>

“ምዕራባውያንና መገናኛ ብዙኃኖቻቸው ስለጦርነቱ መነሻ እውቅና መስጠት አይፈልጉም”(ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን)

ምዕራባውያንና መገናኛ ብዙኃኖቻቸው ስለጦርነቱ መነሻ እውቅና መስጠት አይፈልጉም” 
– ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን- የህወሓት መስራችና አንጋፋ ፖለቲከኛ 
(ኢ ፕ ድ) 

ምዕራባውያንና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃኖቻቸው ለሴራና ለሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመቆማቸው ለጦርነቱ መነሻ ምክንያት እውቅና መስጠት እንደማይ ፈልጉ የህወሓት መስራችና አንገፋ ፖለቲከኛ ኢንጂነር ግደይ ዘረዓጽዮን ገለጹ።
ኢንጂነር ግደይ ዘረዓጽዮን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ምዕራባውያንና ሚዲያዎቻቸው መንግሥት በትግራይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደፈጸመና የትግራይ ህዝብ ላይ በደል እንዳደረሰ አስመስለው ህዝባቸውን በሀሰት መረጃ አሳምነዋል። እነዚህ አገራትና ዓለም አቀፉ መገናኛ ብዙኃን የጦርነቱ መነሻ ምክንያት ምን እንደነበር እውቅና መስጠት የማይፈልጉ ናቸው።
ሕወሓት ጦርነቱን እንደጀመረው የዓለም አቀፉን መገናኛ ብዙኃን ለማደናገር የተጠቀመበት ሂደት ፈጣንእንደነበር ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን አስታውሰው፤ ከእርሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸውና ተመራማሪ ነን የሚሉ፣ ታዋቂ ሰዎችንና በየአገራቱም ከመንግሥታት ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች ተጠቅሞ በአንድ ጊዜ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ማሰራጩትን ገልጸዋል። ይሁንና አሸባሪው ሕወሓት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት አድርሶ ጦርነት መጀመሩን የሚያውቁ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን እውነታውን ከመዘገብ መቆጠባቸውን ጠቅሰዋል።
ጦርነቱ በተቀሰቀሰ ወቅት የአውሮፓ ህብረትም ሆነ የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ትግራይ ላይ የተፈጸመ የዘር ማጥፋት ሂደት በማለት ተከራክረው ውሳኔ ከመሳለፍ ይልቅ የጦርነቱ መንስኤ ምን እንደነበርና ምን ሙከራዎች ተደርገው እንደነበር የሚሉ እውነታዎችን መግለጥ እንዳልፈለጉ ኢንጂነር ግደይ ተናግረዋል። እነዚህ አካላት ስለ ጦርነቱ መነሻ ምክንያት ማንሳት አለመቻላቸውም በኢትዮጵያ ላይ ሴራ እንዳላቸው ማሳያ መሆኑን ነው የጠቆሙት።
Filed in: Amharic