>

"እናቱን የከዳ ለሞግዚቱ አይጠቅምም" (ብርሀኑ ተክለያሬድ)

እናቱን የከዳ ለሞግዚቱ አይጠቅምም”
ብርሀኑ ተክለያሬድ

በየዘመኑ ለነፃነት የሚዋደቁ እልፍ ጀግኖች እንዳሉ ሁሉ ሀገራቸውን ከድተው የጠላት ዱቄት ተሸካሚ አጋሰስ ለመሆን የመረጡ አረሞች መብቀላቸውም አልቀረም።
ዛሬም ዳግማዊ “ኃይለሥላሴ ጉግሳዎች” ከክብር ውርደት፣ ከደጃዝማችነት ሹምባሽነት፣ከአርበኝነት ባንዳነት፣ የይሻለናል ብለው ለመጫን ጀርባቸውን አመቻችተዋል። አጋሰስነቱ ይመቻችሁ ከማለት ውጪ ለነሱ ከዚህ በላይ ትኩረት አያስፈልግም።
ኢትዮጵያን የጎዱ መስሏቸው እንጂ አሸካሚዎቻቸውም ከአጋሰስነት የዘለለ ሚና እንደሌላቸው አሳምረው ያውቃሉ። ኃይለሥላሴ ጉግሳን ጣሊያኖች የትግራይ ጠቅላይ ገዥ አድርገው ሲሾሙት አጋሰስነቱን ፈልገው ነበር።
ማርሻል ደቦኖ ስለእርሱ ሲገልፅ “እኔ እንዳጣራሁት ሕዝብ የሚያቅፈው ትልቅ ሰው አይደለም፤ የተዋጊነት ባህሪም የለውም፡፡ የተከበረበት ምክንያት ባባቱ ትልቅነት ነው፡፡ ይሁንና በንጉሡ ቪክቶር ኢማኑኤል ሳልሳዊ ሥም የትግራይ ጠቅላይ ገዢ ብዬ ሾምኩት፡፡ ጀነራል ሳንቲሊ ስለዚህ ሰው ሲነግረኝ ግን ፈሪና የሚያፈገፍግ ነው” ብሎኛል ሲል ፅፏል፡፡ ጣሊያኑ እንዳለውም እነሱ ሲሸነፉ ከጣሊያኖች ወደ እንግሊዞች ተሸካሚነት ለመዛወር ጊዜ አልወሰደበትም ነበር።
ባንዶችን እንደ አያቶቻቸው የውርደት እግረ ሙቅ ሽልማት የምናበረክትላቸው ጊዜ ሩቅ አይደለም። እስከዚያው በህልም ንግስናቸው እንዲደሰቱ ትተን ወደ አንገብጋቢ አጀንዳዎች እንዙር
ከታች የሚታዩት ምዕራባዊያን እስከመጨረሻው በሀገራችን ላይ ያላቸውን ንቀት ወካይ መግለጫዎች ናቸው።
ኢትዮጵያን በስማ በለው መምራት ይቻላል ብለው አስበው ሳይሆን በየትኛውም መንገድ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የማይመለሱ መሆናቸውን መግለጫ ነው።
እነዚህ ሰዎች ከብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ውጭ እራሳቸውን መግለጽ የማይችሉ ኑሮ የጠገረራቸው ድኩማን እንደሆኑ አቋቋማቸው ይመሰክራል።
በፖለቲካው ልምድ ያላቸው ከኋላ ሁነው መግፋት የመረጡት ጉዳዩ የማያወጣ ስለሆነ ነው። በዚህ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መነጋገር ጊዜ ማባከን ከፍ ሲልም ውርደት ነው።
ዋናው ነገር መሬት ላይ ያለውን እውነት በአጠረ ጊዜ  መቋጨት ነው።  ችግሩ መሬት ላይ የሰው ሃይል አለ። ወኔ አለ አቀናጅቶ የሚመራ እጥረት ግን ተከስቷል።
መንግሥታዊ ስልጣን ለችግር መፍቻ ሃይል እንጅ እውቀት አይሆንም ። የጦርነቱ አመራር ለአዋቂዎች ብቻ ሰጥቶ የፖለቲካ አመራሩ ድፕሎማሲው ላይ ቢያተኩር መልካም ነበር።
አሁን ችግራችን  በጦር ግንባር የእውቀትና የልምድ ክፍተት አለ። አሁን የቀድሞ ሠራዊትም ጥሪ ስለተደረገላቸው ተናበው በቂ ክህሎት ያለው ጦርነቱን ከመራው ችግሩ ይቀረፋል ቀላል ነው።
ችግሩን ያከበደው ፍላጎት እንጅ ልምድ በሌላቸው የጦር መኮንኖችና ፖለቲከኞች  ሜዳው መያዙ ነው። ሁኔታዎቹን ለባለሞያ ከተውናቸው እንኳን ለውጊያ ልምምድ የሚበቃ የጠላት ጦር የለንም።
