላቁ እስክንድር ነጋ እንኳን ተወለድክ!

ጎዳና ያእቆብ

ትሁት፣ የፅናት ውሀ ልክ፣ የከትማ ባህታዊ፣ የዲሞክራሲና ሰብአዊ መብት ተሟጋች እናም ከሁሉ በላይ ሰው! ያውም የሰው ጥግ ….!! 
እንኳን ሰው ሰው የሚሸት ፣ አቋም ያለው፣ የእውነት ወዳጅ በጠፋበትና የምናከብረው ሰው ባጣንበት በኛ ዘመን ተወለድክ!! እንኳንም ከኢትዮጵያ አብራክ ተወለድክ!!!
ብዙ ስላንተ የሚዘከር ቢኖረኝም ሁሌ ከአዕምሮዬ የማይጠፋው በአንድ ወቅት የተጎዱ፣ የተገፉና የሚሸሸጉበት ጥግ ያጡ <<ሲደውሉልን በደወሉልን ሰአት ወደነሱ እሮጠን እንሄዳለን>> ሲለው  ጠያቂው <<ለመሆኑ ማስክ ታደርጋላችሁ ብሎ ሲጠይቀው>> ታላቁ እስክንድር እንዲህ ሲል መለሰ። << በእርግጥ ማስክ ይዘን ነው የምንሄደው። እዛ ስንደርስ ሰዎቹ (ጠሪዎቻችን ማለቱ ነው) ማስክ ካደረጉ እኛም እናደርጋለን። ማስክ ከሌላቸው ግን ሀዘን ያቆሰላቸው እና እራሳቸውን ለመጠበቅ ማስክ የሌላቸው ሰዎች ጋር እኛ ማስክ ማድረግ መመፃደቅ ነውና እኛም አውልቀን ከነሱ ጋር እንመሳሰላለን። ካለማስክ እንቆያለን። የጤና አደጋው ሳይገባን ቀርቶ ሳይሆን የነሱ ስሜት ከሚጎዳና ከሚሳቀቁ ህመምም ቢሆን ቢመጣብን እንመርጣለን።>> ሲል የተናገርው ሁሌም ይታወሰኛል።
 እኔ ያንተን ግማሽ ስብዕና ያለው ሰው ሆኜ ወደ መቃብሬ ከሄድኩኝ እጅግ ስኬታማ ህይወት እንደኖርኩ እቆጥረዋለሁ።
 አንተ መልካምነትን በጎነትን ለጋስነትን ታማኝነት የምለካብህ ውሃ ልኬ ነህ። ክበር! መልካሙን ቀን ፈጣሪ ያሳይህ!!
ንፁህ ሰው አይታሰርምና ከእስር ይፍታህ አልልህም። ከህሊና እስር ነፃ የሆነ ሰው ቢታሰርም ነፃ ነው። የህሊናው እስረኛ የሆነ ሰው ደግሞ በቤተ መንግስትም ቢቀመጥ እስረኛ ነው።
ግን ከቤተሰብህ ይቀላቅልህ ብዬ እመኝልሀለሁ። ፈጣሪ ይጠብቅህ። 
ከአብይ ያውጣህ!!!
Filed in: Amharic