>

" ከፍትህ መጽሄታችን የተቃረሙ ወቅታዊ ቅንጭብጭብ መረጃዎች ...!!!" (ተመስገን ደሳለኝ)

” ከፍትህ መጽሄታችን የተቃረሙ ወቅታዊ ቅንጭብጭብ መረጃዎች …!!!”
ተመስገን ደሳለኝ

* ህውሃት በውጊያ ወቅት ቶሎ ቶሎ የሳተላይት መረጃዎች ይደርሱት ስለነበር ፧ገዥ መሬቶችን እየያዘ ከአለምንም ከልካይ ሽዋሮቢት እንደደረሰ ፣ይህም ሁለት ጠቀሜታ የነበረው ሲሆን 1ኛ,ቦታዎችን ያለመስዋዕትነት መያዙ፣2ኛ,ሰራዊቱ ውስጥ ጥርጣሬ ያነብር እንደነበር ገልፆአል ።
* በጦርነቱ አሻጥሮች እንደነበሩ እና በአንዳንድ ግንባሮች የህወሃት ሰዎች ፣የአማራ ልዩ ሃይል አዛዦችን ፣በአካባቢው ያሉ የመከላከያ ጀኔራሎችን ድምፅ አስመስለው ስልክ በመደወል ፣” የያዛችሁትን ቦታ ለቃችሁ ውጡ” ፧”  ጠላት ሰለቆረጣችሁ በፍጥነት አፈግፍጉ ” ፧”  እኛ ልንወጣ ስለሆነ ፣በዚህ በኩል ለጥቃት ልትጋለጡ ነው” እና የመሳሰሉትን ትዛዞች እያስተላለፉ ፣ቡዙ ቦታዎችን የመቆጣጠር አጋጣሚ ተፈጥረው እንደነበረ ።
ለዚህ የጠቀማቸው ደግሞ ሁለት ነገር ሲሆን ፣1ኛ,የአማራ ልዩ ሃይል ከአለቃው ከጀኔራል ተፈራ ማሞ ጀምሮ ሁሉም አዛዦች ወታደራዊ የመገናኛ ሬዲዮ ስለሌላቸው ፣ውጊያውን በስልክ የሚመሩ በመሆኑ ነው።2ኛ, ህውሃቶች የሚፈልጉትን ሰው ድምፅ የሚያስመስሉበት የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንደነበራቸው ።
* ህውሃት በፌድራል መንግስቱ ከተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳሪዎች ፣በመቶ የሚቆጠሩትን ስለመግደሉ  ።
* በአማራ ልዩ ሃይል ” ጣና ብርጌድ ” አንድ የህውሃት ኮማንዶ ክፍለጦር እና አንድ ፈረንጅ ጦሳ ተራራ ላይ እንደተደመሰሱ ።
* በማይፀብሪ ግንባር አንድ አሜሪካዊ ፣ሁለት ግብፃውያን ( ትግረኛ አቀላጥፈው የሚናገሩ )፧ ሁለት ሱዳናዊያን እና ሁለት ኬንያዊያን እንደ ነበሩ፣አሜሪካዊው የገባው በአለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) አውሮፕላን ረዳት አብራሪነት ሽፋን የገባ ሲሆን፣እዛው ቀርቶ የሽብር ቡድኑን እንደተቀላቀለ።
* WFP ትግራይ ላይ ካሰማራቸው ሰራተኞች ውስጥ ፣ስድስቱ አፍጋኒስታን የነበሩ አሜሪካዊያን ሲሆኑ፣ለህወሃት የተለገሱትን ወታደራዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ኦፕሬት ለማድረግ የመጡ ስለመሆኑ ፣
* በክተት ጥሪ መከላከያን እየተቀላቀሉ ያሉ ወጣቶች የጀርባ ታሪክን መፈተሽ እንደሚገባ፣
* በጎረቤት ሀገራት ያሉ የሽብር ቡድኑ እንቅስቃሴዎች በንቀት የሚታለፍ አለመሆኑ ፣
* እንደ ሱዳን ሁሉ ኡጋንዳ እና ሩዋንዳንም ለወታደር ማሰልጠኛነት የመጠቀም አዝማሚያዎች እንዳሉ አጋርቶናል ።
Filed in: Amharic