>

80ዎቹ እንደ ዛሬ!! (ኢ ፕ ድ)

80ዎቹ_እንደ ዛሬ!!

ኢ ፕ ድ

*… ግንቦት 19 ቀን 1983 ዓ.ም  አሜሪካ ከለንደን የህወሓት ወታደሮች አዲስ አበባ እንዲገቡ ትእዛዝ የሰጠችበት ታሪክ
ይህ የዋሽንግተን ፓስት ዘገባ የባይደንን አስተዳደር የዛሬ ፍላጎት የሚያሳይ የ1983ቱን ታሪክ አትቷል።
ጊዜው 1983 ዓ.ም ነው። ቦታው ለንደን። ሰኞ። የኢትዮጵያ ልዑካን ለለንደኑ ድርድር ለንደን ተገኝቷል።
የወቅቱ ሁኔታ ወሳኝ ሰው አሜሪካዊው ዲፕሎማት ኸርማን ኮኸን ከድርድሩ አስቀድሞ የህወሓት ጦር አዲስ አበባ እንዲገባ ያለበት መግለጫ ከዛሬው “የአዲስ አበባ ተከባለች” ዘገባና እና የአሜሪካ ጦር ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነው ከተባለበት ዘገባ ጋር በይዘቱ ፍጹም አንድ ባይሆንም የሚያመሳስለው ፍላጎት አለ።
ዋሽንግተን ፖስት እአአ ግንቦት 28 ቀን 1990 ባወጣው ዘርዘር ያለ ዘገባ፤ በህወሓት የሚራው ሰራዊት ወደ አዲስ አበባ እንዲገባ ትዛዝ የሰጠው የአሜሪከ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ከፍተኛ ባለስልጣን ነው ሲል አስነብቧል።
የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ እንደሚያሳየው  አሜሪካ የሰላም ድርድር በሚል  በወቅቱ የነበሩ የደርግ ባለስልጣናትንና ሌሎች ቡድኖችን ለንደን ጠርታ ባለችበት ወቅት አሜሪካ ለህወሓት መራሹ አማጺ አዲስ አባበ ግቡ የሚል ትዛዝ ሰጥታለች።
የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሀፊ እና የሰላም ድርድር አወያይ የነበሩት ኸርማን ኮኸን በቀጥታ በቴሌቪዥን በመቅረብም በኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ተስማምተዋል የሚል መግለጫ እንደሰጡ የዋሽንግተን ፖስት የያኔው ዘገባ ያሳያል።
የቀድሞ መንግስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶ/ር አሻግሬ ይገለጡ አሜሪካ በኸርማን ኮኸን አማካኝነት የሰራችውን ሸፍጥ በተመለከተ ከሁለት አመት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢሳት በሰጡት ቃለመጠይቅ አብራርተዋል።
ዶ/ር አሻግሬ በወቅቱ እሳቸውን ጨምሮ ሰባት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ለንደን ለድርድር ሄደው እንደነበረና፤ ኸርማን ኮኸን እራሱ ሆቴል ውስጥ እንገናኝ ብሎ እሁድ ቀን አግኝቷቸው በጥሩ ስሜት ከተነጋገሩ በኋላ፤ ለማክሰኞ ቀጠሮ ይዘው በተለያዩበት አጋጣሚ፤ በድጋሜ ሰኞ ጠዋት ኮኸን ደውሎ በአስቸኳይ ሆቴሌ ድረስ ኑ የሚል ትዛዝ እንደሰጣቸው ያስታውሳሉ።
ኸርማን ኮኸን ሆቴል ሲደርሱም፤ “ተስፋዬ ገ/ኪዳን የአሜሪካ መንግስት ለእሱ ጥገኝነት እንዲሰጠውና የህውሓት ሰራዊት አዲስ አበባ ይግባ ብሏል” የሚል መረጃ እንደሰጣቸውና  ይሄንኑ ለማረጋገጥ ወደ ኢትዮጵያ ስልክ እየደወሉ ባለበት አጋጣሚ ኮኸን በሰበር ዜና መግለጫ እየሰጠ፤ “ጀግናው የትግራይ ነፃ አውጪ ሰራዊት ለ17 ዓመታት ሲታገል ቆይቶ ወደ አዲስ አበባ ገብቷል፤ አሜሪካም ሙሉ ድጋፍ ትሰጠዋለች” የሚል ያልተጠበቀ መረጃ መስጠቱን እንደተመለከቱና በዚህም የልዑካን ቡድኑ አባላት ግራ መጋባታቸውን ዶ/ር አሻግሬ ተናግረዋል።
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአዲስ ወግ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው እንዳሉት ደግሞ፤ አሁን የገጠመን ጦርነት የማጭበርበር ጦርነት ነው። ይህ  የማጭበርበር ስልት ልክ ዛሬ እንደሚገረገው በ1983 ተደርጓል” በማለት ሀገር በማጭበርበር የማይፈታ ይልቁንም እኛ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያ ሆነን እንደኖርነው ሁሉ ኢትዮጵያ ሆነን እንሞታለን። ማሸነፋችንም ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለውም ሲሉ አስረግጠው መናገራቸው ይታወሳል።
Filed in: Amharic