ጦርነቱ የምዕራባውያን ፕሮፖጋንዳና ሙስናን ማሸነፍ መቻል ነው። ሰርጎ ገብ በምዕራባዊያን በሙስና የተያዙ ጀነራሎት መኖራቸው ከሰሞኑ ፕሮፖጋንዳ መረዳት ይቻላል። አዲስ አበባ ተከቧል ደርሰዋል የሚለው ወሬ ተፈጥሮ አልተወራም።  በዚያ አካባቢ ያለው የጦር መሪ ይሁንታ የሰጠበት ነገር ግን በሥራ ላይ ያላዋለው ወሬ መሆኑን መገንዘብ አይከፋም።
እርግጥ ነው ከተደገሰው አንጻር የመንግሥት ጥንካሬ ሊወደስ ይገባል። ብዙ አክሽፏል። ያልቻለው የጦር ሜዳውን ግዳጅ አፈጻጸም ነው። ይህን ሜዳ በሕይወታቸው ተወራርደው በወኔ ለተነሱ የጦር መሪዮች ምቹ አድርጎ  መተው እንደ መዋጋት ይቆጠራል።
እነዚህ መጠጥና ስኳር እየተፈራረቀ የሚያስቸግራቸው የጦር መኮኖች አርቆ ወኔ የገዛቸውን ፊት ለፊት ማምጣት ሁኔታውን በአጭር ጊዜ ለመጨረስ ይረዳል።
የዋሽግተኑን ግርግር ለጊዜው ብዙም ቦታ ባንሰጠው ጥሩ ነው። እንኳን ሀገር ሊመሩ በመንደር በእድርና በማህበራዊ ኑሮ አናውቃቸውም።
ቢሞቱ እንኳን ለሳምንት ተለምኖ በመዋጮ የሚቃበሩ ናቸው። የእነዚህን ስም ከኢትዮጵያ ጋር አያይዞ  ማንሳት ሀገርን ማሳነስ ነው። በውጭ ያለውን ማሕበረሰብ እንደ መስደብ ይቆጠራል። ብዙ ሀገር የሚያስጠራ አርቆ አሳቢ ምሁር አለ።
በውጭ ያለው በመንግሥት አሰራር ቢከፋ እንኳን በሀገሩ ጉዳይ አንድ ነው። ሀገሩን ለድርድር አያቀርብም። ብዙ የሃሳብ ልዩነቶች አሉ ።በኢትዮጵያ ጉዳይ አንድ ነው።
ብዙው ሰው በጥቃቅን ጉዳይ አይግባባም በሀገሩ አንድነት ዙሪያ ልዩነት የለውም።
የሀገር ቤቱ ነጸብራቅ ዘረኝነቱ ቢኖርም እንኳን በሀገሩ ጉዳይ አንድ ነው።
መሰዳደብ ፣መጠላለፍ ቢኖርም። እንደ ትግርኛ ተናጋሪዎች  ስደተኞች ሀገሩን ለክፉ አሳልፎ አይሰጥም። በውጭ ያሉ ትግርኛ ተናጋሪዎች ልብ ይስጣቸው ብሎ የሚጸለይላቸው በለይቶ ማቆያ መኖር የሚገባቸው ከሆኑ ቆይተዋል።
አደባባይ ወጥተው እንደ ማኀበረሰብ አማራን ውሻ አንድ ነው ብሎ መሳደብ የጤነኛ ሰው ምልክት አይደለም። አማራው እህል አንሰጥም እራሳችሁን ቻሉ አለ እንጅ ስጡኝ አላለም።መጥቼ ልኑር ብሎ አለመነም። በእየእውድማው እየዞረ በመለመን አይታወቅም። ታዲያ ለማኝ ለምኖ ሲያጣ ወደ የሚሰጠው ይሄዳል እንጅ ይህን ያህል የአደ ባባይ ስድብን ምን አመጣው? ብሎ መጠየቅ ይገባል።ገደላችሁን፣ ወረራችሁን ፣ብሎ ሰልፍ አልወጣም።  ሲፈልግ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል። የሰዎችን መብት ማስከበር ያለበት መንግሥት መሆኑን ይረዳል። መንግስታዊ ማዕከላዊነትን ይጠብቃል።
በራሱ ሲነሳ እንኳን ወደ እሱ መሬት ለመምጣት በመሬታቸው ላይ ለመኖር  የእሱ ይሁንታ የሚያስጠይቅ ጀግና ነው።
ጀግና በሆነ ባልሆነው አይነሳም። የግፍ ጽዋ ሞልቶ ሲፈስ ከተሳ መላሽ የለውም።
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሁልጊዜም የግፍ ጽዋ እስኪሞላ ይታገሳል። እውነቱ ይህ ነው።
ከዚያው ውጭ ተባብሮ መነሳት ጀምሯል። እውነቱን መሬት ላይ ታዩታላችሁ።  እኔ ታሪክና ባህልን ነው የምጽፈው የቆየ ውርስ ነው የምናገረው በመሬት ደግሞ እውነቱን ታዩታላችሁ።
ለማኛውም አሜሪካ የአፍሪካ መሪዎችን ለማስፈራራት የምታቋቁማቸው ፓርቲዎች አንዳቸውም ሀገራቸው ገብተው መንግሥት ሁነው አያውቁም።  እነዚህም መግለጫ ለመስጠት ያለፈበትን ፋሽን ተከታዮች ናቸው ብዙ ፊት አትስጧቸው እርሷቸው። ለወሬ አይበቁም።።
Filed in: Amharic