>

“አሜሪካ የሽብር ቡድኑን የምትደግፈው የራሷን አጀንዳ የሚያስፈፅም መንግሥት ለመመስረት በማሰቧ ነው”  ሔርሜላ አረጋዊ፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የሲ.ቢ.ኤስ ጋዜጠኛ

አሜሪካ የሽብር ቡድኑን የምትደግፈው የራሷን አጀንዳ የሚያስፈፅም መንግሥት ለመመስረት በማሰቧ ነው” 
ሔርሜላ አረጋዊ፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የሲ.ቢ.ኤስ ጋዜጠኛ

 (ኢ ፕ ድ)
አሜሪካ የሕወሓት የሽብር ቡድንን የምትደግፈው የራሷን አጀንዳ የሚያስፈፅም መንግሥት ለመመስረት በማሰቧ ነው ስትል ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የሲ.ቢ.ኤስ ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ ገለፀች፡፡
ጋዜጠኛ ሔርሜላ እንዳስታወቀችው አሜሪካም ሆነች አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት አሁን ባለው የዶክተር ዐቢይ መንግሥት ደስተኛ እንዳልሆኑና ይህም ደግሞ የሆነው እንደ ሕወሓት የእነርሱን አጀንዳ የሚያስፈፅም መንግሥት ስላልሆነ ነው ስትል ትናግራለች፡፡
እንደ ሔርሜላ ንግግር አሜሪካና ጀሌዎቿ ሕወሓትን የሚደግፉት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ቀጠናዊ የፖለቲካ የበላይነት ለማረጋገጥ ከመፈለግ አንፃር ሲሆን፤ ለዚህም ደግሞ እንደ ሕወሓት ያለ ለእነርሱ የሚያጎበድድና ሀሳባቸውን ከዳር የሚያደርስ ተላላኪ መንግሥት በኢትዮጵያ ውስጥ ስላላገኙ ነው ስትል ሀሳቧን ትገልጻለች፡፡
“አሜሪካም ሆነች ሌሎች ምዕራባውያን ሀገራት የዐቢይ አሕመድን መንግሥት ያልፈለጉት ዐቢይ እጅግ ጠንካራና እርሱ በሚመራት ሀገር ላይ ለእነርሱ ፍላጎት የማያጎበድድ መሆኑን ስለተረዱ ነው፡፡” የምትለው ጋዜጠኛ ሔርሜላ፤ ይሄ ይሁን እንጂ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚጠላውና በፍፁም ወደ ስልጣን እንዲመለስ ከማይልጉት ከሕወሓት ጋር አሜሪካ ለመሥራት ማሰቧ የተሳሳተ ውሳኔ እንደሆነ አውስታለች።
Filed in: Amharic