ዩናይትድ ስቴትስ
D W
አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ጦር ግንባር መሄዳቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙሀን ከዘገቡ በኋላ ትናንት ባወጡት መግለጫ ለጦርነቱ «የመጀመሪያ የመጨረሻውና ብቸኛው አማራጭ ዲፕሎማሲ ነው» ሲሉ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጦር ግንባር እንደሚገኙ፣ሌሎች ታዋቂ አትሌቶች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣የፓርቲና የክልል መንግሥታት መሪዎችም ወደ ጦር ግንባር እንደሚሄዱ ማሳወቃቸውን ከዘገባዎች እንደተረዱ የገለጹት ባለስልጣኑ፣«ሁሉም ወገኖች ሁኔታውን ከሚያባብስ ድርጊት እንዲቆጠቡ፣ ሰብዓዊ መብቶችን እንዲያከብሩ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ እንዲፈቅዱና ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ እንዲያደርጉ ጥሪ እናስተላልፋለንም» ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በኢትዮጵያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አሰቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ትናንት ጠይቋል።የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ አንቶንዮ ጉተሬሽ «የተኩስ አቁሙ ቀውሱን ለመፍታት በኢትዮጵያውን መካከል ውይይት ማድረግ የሚያስችል እና ኢትዮጵያ እንደቀድሞው ለቀጣናው መረጋጋት አስተዋጽኦ የምታደርግ ሀገር እንድትሆን የሚፈቅድ መሆን አለበት» ብለዋል።
የፌስቡክ ተከታታዮቻችን አሜሪካና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ወቅታዊው ሁኔታ ላይ ስላወጧቸው ስለነዚህ መግለጫዎች ምን አስተያየት አላችሁ?ለኢትዮጵያው ቀውስ መፍትሄ የምትሉት ምንድን ነው? ጻፉልን ተወያዩበት