>
5:33 pm - Saturday December 5, 1981

"ኢትዮጵያን ለድርድር ማስገደድ የሚችል ኃይል በምዕራባዊያን ምናብ ውስጥ ብቻ ነው ያለው...!!!" ኬንያዊው ፖለቲከኛ ፋራህ ማሊም

ኢትዮጵያን ለድርድር ማስገደድ የሚችል ኃይል በምዕራባዊያን ምናብ ውስጥ ብቻ ነው ያለው…!!!”
ኬንያዊው ፖለቲከኛ ፋራህ ማሊም

ኅዳር 4/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት አዲስ አበባ ውስጥ ዘልቆ መግባት ወይም የኢትዮጵያ መንግሥትን ለድርድር ማስገደድ የሚችልበት ጠንካራ ኃይል ያለው በምዕራባዊያን ኒዮኮሎኒያሊስቶች ምናብ ውስጥ ብቻ ነው አሉ፤ የኬንያው ፖለቲከኛ ፋራህ ማሊም።
የኬንያ ብሔራዊ ጉባኤ የቀድሞው ምክትል አፈ ጉባኤና የፓርላማ አባል እንዲሁም ፖለቲከኛ ፋራህ ማሊም ምዕራባዊያን የ120 ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያዊያንን ፈቃድ መሻር አይችሉም ብለዋል፡፡
ከኢትዮጵያ እውነት ጎን የቆሙት ፖለቲካኛው ጦርነቱን በእነ ሲኤንኤን፣ ቢቢሲና ሌሎች የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን የፈጠራ ወሬ እናሸንፋለን ብለው ተስፋ የሰነቁ ካሉ አሸባሪው ሕወሓት ድል ያደርጋል ብለው ዘላለም ሲጠብቁ ይኑሩ ሲሉ ከዚህ ቀደም መጻፋቸው ይታወሳል።
አዲስ አበባ እገባለሁ ብሎ የፎከረውና ከመደበቂያ ዋሻው የራቀው የሽብር ቡድኑ በፈፀመው ስህተት ራሱን እያጠፋ እንደሆነም ጠቁመው ነበር።
ኬንያዊው ፖለቲከኛ “ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ናዚ የሆነውን አሸባሪውን ሕወሓት የግድ ማስወገድ አለባት፤ ይህን የማድረግ አቅሙም አላት” የሚል እምነትም አላቸው።
Filed in: Amharic