>

"ወራሪውን ጠላት ኃይል አንድ ሆኖ ማጥፋት ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ...!!!" አማራ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ

“ወራሪውን ጠላት ኃይል አንድ ሆኖ ማጥፋት ጊዜ ሊሰጠው አይገባም …!!!”

አማራ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ


የፋሽስቱ ሞሶሎኒ የመንፈስ ልጅ የሆነውን አሸባሪውና ወራሪው የሕወሓት ቡድንን በአጭር ጊዜ ከስር መሰረቱ ለመንቀል ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት።

ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ እንደገለጹት፤ የአሸባሪው የሕወሓት ቡድን የአማራ ህዝብ ንብረት ለመዝረፍ አሰፍስፎ ወደ አማራ ክልል ዘልቆ ገብቷል። ይህ የጥፋት ኃይል የሚከተለው አዲስ ስልት ሳይሆን ፋሽስቱ ሞሶሎኒ ኢትዮጵያን ሲወር የተከተለው ነው፡፡ወራሪውን የሕወሓት ቡድን በአጭር ጊዜ ከሥር መሠረቱ ለመንቀል ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡

ይህ ወራሪ ሀይል ቅስሙ ከተሰበረና ከተወገደ ብቻ ነው መኖርም፣ መልማትምና መበልጸግ የሚቻለው ያሉት ጀነራሉ፤ኢትዮጵያ ሰላም ስትሆን ነው ሁሉም ነገር መልክ የሚይዘው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኀይል በመደራጀት እና ሎጀስቲክስ በማጠናከር በአጭር ጊዜ መደምሰስ እንደሚገባ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ አመልክተው፤የአማራ ወጣት፣ ባለሐብቱና ህዝቡ ድጋፉን በማጠናከር የወራሪ ኃይሉን መቀበሪያ ጊዜ ማሳጠር እንደሚኖርበት ገልጸዋል፡፡

ወራሪውን ጠላት ኃይል አንድ ሆኖ ማጥፋት ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ያሉት ጀነራሉ፤ይህ ኃይል ለ27 ዓመታት ለጦርነት የተዘጋጀ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ተፋልመው ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ የዛሬ አንድ ዓመት ጠርገውታል፡፡ማርከውታል፤ የቀረውንም ዋሻ ውስጥ ከተውት ነበር ብለዋል፡፡

ለወራሪው ኃይል መጠቀሚያና ተባባሪ የሆኑትን ሕዝቡ መንጥሮ ሊያወጣቸው እንደሚገባ አሳስበው፤ ለሠርጎ ገቦች ተገቢውንና ፈጣን ምላሽ መስጠት ያለበት ሕዝቡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለአሸባሪው ሕወሓት ሲሠሩ በሕዝቡ ጥቆማና በጸጥታ ኃይሎች ክትትል የተገኙትን መንግሥት ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድባቸው መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

የአማራ ህዝብ በሆነ ባልሆነው በጠላት ፕሮፖጋንዳ የሚረበሽ ህዝብ መሆን የለበትም ያሉት ጀነራሉ፤ይህ የወራሪ ኃይል በኢትዮጵያ ጀግኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስከ ዘላለሙ ይቀበራል ብለዋል፡፡

Filed in: Amharic