>

ፍትህ ለእስክንድር ብሎ ግልገል አምባገነንን መጠየቅ ቅንጦት ይሆን ?  (የምስራች ደጀኔ)

ፍትህ ለእስክንድር ብሎ ግልገል አምባገነንን መጠየቅ ቅንጦት ይሆን ? 
የምስራች ደጀኔ

ፍትህ ብለህ የምትጠይቀው ፍትህን የሚያውቅ ሀቅ የማይተናነቀውን ራስ ወዳድ ያልሆነን ነው። 
የብልፅግና መንግስት እስክንድርን ያሰረው በአዲስ አበባ ላይ የሚያካሂደውን ሌብነት ኦሮሙማ ብሎ የሚፈነጭበት ገደብ የሌለው አፕታይቱን እንደፈለገው እንዳይቀበትት ጥያቄ በማንሳት አላላውስ ስላለ ነው ( ብዙሃኑ የሚያውቀው አድር ባይ አደዝዳዥ እስከ ጀሌዎቹ የሚክደው እውነታ )
እስክንድር ለአመነበት መስዋዕት መክፈሉ ለቤተሰቡ የሚያጎድለውን ማሰብ ህመሙ እዚህ ማስፈርም አይቻልም ከባድም ነው ( ለብዙ ምስኪኖችንም አጉድሏል )። እስኬውን አስሮ ሀቅን መቅበር የማይሆን ነው ። እየወጣ ባገኘው ሚዲያ የሚቀባጥረው በየፌዝቡኩ አፉን የሚከፍተው ብቻ ሳይሆን #እስክንድር_ነጋ_ፈንታ ከምንም ወንጀል ፅድት ማለቱን አሳሪውም ድብን አድርጎ ያውቃል።
እውነትና ፍትህ ቀን የገጠሙ ቀን በምንም ነፃ ሰው መሆኑ ይብላኝ ለውሸታም ያስብላል።
“A lie can travel around the world and back again while the truth is lacing up its boots.” Mark Twain.
እውነት አትንቀዥቀዥም ‼
እስኬው ዛሬም ሆዳም እርምጥምጡን ባየሁ ጊዜ ላንተ ያለኝ ክብር ከትላንቱ ቢጨምር እንጂ ቅንጣት የሚቀንስ አይደለም በፍፁምምም

እስክንድር ብርቱ 

ድል ለእውነተኛ ዲሞክራሲ

Filed in: Amharic