>
5:18 pm - Thursday June 15, 2778

የጨነቀለት የውሸት ካብ ይናድና እውነት በከፍታው ላይ ትወጣለች...!!!  (ጎዳና ያእቆብ)

የጨነቀለት የውሸት ካብ ይናድና እውነት በከፍታው ላይ ትወጣለች…!!! 

ጎዳና ያእቆብ

 

አሁን ካለው ጦርነት የተገኘ አንድ መልካም ነገር ቢኖር እነ አብይ አህመድ ትላንት ጨቋኝ ዘረኛ እና ቅኝ ገዢ እያሉ ለፓለቲካ ትርፍ በሀሰት ሲከሷቸውና ካለ ስማቸው ስም ሲያወጡላቸው የነበሩትን አባቶቻችንን ማሞገስ ማወደስና ብሎም የአባቶቻችን ልጆች ነን ማለት መቻላቸው ነው።
*..  ጨከን ብሎ <<የአባታችን ልጆች ነን።>> አለኮ ወይ ጊዜ! አዳነችም <<የአድዋ ልጆች መሆናችንን እረስተው በአገዋ ያስፈራሩናል>> እያለች ስትሸልል የሚታየኝ ቅንጡና ውድ መነፅሯ ነበር
ምንም እንኳን አምነውበት ነው የሚል ግምት ባይኖረኝም  ለፖለቲካ ትርፍም እንኳን ቢሆን እንደ ኮሶ የሚመራቸው እውነት በነሱ አንደበት መነገሩ መልካም ነው።
ጨከን ብሎ <<የአባታችን ልጆች ነን።>> አለኮ ወይ ጊዜ! አዳነችም <<የአድዋ ልጆች መሆናችንን እረስተው በአገዋ ያስፈራሩናል>> እያለች ስትሸልል የሚታየኝ ቅንጡና ውድ መነፅሯ ነበር። ለ
ማንኛውም በጋራ በተደረገው ምርመራ የወጣው ሪፓርት አብይ አህመድ ባወጣው መግለጫ ላይ እንኳን በግልፅ እንደተቀመጠው የሚሸፍነው ጦርነቱ ተጀምሮ መንግስት የጥሞና ጊዜ ብሎ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ብቻ መሆንን ልብ ማለት ያስፈልጋል።
 ረሀብን እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቀሙ የሚለው ክስ ደግሞ ማዕከላዊው መንግስት ትግራይን ለቆ ከወጣና ከበባውን ከጀመረ በኃላ መሆኑን ማወቅ እንደነ አዳነች አይነቱ ንቁውን አዲስ አበቤ ማሳመን እና ምስደናገር እንዳትችል ይጠቅማል።
 የወጣው ሪፖርት ከበባ አለ፣ መንግስት እርዳታ እንዳይገባ ቀዳዳዎቹን ሁሉ ደፍኗል የተባለለትን ከትግራይ ለቆ ከወጣ በኃላ ያለውን ጊዜ አይጨምርም።
እነ ማርክ ሎኮክ አቤቱታቸውን ያቀረቡበት ሰነድ/ሪፖርት አያካትትም። ያንን ግን እነ አብይ አህመድ ጠንቅቀው ያውቃሉ። እንዴት አወቅክ ካላችሁኝ ስለ ሪፖርቱ ሀተታ በሰጠበት ዘንግ ያለ ፅሁፉ ላይ በግልፅ አስቀምጦታልና ነው። ነገር ግን እውነታውን ማወቃቸው ለህዝብ ከመዋሸት አያግዳቸውም።
  ጉዳያቸው የህዝብን ስሜት መኮርኮር እንጂ ለጭንቅላት መናገር ስላልሆነ ቅጥፈታቸውን እንደሚቀጥሉበት ግልፅ ነው።
አዳነች አቤቤ በውሸት ከሰውን የገዛ ሪፓርታቸው ነፃ ሲያወጣ አንድም ሚዲያቸው አልዘገበውም ስትል ነፃ የሚያወጣ ነገር እንደሌለ ጠፍቷት አይደለም።
ረሀብን እንደ ጦር መሳሪያ በዛን ወቅት አልተጠቀሙም ሲባል በሪፖርቱ ላይ ማቅረባቸውም የሚደንቅ ነው።
ለምን ብለው በዛን ወቅት ይጠቀሙታል? የህዋሃትን ፅህፈት ቤት የብልፅግና ፅህፈት ቤት ብለው በሚለውጡበትና ጊዜአዊ አስተዳዳሪ አሰምስርተው አዛዥ ናዛዥ በነበሩበት ወራት ስለምን ረሀብን እንደ ጦር መሳሪያ ይጠቀሙታልና ነው ሪፓርቱ ተጠቀሙት አልተጠቀሙት የሚል ብያኔ ላይ የሚደርሰው?
ያ ክስ የመጣው ከትግራይ ለቀው ከወጡ በኃላ፤ ይህ ሪፖርት ሙሉ በሙሉ የጠናውና ያጠነጠነው ከትግራይ ለቀውሳይወጡ እስካለው ጊዜ ድረስ ብቻ። ቶም ክሩዝ ማይኖሪቲ ሪፖርት በተሰኘው ፊልም ላይ ወደፊት ስለምትሰራው ወንጀል በቁጥጥር ስር ውለሀል ይል እንደነበረው ሆኖባቸው ካልሆነ በስተቀር ጉዳዩ ገና እየሰፋ የሚሄድ ነው።
 የዘር ማጥፋት ወንጀል ከሚለው ማምለጥ ባይሆን ትልቅ ነጥብ ነው። ያም ቢሆን special intent ማቋቋም አልቻሉም ወይም አልቻልንም የሚል ይሆናል። ይው ሪፓርት የጦር ወንጀልና በሰብአዊነት ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ተፈፅመዋል ይላልና መቼም ጉደኞች ነን መርጠን እንደምናለቅሰው ሁሉ መርጠን ከሪፖርቱ ካልተቀበልን በስተቀር ከአራቱ atrocity ወንጀሎች ኢትዮጵያ በሁለቱ በመከሰስ 50 ከ100 አምጥታለች።
 ይህንን ጠንቅቃ የምታውቀው አዳነች አቤቤ ግን አይኗን በጨው አጥባ ነፃ ወጣ እያለች የብልፅግና ካድሬዎችን እና  ሀገር ወዳድና ኩሩውን ወጣት ታስጨፍረዋለች። ወይ ዘመን!!!

https://www.facebook.com/fanabroadcasting/videos/789542721857356/

Filed in: Amharic