>

ካናዳዊ ጋዜጠኛጄፍ ፒርስ ለኢትዮጵያዊያን የላከው መልዕክት...!!! (ዮናስ አበራ )

ካናዳዊ ጋዜጠኛጄፍ ፒርስ ለኢትዮጵያዊያን የላከው መልዕክት…!!!
ዮናስ አበራ 

 በኢትዮጵያ ላይ የተቃጡ የውጪ ዘመቻዎችን በመመከት የኢትዮጵያ ወዳጅ እንደሆነ የሚታወቀው ካናዳዊ ጋዜጠኛ ጄፍ ፒርስ ኢትዮጵያዊያን የሃገራቸውን እውነታ ለማስረዳት ድምፃቸውን በጋራ እንዲያሰሙ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
 ለሃገራችሁ ክብርና ነጻነት በጋራ በቆማችሁበት በዚህ ወቅት አብሬአችሁ ብሆን ደስታዬ ነበር
አጠገባችሁ ባልገኝም እኔን ጨምሮ ምዕራባዊያን እና የተባባሩት መንግስታት በናንተ ላይ የሚፈጥሩትን ጫነሳ እና ጣልቃ ገብነት የሚቃወሙ በርካታ ወንድሞች እና እህቶች እዚህ ካናዳ፣ አሜሪካና አውሮፓ እንዳሉ ልነግራችሁ እወዳለሁ፡፡
 ቤተሰቦቻችሁ እና ጓደኞቻችሁ ለሃገራቸው መስዋዕት ለመክፈል ወደ ጦር ግንባር ሲሄዱ ማየት ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ በአሸባሪው ቡድን የተገደሉ ወገኖች በየቦታው ወድቀው ማየት እጅግ ያማል፡፡
 ነገር ግን ምርጫ የለም፡፡
 እነሱ እድል ካገኙ እናንተን ሊያጠፉ መሆኑን ታውቃላችሁ፡፡ አሁን አሁን ደግሞ የምዕራባዊያን መንግስታት አሸባሪው ቡድን እንዲገላችሁ እንደፈቀዱለት ግልፅ ሆኗል፡፡
 ስለዚህ ነጻነታችሁን ለማረጋገጥ ዋጋ መክፈል አለባችሁ፡፡ አያት ቅድመ አያቶቻችሁ በነፃነት እንድትኖሩ የከፈሉትን ዋጋ እናንተም ደግማችሁ ነጻነታችሁን አረጋግጡ፣ ራሳችሁን ከዚህ ገዳይ ቡድን አድኑ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ምዕራባዊያን እውነቱን ክደው ፊታቸውን ቢያዞሩባችሁም ሌሎች እውነቱን ተረድተው ለማሳወቅ የሚጥሩ ወገኖቻችሁ ከጎናችሁ መሆናቸውን መግለፅ እፈልጋለሁ፡፡
 እናንተ ኢትዮጵያ ናችሁ! በዓለም ላይ ብቸኛው የሰው ዘር መገኛ ምድር! አሁንም በከፍታ ላይ ያላችሁ፡፡ ስለዚህ በዚህ ጊዜ ባህር አቋርጦ ዋሺንግተን፣ ጀኔቫ፣ ብራስልስ እና ግብፅ ድረስ ሊሰማ የሚችል ድምጻችሁን በጋራና በአንድነት በማሰማት የሃገራችሁን እውነታ አሳውቁ፡፡
 ድምፃችሁ እንዲሰማ አድርጉ!
 ጫናዎቹን መቋቋም ትችላላችሁ!
 ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!”
  (ጄፍ ፒርስ)
Filed in: Amharic