ግርማ ካሳ
የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ነበር።፡ ግንቦት ሰባት ነህ ተብሎ በወያኔ ለረጅም ጊዜ በወህኒ ማቋል።
ያኔ የእርሱን የስልክ ንግግር ኢንሳዎች ጠልፈው በመጥለፍ ከነ ፋሲል የኔዓለም ጋር ተነጋግረሃል ብለው ነበር ያሰሩት።
አዎን፦ ኢንሳዎች …ማለትም የኢንሳ አመራሮች ደግሞ እነ ማን እንደነበሩ ያው ታውቃላችሁ ብዬ እገምታለሁ- የዛሬው ጠምር እነ ዶ/ር አቢይ አቶ ተመሰገን ነበሩ
በ2018 መስከረም ላይ እነ ዶር ብርሃኑ ነጋና ግንቦት ሰባቶች ሲመጡ፣ የግንቦት ሰባት መሪዎችን ለመቀበል የተዘጋጀ ኮሚቴ ነበር። ይህ ሰው የዚያ ኮሚቴ ሰብሳቢም ሆኖ አገልግሎ ነበር።
ብዙም ሳይቆይ የቡራዩ ሰቆቃ ሲፈጸም በአዲስ አበባ ተቃውሞ ተነሳ። ” አንተ ነህ ያደራጀኸው” ተብሎ ከ1300 የአዲስ አበበ ወጣቶች ጋር በኦህዴድ መንግስት ታስሮ ተሰቃይቶ ነበር።
በኋላ ላይ በአባይ ሜዲያ ላይ በታወቀው የአውድማ ፕሮግራም ዝግጅ ላይ አንዳንዴ ሞደሬት ሆኖ በመቅረብ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተንታኝ ሆኖ በገኘት በጋዜጠኝነቱ ሲሰራ ነበር።
ጋዜጠኛ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ይባላል።
በግሌ ከማደንቃቸውና ከማከብራቸው ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዱ ነው።፡
ግን ያው ጦርነቱን እንደ ሰበብ በመጠቀም የማይፈልጓቸውን ሀገርና ወገን ወዳዶችን እውነትን ተከታዮችን የማስፈራራት፣ የማሰር እኩይ ተግባራትን በኦህዴድ ብልጽግናዎች መወሰድ ስለተጀመረ፣ በዚህ አጋጣሚ ወንድም ብርሃኑ ተክለያሬድን አስረውታል።
የታሰረበት ወንጀል አገሩን መውደዱ፣ እውነትን መናገሩ፣ የእነርሱ አጨብጫቢ ተደማሪና ተለጣፊ ያለመሆኑ ብቻ ነው !!!!!