>

"ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ የሚሄደው ባቡር ተጠምዞ ወደመቀሌ እየሄደ ነው...!!!" ግብፃዊ የፖለቲካ ተንታኝ አልሸርቅ ሚዲያ ላይ ከተናገረው 

“ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ የሚሄደው ባቡር ተጠምዞ ወደመቀሌ እየሄደ ነው…!!!”
ግብፃዊ የፖለቲካ ተንታኝ አልሸርቅ ሚዲያ ላይ ከተናገረው 
(ትርጉም ሱሌማን አብደላ)

ግብፃዊ የፖለቲካ ተንታኝ አልሸርቅ ሚዲያ ላይ ከተናገረው የተወሰደ አሜሪካ አውሮፓ ሁሉም ከኛ ጋር ቆመው ነበር። የህወሓት ተዋጊዎች አስገራሚ በሚመስል መልኩ ወደ አዲስ አበባ እየገሰገሱ ነበር።
 በዚህ ሁለት ወይም ሦስት ቀናቶች ውስጥ አዲስ አበባ ገቡ፣ ይሄንን ሰውየ ተገላገልን ብየ ለመናገር ትንሽ ሰአት ቀረኝ ስል፣ ሰውየው ጭራሹንም ጦሩን እራሴ እመራለሁ ብሎ መግለጫ ሰጠ። ወርዶ ሲያዋጋ ቆየ። ህወሓት ይቆጣጠረዋል የተባለውን የጅቡቲ መንገድ ነፃ አወጣ። አፋር ክልል ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆነ። ኮምቦልቻ ባቲና ጋሸ  ጭፍራ የሚባሉ ወሳኝ ወታደራዊ ቦታዎችን ያዘ። አሁን ነገሮች ተቀያይረዋል። ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ የሚሄደው ባቡር ተጠምዞ ወደመቀሌ እየሄደ ነው። በየትኛውም ቀን ወይም ሳምንት ውስጥ መከላከያ መቀሌ ይገባል። የህወሓት ተዋጊዎች አቅም አንሷቸዋል። የሎጀስቲክ የሰው ሀይል የውጊ መጨለም ገጥሟቸዋል። በዚህ ደረጃ ላይ ቆመው ወደኋላ እየሸሹ ነው።
.አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት የኛ ሀይል በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የፈጠረው ተፅዕኖ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እልህና ቁጭትን ዘርቷል። ሚሊየኖች ወደ ጦር ግንባር እየሄዱ ነው። ጦረነቱ ከአብይ አሕመድ ስረአት ተላቆ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚደረግ ጦርነት ሆኗል። አፍሪካዊ የፀረ አፓርታይድ ትግል ነው ተብሎ በአፍሪካውያን እየተቀነቀነ ነው። አብይ ስልጣኑን አልፈልግም ሀገሬ ትቀድማች ሞቼ ወይም ተዋግቸ ኢትዮጵያን አስቀጥላለሁ ብሎ ወደ ጫካ ሲገባ ነው ነገሮች የተቀያየሩት። ህዝቡ እንዳለ ግንፍል ብሎ ወጣ ። ሁሉም ነገር ተቀይሯል።
ከዚህ ቡሀላ የግብፅ ጉዳይ ከአብይ አሕመድ እጅ እንዳሎጣ እመኑት። ካይሮ ላይ ወላሂ ወላሂ ብሎ እንደከዳን አሁን ፈጣሪ ክዶት ይገረሰሳል ብለን ስንጠብቅ ጦርሜዳ ተዋጊ ሆኖ ማሸነፍ ጀምሯል። ከዚህ ቡኋላ የሚደረጉ ውጊያዎች ከአብይ ጋር  ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ጋር የሚደረግ ውጊ ሆኗል። እሱ ሲነሳ ህዝቡ እንደ ህዝብ ”ሆ” በሎ ነው የወጣው። ህዝብን ከጎኑ አሰለፈ ማለት ነገሮች ተቀያየሩ ማለት ነው። አብይ አሕመድን ማሸነፍ በፍጹም አይቻልም። ይሄንን ሁሉም አለም አምኖ ሊቀበለው ይገባል ።
Filed in: Amharic