>

የእለቱ የእነ እስክንድር ችሎት ውሎ... !!! ባልደራስ

የእለቱ የእነ እስክንድር ችሎት ውሎ… !!!

ባልደራስ
በእነ እስክንድር መዝገብ ለህዳር 6 ተቀጥሮ የነበረው ችሎት ቀሪ ምስክሮቹን የማሰማት ሂደትና ሌሎች 12ቱ ምስክሮች ስም ዝርዝር እንዲያቀርብ ታዝዞ ነበር ለዛሬ የተቀጠረው።
ተከሳሾች እነ እስክንድር ነጋ በተቀጠሩት መሰረት እና ፍርድ ቤቱ በቀጠረው መሰረት እኛም በተፈቀደል ሰዓት በሰዓቱ ቢገኝም አቃቢ ሕግ ግን ቡና ልጠጣ በሚል በሰዓቱ ሳይገኝ ቀርቶ ለ15 ደቂቃ ያክል ችሌቱ ዘግይቶ ነበረ የጀመረው።
አቃቢ ሕግም በታዘዘው መሰረት 3ቱ ምስክሮቹን አቅርቦ በችሎቱ እንዲያሰማ እና የ12ቱ ምስክሮች ስም ዝርዝር እንዲያቀርብ በግራ ዳኛዋ ቢጠየቅም አቃቢ ሕግ 1ኛው ምስክር በኮሮና ምክንያት ስላልተሻለውና ነገ ማቅረብ እንደሚችል እንዲሁም 2ቱ ምስክሮች አድራሻቸው ባለማወቁ ለፌደራል ፖሊስ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥበት ቢጠየቅም ትዕዛዙ ወጩ ስለተደረገ ማግኘት አቻልኩም ሲል ተከራክሯል
12ቱ ምስክሮቹን በተመለከተ አቃቢ ህግ ከዚህ በፊት ለአንድ አመት ሲያከራክር ቆይቶ ብይን የተሰጠበትን በግልፅ ችሎት እንዲያሰማ እና ስም ዝርዝር ለተከሳሽ እንዲሰጥ ጉዳይ እንደገና ዛሬ በማንሳት ስም ዝርዝር አልሰጥም ይግባኝ እጠይቃለሁ ሲል ተከራክሯል።
በፍርድ ቤቱ መልስ ስጡበት የተባሉት የተከሳሽ ጠበቆችም አቃቢ ሕግ አንደኛው ምስክር በኮሮና ታሟል ያለውን ምስክር ፍርድ ቤቱ የህክምና ማስረጃ እንዲያቀርብ ቢታዘዝም የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ባለማክበር በዘፈቀደ ምስክሬን ላሰማ ማለቱ ፍርድ ቤቱ ሊቀበለው አይገባም ፤ ሁሉትን ምስክሮች በተመለከተ ደግሞ አቃቢ ሕግ በትክክል የችሎቱን ጉዳይ እንደማይመለከተው ማሳያ ነው ምክንያቱም የመጥሪያ ትዕዛዝ ማን እንዳወጣው አላውቅም ማለቱ አቃቢ ህግ ሆን ብሎ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ችሎቱን ለማጓተት እና ለማዘግየት ፈልጎ ስለሆነ የተከበረው ፍርድ ቤት ውድቅ እንዲያደርገው እንዲሁም 12ቱ ምስክሮች በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ውስኔ የሰጠበትን ጉዳይ እንደገና ዛሬ አንስቶ ስም ዝርዝር አልሰጥም ማለቱ የአቃቢ ህግን ቁመና ምን እንደሆነ በማየት ፍርድ ቤቱ እስካሁን በተሰሙ ምስክሮች ብቻ ችሎቱን እንዲመራው እንጠይቃልን ብለው ተከሯክረዋል።
#ውሳኔ
የግራ ቀኙ ክርክት የሰማው ፍርድ ቤቱ 1ኛው ምስክር ነገ ቀርቦ ምስክር እንዲመሰክር ፤ 2ቱ ምስክሮች ለሐሙስ ቀርበው እንዲመሰክሩ እንዲሁም 12ቱን ምስክሮች ስም ዝርዝር እንዲያቀርብ ውሳኔ ሰጥቶበታል። ችሎቱም ነገ ይቀጥላል። አዲስ አበቤ ከወዲሁ ሱሪህን ጠበቅ አድርግ
በተያያዘ ዜና የምኒልክ ቴሌቭዥን ጋዜጤኛው አዲሱ አበበ በእነ እስክንድር መዝገብ አዘጋገብ ላይ አቃቢ ህግ ክስ መስርቶበት ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ታዝዞ የነበረ  ሲሆን መጥሪያውንም ተቀብሎ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ክስ ላይ መልስ ይዞ እንዲቀርብ ለረቡዕ 08.06.2014 ታዛል።
ሰላማዊ ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል
ድል ለዲሞክራሲ
Filed in: Amharic