ዶር ቢቂላ ሁሪሣ
በዚህ የሕልውና ዘመቻ ላይም ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውም ለመጠበቅ በፍፁም አርበኘነት ስሜት ከዳር ዳር እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። በዚህም በአሁን ወቅት ኢትዮጵያውያን በአርበኝነት ንቅናቄ ላይ ናቸው። ፈተናው ለሕዝቦች የጋራ እንቅስቃሴ መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል።
ከአድዋ ወቅት ከነበረው ንቅናቄ ባልተናነሰ መልኩ ሕዝቡ በአርበኘንት ከዳር ዳር ተነቃንቀዋል። ይህም የሕዝቦች አርበኝነት ንቅናቄ ሦስት መሠረታዊ ሂደቶች ያሉት ሲሆን:-
-አንደኛው ሀገርህን ለማዳን ዝመት ይላል። -ሁለተኛውም ጠብቅ የሚል መርህ ያለው ሲሆን በዚህም ሕዝቦች እኔ እያለሁ በአከባቢዬ ፈፅሞ ሽብርና ወንጀል ቦታ አይኖረውም በሚል በንቃት አከባቢያቸውን በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
-ሦስተኛው መሠረታዊ ሀሳብ ደግፍ የሚል ሲሆን፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በቁስም በገንዘብም በስነልቦናም በመደገፍ የሀገር ሕልውና ዘመቻውን ከግብ ማድረስና የሀገርን ድል ማብሰር ነው።
ለዚህም ሀገራችንና ሕዝቧ ያልተነካ እምቅ የሆነ አቅም እንዳለው እያሳየ ይገኛል።” –