>

"የአሜሪካ ነገር ....!!!"   ግርማ ካሳ

“የአሜሪካ ነገር ….!!!”  

ግርማ ካሳ

ማንም አሜሪካ ያሉ “አዋቂዎች ነን : ተንታኞች ነን ወዘተ ” የሚሉትን እየሰማን “አሜሪካ እንዲህ ልታደርግ ነው:: ኢትዮጵያን ልትወር ነው” ብሎ መደናገጥ የአሜሪካን ሲስተምና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎችን አለመረዳት ነው::
Foreign Policy የሚባል ጋዜጣ አለ:: እንዲሁም ፖለቲኮ ብሉምበርግ የሚባሉ:: በዚያ ላይ የሚፅፉ ሰዎች ተራ ጋዜጠኞች ናቸው:: ባለስልጣናት አይደሉም:: ወያኔዎች በገንዘባችው የገዙዋቸውም ሊሆኑም  ይችላሉ::
1ኛ እሜሪካ  ህግ የበላይ የሆነባት አገር ናት:: በዚያ ወታደሮች ወደ ሌላ አገር ለመላክ ህጋዊ መስፈርቶች አሉ:: በህጋቸውም መሰረት ጦርነት ማወጅ የሚችለው ኮንግረስ ብቻ ነው:: በኮንግረስ ደግሞ የአፍሪካ ጉዳይ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ካረን ባስ የተናገሩትና ኮሚቴውም ያረቀቀውን አዋጅ የምናውቀው ነው::
2ኛ  አሜሪካ ኢትዮጽያን በማጥቃት ምን ጥቅም ነው የምታገኘው ?  አሁን ባለው ሁኔታ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ታስፈልጋታለች እንጂ  ኢትዮጵያ ለእሜሪካ አታስፈልጋትም::
አንርሳ አንድ ሶስተኛ የመንግስት ባጀት የሚሸፈነው በውጭ ድጋፍ ነው:: ራሳችንን የቻልን እይደለንም:: እሁን ደግሞ በጦርነቱ ራሳችንን በራሳችን ብዙ አውድመናል:: በአማራ ክልል ብቻ ከ 5 ቢሊዮን ዶላር ወይም 250 ቢሊዮን ብር በላይ ውድመት ተከስቱዋል::
ጀርመኖች በሁለተኛ አለም ጦርነት ከወደሙ በሁውላ ማርሻል ፕላን በሚል እሜሪካኖች ደግፈዋቸው ነው እንደገና እንሰራርተው የተነሱት:: እኛም በቶሎ ተነስተን ራሳችንን እስክንችል ድጋፍ ያስፈልገናል::
3ኛ  የአሜሪካ ጥቅም የሚጠበቀው ጠንካራ የተረጋጋች ኢትዮጽያ ስትኖር ነው:: ህወህት ያኔ አገር አረጋግታ ትገዛ ስለነበር ህወሃቶች ወደ ስልጣን ከመጡ አገር ማረጋጋት ይችላሉ የሚል እምነት አንዳንድ ባለስልጣናት ነበራቸው::
ነገር ግን አሁን የህወሃት ነገር ያበቃለት እንደሆነ እይተረዱ ነው:: ለህወሃቶች ያደሉ ነበር:: አሁን ግን ህወሃት የችግሩ አንዱ አካል እንደሆነ እያወቁ ነው:: ታዲያ ማንን ለማገዝ ነው ኢትዮጵያ ጦርነት የሚከፍቱት ?
4ኛ  በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በአፍሪካ ህብረት የሚመራ ድርድር እንዲደረግ ተወስኑዋል:: ከዚያ ድርድር ማእቀፍ ውጭ የአፍሪካ ህብረት የተባበሩት መንግስታትን ወደ ጎን አድርጋ ወታደራዊ እርምጃ ያውም የእፍሪካ እናት የሆነችው ኢትዮጵያ ላይ የምተወስድ እብድ አገር አይደለችም::
5ኛ  እንደው ነገሮች ከፍተው እሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ እርምጅ መውሰድ ከፈለገች ደግሞ ወታደራዊ  እርምጃ መውሰድ አያስፈልጋትም::  አጋር  አገሮችን አስተባብራ ሙሉ የኢኮኖሚ እቀባ ማስደረግ ትችላለች:: ኢትዮጵያን ከኩባ እኩል ከመደበቻት ደግሞ ከአሜሪክ ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ሁሉ መላክ ሊችግር ይችላል:: ይሄ ከሆነ ደግሞ በአገራችን ኢኮኖሚ ላይ ምን ሊክተል እንደሚችል መገመት አያስቸግርም::
አሜሪካኖች በኢትዮጵያ መረጋጋት እንዲኖር ስለሚፈልጉ መረጋጋት እንዲኖር ደግሞ ብሄራዊ መግባባት እንዲኖር ግፊት እያደረጉ ነው:: አሁን ያለው ጦርነት እንዲቆም ይፈልጋሉ:: ይሄን ማለታቸው ደግሞ ምንም ችግር አለው ?
እርሱንም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት የማጥቃት ዘመቻውን ጀምሮ ጥሩ ውጤትን ማስመዝገብ ከቻለ የሃይል ሚዛኑን አይተው አሜሪካኖች ህወሃቶችን ለቃቹህ ውጡ ነው የሚሉዋቸው:
Filed in: Amharic