ይለያል ዘንድሮ
ዘምሳሌ
የፀረኞች ኑሮ የአሸባሪ ኑሮ
የዘረኞች ኑሮ የወያኔ ኑሮ
የኦነግ ሸኔዎች ኑሮ
የኢትዮጵያ ጠላት ኑሮ
በግፍ ቢገሉንም መሄጃ እያሳጡ
ሰላም ቢነሱንም በእኛ እያሽሟጠጡ
ቆዳችን ከነነፍስ እየገሸለጡ
ቢፈጁን ቢፈጁን ሸሽተው ላያመልጡ
በዕብሪታቸው ከፍተው እኛን ሲያራውጡ
ገድለውን ገድለውን አለም ተነስቶብን
በሀገር ምድራችን እንደመጤ ታይተን
ለአመታት ስንኖር በነርሱ ተጠልተን
መሄጃ መድረሻ መተንፈሻ አጥተን
ቢያዩን አንቀንስ ከነሱ እየበዛን
ፀጋ ይሁን መርገም በእኛው ላይ ተጣብቶን
ተወቅሰን ተወግዘን በምንወዳት ሀገር
በተጋቡን ሰዎች ስማችን ሲሰበር
የለም ሲሉ አምሀራ ሲያደርጉን ባይተዋር
ሀብትም ሲዘርፉብን በግፍ ስንታስር
የሚዳኘን ጠፍቶ ሁሉ በውሸት ሲያብር
መከራችን በዝቶ ህዝባችን ሲወረር
እንዲህ ጊዜ ብሶ በኢትዮጵያ ልጅ እልቂት
እየተቃበሉ ሲገድሉት ሲበሉት ሲጥሉት
ስጋውን ዘልዝለው በልተው እንደከብት
ከዛም እያለፉ ገደል ሲጨምሩት
አይደርስ መስሏቸው ሰላም ሚሰፍንበት
አምሀሮች በሰላም ወጥተው ሚገቡበት
አንቀርም ተገፍተን በእንጉርጉሮ ኑሮ
ላመታት ብንኖርም ልባችን ተሰብሮ
በዋሾዎች ህብረት በስልጣን ቋጠሮ
መርዙን ምላሳቸው ህዝባችን ኣማርሮ
ከዘረኞች ትብታብ ትዕቢ አምባጓሮ
መኖር አቁመናል ከአሸባሪ አብሮ
ይለያል ይለያል ...ይለያል ዘንድሮ !!!