>

ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል!! የአዳነች አቤቤ ንግግር እጅግ አደገኛ መርዝ ነው!!! (ዮሴፍ የየሱስ ወርቅ)

ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል!!
የአዳነች አቤቤ ንግግር እጅግ አደገኛ መርዝ ነው!!!
ዮሴፍ የየሱስ ወርቅ

 

*…. አዳነች ልትነግረን የምትፈልገው ጦርነቱ ይቁምና የትግራይ ህዝብ በህዝበ ውሳኔ ከኢትዮጵያ ጋር መቀጠል አልፈልግም ካለ ይሂድ ነው..  !
በቴሌቪዝን መስኮት ቀርባ አዳነች አቤቤ ወያኔ ኢትዮጵያን ማፍረስ ሳያስፈልገው ራሱ ባፀደቀው ህገመንግስት ውስጥ ከኢትዮጵያ ጋር አልቀጥልም ያለ የሚገነጠልበት አንቀፅ አለና ከፈለጉ እሱን ተጠቅሞ መሄድ ነው የሚል  መልእክት አስተላልፋለች!!
በተደጋጋሚ በዚህ ጦርነት ዙሪያ በግሌ የምሰጠው እስተያየት ላይ በሁለቱም ወገን ሆነው እየተዋጉ ያሉት የቀድሞው አንድ ኢህአዴጎች ከተመቻቸው ብቻ የሚፈልጏትን ” የውሸት ኢትዮጵያ” በምናብ መስርተው ባልተመቻቸው ጊዜ በፌዴራሊዝም ስም ባስቀመጡት ህገመንግስት አሊያም በጦርነት የኔ የሚሉትን ክልል ከኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ለመገንጠል የሚሰሩ  ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች መሆናቸውን ለማሳየት ሞክሪያለሁ!!
አዳነች ልትነግረን የምትፈልገው ጦርነቱ ይቁምና የትግራይ ህዝብ በህዝበ ውሳኔ ከኢትዮጵያ ጋር መቀጠል አልፈልግም ካለ ይሂድ ነው
ምናልባትም የፊንፊኔ ከንቲባነቷን  በማንኛውም ጊዜ ካጣችው ጌታዋ አብይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን ተገዶም ሆነ ተገፍቶ ቢለቅ እንደ ወያኔ ወንድሞቻችን ኦሮምያን የመገንጠሉን ጉዳይ ስንፈልግ በህገመንግስቱ ካልሆነም በጦርነት ማሳካት እንችላለን ነው!!!
ኢትዮጵያ የሚባል ሰፈር ክልል ቦታ አገር በሌለበት ኢትዮጵያዊ የሚባል ዜጋ በሌለበት ኢህአዴግ በዘረጋው ና 30 አመታት ባስቆጠረው ህገመንግስታዊ ስርአት ውስጥ ያሉት  አስር ክልሎች መዳረሻም ከኢትዮጵያ ፌዴሬሽን መገንጠልን ባፀደቀ ህገመንግስት ዙሪያ ያጠነጠነ ነው!!
አባቶቻችን  ህይወታቸውን  ገብረው ያቆዩት ን አድዋ ማይጨው ልጆቻቸውም በስልሳ ሺ በላይ ህይወት የተጋደሉለት ባድመ ዛላንበሳ  የትግራይ ህዝብና ወያኔ ብቻ በፈለጉ ጊዜ ከኢትዮጲያ እንዲገነጠሉ የመወሰን መብት የሰጣቸውን ጭራቅ ህገመንግስት በምንም ምክንያት እንደ አንድ አገራዊ ሰነድ ተቆጥሮ የችግር መፍቻነት እንዲሆን የሚፈልጉትን የቀደሞው አንድ ኢህአዴጎች
የአሁኑን ወያኔና ብልፅግናዎች ያለ አንዳች ልዩነት አምርሮ መታገል ይገባል!!
በምንም ምክንያት የትግራይን የመገንጠል ጥያቄ ለወያኔና ለትግራይ ህዝብ ብቻ  የተሰጠ መብት አድርጎ የሚደነግገውን ጭራቅ ህገመንግስት አልቀበልም!!!
ስለ አድዋ አክሱም መቀሌ ለመወሰን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ያገባዋል!!!
ትግራይ የወያኔና የትግራይ ህዝብ ብቻ አይደለችም!!
የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ!!!!

https://www.facebook.com/479008082529953/videos/690711218571060/

Filed in: Amharic