አቻምየለህ ታምሩ
የደብረ ብርሀን ፖሊስ አዛዥና የከተማው ከንቲባ የፋሽስት ወያኔ አስተኳሾች ሆነው ስለተገኙ መታሰራቸው ተሰምቷል። ከዚህ በፊት በተደጋገሚ እንደተናገርነው ፋሽስት ወያኔ ከኮረም እስከ ሸዋሮቢት ድረስ የደረሰው በጦር ሜዳ አማራን ድል አድርጎ ሳይሆን አማራን ለመታገል በተፈጠረው ብአዴን በሚባለው ነውረኛ ድርጅት መዋቅር እየተመራ መሆኑን ተናግረን ነበር።
አማራን ለመታገል የተፈጠረው ብአዴን አማራ ራሱን ከሚያጠፋው ጠላት እንዳይከላከል አድርጎ የፍጥኝ አስሮ ስለያዘው የብአዴን ፈጣሪው ፋሽስት ወያኔ ፍጡሩ በከፈተለት መንገድ እየተጓዘ ከኮረም እስከ ሸዋሮቢት በሶምሶማ ሩጫ ሊደርስ ችሏል። ከዚህም በመነሳት የኅልውና ዘመቻው ብአዴን የሚባለው ጉድ በማይደርስበት አኳኋን እስካልተመራ ድረስ ከፋሽስት ወያኔ ጋር የሚደረገው የኅልውና ተጋድሎ ከባድ መስዕዋትነት እንደሚያስከፍለን በተደጋጋሚ አሳስበን ነበር።
እስካሁን ድረስ አማራን የከዳ ብአዴን እንጂ አማራን የከዳ ፋኖ፣ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አልታየም። ብአዴን የሚባለው ዘግናኝ ፍጥረት ፋኖ፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ የሚገባውን ትጥቅና ስንቅ አግኝቶ በራሱ እቅድ እንዳይመራ እያደረገ ያለው ብአዴን ፋሽስት ወያኔ እንጂ አማራ እንዲያሸንፍ ስለማይፈልግ ነው። ብአዴን የተፈጠረው አማራን ሊታገል መሆኑን መናገር ለቀባሪው ማርዳት ነው።
አማራን ለመታገል የተፈጠረው ብአዴን ለአማራ እንዲታገል መጠበቅ ከእባብ እንቁላል የእርግብ ጫጩት እንደመጠበቅ አይነት ጅልነት ነው። የብአዴን መዋቅር ፋሽስት ወያኔ የዘረጋው መዋቅር ነው። መዋቅር ሲባል በየቦታው የተቀመጡ ሰዎች ማለት ነው። በሌላ አነጋገር በብአዴን መዋቅር ከቀበሌ እስከ ክልል ተብዮው ድረስ በየቦታው የተቀመጡ ርጉሞች የፋሽስት ወያኔ ታማኝ የውስጥ የመረጃ ምንጮች እና አስተኳሾች ናቸው። ፋሽስት ወያኔ ከኮረም እስከ ሸዋሮቢት የደረሰው በነዚህ የብአዴን ፍጡራን መንገድ መሪነት፣ መረጃ አቀባይነትና አስተኳሽነት ነው።
ከሳምንት በፊት የከለላ ወረዳ አመራሮች በሙሉ ፋሽስት ወያኔን ለመቀበል ሽርጉድ ሲሉ በአማራ ልጆች ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። ይኼው አሁን ደግሞ የደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳድር ፖሊስ ኃላፊና ከንቲባ የፋሽስት ወያኔ አስተኳሾች በመሆናቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ። የፖሊስ ኃላፊውና ከንቲባው የፋሽስት ወያኔ አስተኳሾች ከሆኑ እነዚህ ሰዎች በዘረጉት መዋቅር ስር የተቀመጡ ሰዎች ለማን እንደሚሰሩ መገመት አይከብድም። በጎጃም፣ በጎንደርና በወሎም እንደዚያው ነው። ምስራቅ ጎጃም ውስጥ ብአዴን በጎለታቸው ሰዎች ቤት ውስጥ እየተገኘ ያለውን ጉድ ደፋር ልጆች እየተናገሩት ስለሆነ አንብባችሁት ይሆናል። ከቀበሌ እስከ ዞን ድረስ ያለው የብአዴን የምስራቅ ጎጃም መዋቅር ፋሽስት ወያኔ አባይን ባለመሻገሩ የሚቆጩ ጉዶች የሞሉበት ነው።
ባጭሩ አማራ በሁለት ግንባር እየታገለ ያለው በአንድ እጁ ነው። ከፊት ለፊት ፋሽስት ወያኔን በአንድ እጁ ሲዋጋ ከኋላው ደግሞ አንድ እጁን የወደኋሊት አስሮ ከሚወጋው ብአዴን ከሚባል ዘግናኝ ፍጥረት ጋር እየተዋጋ ነው። ፋሽስት ወያኔ ከኮረም እስከ ሸዋ ሮቢት ድረስ የደረሰው አማራው ከፊት ለፊት በፋሽስት ወያኔ ከኋላ ደግሞ ብአዴን በሚባለው የሕወሓት ድርጅት እየተወጋ ነው። ብአዴን ባለበት ሁሉ የፋሽስት ወያኔ መዋቅር፣ የፋሽስት ወያኔ ዓላማ፣ የፋሽስት ወያኔ ስር አለ። ብአዴን እንደ ድርጅት የተፈጠረው አማራን ለመታገል ነው። እስካሁን ድረስ በተካሄደው ተጋድሎ አማራን የከዳ፣ ለፋሽስት ወያኔ የሚያስተኩስና መረጃ የሚሰጠ ብአዴን እንጂ አማራን የከዳ ፋኖ፣ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና መከላከያ ሠራዊት አልታየም።
በመሆኑም የፋሽስት ወያኔ አስተኳሽ የሆኑት ብአዴኖች ከጥቅም ውጭ ሆነው ጸረ ፋሽስት ወያኔ ተጋድሎው በሕዝብ ልጆች ፊታውራሪነት እስካልተካሄደ ድረስ በሕወሓቱ ነውረኛ ድርጅት በብአዴን አዝማችነት የሚካሄደው ጸረ ፋሽስት ወያኔ ተጋድሎ ከጠላት ጋር ተሰልፎ ጠላትን አሸንፋለሁ ብሎ እንደማሰብ አይነት ቂልነት መሆኑ መታወቅ አለበት።
ስለዚህ የኅልውና ዘመቻው ውጤት ከእስከንደዛሬው የተለየ እንዲሆን ከተፈለገ የብአዴን የሆነው ነገር ሁሉ ታግዶ ጸረ ፋሽስት ወያኔ የኅልውና ተጋድሎው ብአዴን በማይረርስበት ሁኔታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ በመከላከያው፣ በልዩ ኃይሉ፣ በሚሊሻውና በፋኖው የተቀናጀና የተናበበ ስምሪት መካሄድ ይኖርበታል።
ለፋሽስት ወያኔ ሲያስተኩሱ የተገኙት የብአዴን አመራሮች በሙሉ ያለ ምሕረት እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል። እነዚህን ባንዳዎች ለመከላከል የሚሞክር ብአዴን ቢኖር እንደነሱ ያለ ባንዳ ስለሆነ ዋጋውን ማግኘት አለበት። ለባንዳ፣ ለከሀዲ፣ ለፋሽስት ወያኔ አስተኳሽና መረጃ አቀባይ ምህረት ሊኖር አይገባም።