ለእስክንድር ይሄ አይገባውም ነበር !!
ሰለሞን አላምኔ
እስክንድርን ቀደም ባለው ጊዜ ነው የማውቀው ሰው ነው። እኔ ፣ እስክንድር ነጋ እና ሲሳይ አጌና በጣም ቅርብ ጓደኞች ነበርን። እና እስክንድርን አሁን እያሉት ባለው ነገር በፍፁም አልስማማን በፍፁም፣ እሱ እንደዚህ ያለ ተግባር የሚፈፅም ሰው አይደለም። እንዴውም በተቃራኒው የሆነ ሰው እንጅ።
ከእኔ በላይ ከሲሳይ አጌና ጋር በጣም ቅርብ ወዳጅ ነበሩ። እስክንድር ሲታሰር ግን ሲሳይ ዝም በማለቱ እጅግ እጅግ በጣም አዝኛለሁ። አዎ በጣም አዝኛለሁ። እንዴውም የፍትሕ ስርዓቱ መፈተሻ እናደርገዋለን ብሎ ሲናገር ስሰማ በጣም ደንግጫለሁ። አዲስ አበባ በመጣ ጊዜ ሲሳይ አጌናን አግኘቸው ተጨዋውተናል። ስለ እስክንድርም ሳነሳበት ተበሳጨ! እንዳነሳበትም አልፈለገም ። ገረመኝ !! ለምን እንዳበሳጨውም አላውቅም። ግራ ገባኝ!! ለምን? በዚህ ልክ ብር የሰውን ልጅ ይቀይራል ብየ አላምንም ነበር ግን ገንዘብ የሰው ልጅ እንደሚቀይር አረጋግጫለሁ። በውነት በውነት ሲሳይ አጌና እንደዚህ በእስክንድር ላይ ፊቱን ያዞርበታል ብየ አላስብም ነበር።
ሰሞኑ መሳይ መኮነን አዲስ አበባ መጥቶ የተለያዩ ተቋሟትን ኢንተረቪው ሲያደርግ አይቻለሁ። ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወ/ሮ መ ዓዛ አሸናፊን ሲጠይቃት ነበር! ቴክስት ሁሉ አድርጌለት ነበር ። ( በነገርህ ላይ ከዚህ በፊት መዓዛ ላይ እምነት ነበረኝ! እምነቴ ግን የተሳሳተ ነበር። ያስዝናል!) ስለ እስክንድር እስር ምን ትያለሽ ብልህ ጠይቃት ብየ። እውነት ወንጀለኛ ከሆነ ለምን እስካሁን አቆያችሁት ብየ? #አይመልስም !! በጣም አዝኛለሁ።
እስክንድር ላይ ምንም ነገር እንደሌለ እርግጠኛ ነኝ። ለእስክንድር ይሄ አይገባውም ነበር። ለዚህች ሀገር ከፖለቲከኞች በላይ እስክንድር ዋጋ ከፍሏል። አሁን ደግሞ ፖለቲከኛ ሆኖ በግፍ እስር ቤት ዋጋ እየከፈለ ይገኛል። በአንድም በሌላ መልኩ ሀገር ዋጋ እየከፈለች ያለችው በእንደዚህ አይነት ነገር ነው።
ከመረጃ ቲቪ የተወሰደ
አለምነህ ደሴ
እኔም እላለሁ ፦ እስክንድር ቀንዲላችን ነው። ብቸኛችን። በዚህ ውጥንቅጡ በጠፋበት የሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ በትክክለኛው ሰዓት ተገኝቶ በኢትዮጲያ ውስጥ የዘር ማጥፋት እንደሚካሄድ ፤ ዜጎች በማንነታቸው ብቻ ለሞት ለመፋናቀል ለስደት ለብዙ መከራ እንደሚዳረጉ ፤ ተረኝነት እንዳለ ፤ የብሔር እንጅ የስርዓት ለውጥ እንዳልመጣ ፤ ይሄ ስርዓት ህግ ወጥ መሆኑን (በሠዓቱ) ፊት ወጥቶ የተናገረ ፤ ከኢሀዴጋውያን ለሀገር የሚበጅ ነገር ጠብ እንደማይል እና የህውሀት እና የኦህዴድ የስልጠን ሽኩቻ ሀገር እንደሚያናጋ ከማንም ቀድሞ የተናገረ ብቸኛ ሰው ነው እስክንድር። ለዚህም ነው በብቸኝነት ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ ግልፅ ጦርነት ያወጁበት!