>

"በርካታ የህወሃት የጦር መሪዎች በሃሰተኛ አይሁድነት ማስረጃ እስራኤል ገብተዋል...!!!" ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ 

“በርካታ የህወሃት የጦር መሪዎች በሃሰተኛ አይሁድነት ማስረጃ እስራኤል ገብተዋል…!!!”
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ 
ዘ አዲስ

 

ከተጓዦቹ መካከል አራት ያህሉ በጦር ወንጀል የሚፈለጉ የህውሃት ከፍተኛ የጦር አበጋዞች ናቸው! 
 በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ካለው ያለመረጋጋት ጋር በተያያዘ እስራኤል በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ይሁዲዎችን በጥድፊያ ወደ ግዛቷ ለማስገባት ባደረገቸው ዘመቻ ነው  የጦር መሪዎች ጭምር የሚገኙበት በርካታ የህወሃት አባላት ወደ እስራኤል የገቡት።
ቻናል 13  የተሰኘ ሃገሪቱ የቴሌቪዥን ጣባያ ጠቅላይ  ሚንስትር ዶክተር አቢይ አህመድን ጠቅሶ እንደዘገበው በሃሰተኛ ማስረጃ በቤተ አይሁድነት ከተጓዙት ህውሃታውያን መካከል አራት ያህሉ በኢትዮጵያ በጦር ወንጀለኝነት የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች ናቸው። ጠቅላይ ምኒስትር  አቢይ አህመድም ቅሬታቸውን ለእስራኤሉ አቻቸው ናፍታሊ ቤኔት ገልጸውላቸዋል ብሏል ጋዜጣው።
ጠቅላይ ምኒስትር አቢ አህመድ በጉዳዩ ላይ በቅርቡ ከእስራኤሉ አቻቸው ጋር በስልክ ከመምከራቸው ቀደም ብሎ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ባደረጉት ማጣራት በቀርቡ በፈላሸናት ወደ እስራኤል ከገቡት በርካታ ሰዎች መካከል ሰባ ሰባት ያህሉ ኢትዮጵያውያን ይሁዲዎች ያለመሆናቸውን አረጋግጠዋል።
 ቤተ እስራኤላውያኑን  ከኢትዮጵያ በጥድፊያ ለማስወጣት የተከናወነው ዘመቻ የቀድሞው የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤን ያሚን ኔትናያሁ ስልጣን ከመልቀቃቸው የመጨረሻ ሳምንታት መካሄዱ ሲነገር የጦርነት ስጋት ካለባቸው የኢትዮጵያ ግዛቶች  77 ሰዎች ለማሰወጣትም ከ 4.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወጪ መሆኑ ታውቋል።
 በተለይም ከ77ቱ መካከል 53ቱ ከቤተ እስራኤላዊ የይሁዲ ነገዶች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የላቸውም ሲል የቴለቪቭ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ማረጋግጡን ዘገባው አመልክቷል።
Filed in: Amharic