ሸንቁጥ አየለ
“- ከበሽታዉ ነጻ መሆንክን መመርመሪያ መስፈርቶች…!!!”
ላለፉት ሰላሳ አመታት አብዛኛዉ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በአራት አይነት የብሄርተኝነት በሽታዎች ተመትተዋል::እነዚህ አራት አይነት በሽታዎች ከኢትዮጵያ ሳይወገዱ እና ፖለቲከኞቹ ሳይፈወሱ ኢትዮጵያ ከቶም ፈዉስም እረፍትም ጤናም ሰላምም አይኖራትም::በነዚህ አራት አይነት የብሄረተኝነት በሽታዎች የተነሳ ኢትዮጵያዉያንም በእኩልነት እና በወንድማማችነት አብረዉ መኖር አይችሉም::
1.የአሳማ ብሄረተኝነት:-
የብአዴናዉያንንነና የብአዴን መርህ ተከታዮችን ያጠቃ የበሽታ አይነት ነዉ::ለእነዚህ ፖለቲከኞች ሰዉነት ከእነሱ ሆድ በታች ነዉ::በዚህ በሽታ የተጠቁ ፖለቲከኞች እናቶቻቸዉም:ልጆቻቸዉም:ቤተሰባቸዉም እየታረዱ በሚታረድ ወገናቸዉ ፊት ቆመዉ ሆዳቸዉ እስካልጎደለ ድረስ ሁሉም ነገር ሰላም ነዉ ብለዉ የሚለፈልፉ በሽተኞች ናቸዉ::
2.የእሥስት ብሄረትኝነት:-
ከግንቦት ሰባት እስከ ኢዜማ ያሉ እና በኢትዮጵያ ብሄረተኝነት ስም የሚያጭበረብሩ አስመሳይ ፖለቲከኞችን ያጠቃ በሽታ ነዉ::እነዚህ ፖለቲከኞች ፍጽም የኢትዮጵያዊነት ፖለቲካ ከሚያራምደዉ ቅንጅት ጀምሮ ኢትዮጵያን ለማጥፋት እስከሚሰራዉ ኦነግ ድረስ ወዳጅነት እና ግንባር ለመፍጠር የሚችሉ ባህሪያቸዉን እንደ እሥስት ያለ መርህ የሚለዋዉጡ ናቸዉ::ልክ እንደ እሥስት ባህሪም ሁሉንም ባህሪ ለመተውን ታላቅ የማጭበርበር እና የማስመሰል ክህሎትን የተካኑ ናቸዉ::
ለነዚህ ፖለቲከኞች መርህ ወይም እዉነት ቦታ የለዉም::እንደ እሥስቷ እንደ ሁኔታዉ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከሚያራምዱ ሀይሎችም ጋር ወይም ኢትዮጵያዊነትን ሊታደጉ ከሚችሉ ሀይሎች ጋር መተባበር ይችላሉ::በሽታዉ ያጠቃዉ ፖለቲከኛ በበርካታ ሁኔታዎች ዉስጥ እንደ ሁኔታዉ ሆኖ መተወን ይችላል::
3.የካንሰር ብሄረተኝነት :-
ይሄ በሽታ የህዉሃት አባላት እና አመራሮች ያጠቃ ነዉ::በሽታዉ ዋና መለያዉ የካንሰር ባህሪ አለዉ::አንዴ ይሄ በሽታ ከተጠናወተ አይድንም::ተቆርጦ እስኪጣል ድረስም የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ዋና የህልዉና እና እንደ ሃገር የመቀጠል ነቀርሳ ነዉ::ይሄ በሽታ ተጨማሪም መለያዎች አሉት::እንደ ተስቦ በሽታም ተላላፊ ነዉ::ከዚህ የብሄረተኝነት በሽታ በርካታ አይነት የብሄረተኝነት በሽታዎችም መቀፍቀፍ ችለዋል::
4.የአጋንንት ብሄረትኝነት:-
ይሄ በሽታ ኦነጋዉያንን/ሸኔን እንዲሁም ኦህዴዳዉያንን ያጠቃ በሽታ ነዉ::በዚህ በሽታ የተመታ ፖለቲከኛ የአዳም ዘር አንድ የአዳም ልጅ ነዉ ብሎ አያምንም::ይሄ በሽታ የሌሎች ነገዶችን ደም በማፍሰስ እና ሌሎች ነገዶችን ከምድረ ገጽ በማጥፋት ከፍተኛ እርካታ የሚያገኝ ነዉ::በዚህ በሽታ የተጠቁ ፖለቲከኞች የህዝብ ደም ሲፈስ በታላቅ እርካታ የሚያስጓራ በሽታ የያዛቸዉ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ነገዶችን ማጥፋት የግባቸዉ ቁልፍ አካል አድርገዉ የያዙ ናቸዉ::ይሄ በሽታ ኢትዮጵያዉያን ነገዶች እንደ ሰዉ አብረዉ መኖራቸዉን የማይቀበል እና የኢትዮጵያዉያንን የእርስ በርስ ፍጅት ያወጀ በሽታ ነዉ::
==================
የአራቱም የብሄርተኝነት በሽታዎች የጋራ ባህሪ
——
1.እዉነትን በሀሰት መለወጥ እና የሀሰት ፕሮፖጋንዳን እንደ ፖለቲካ መሳሪያ መጠቀም
=============
የካንሰር የብሄርተኝነት በሽታዎች እና የአጋንንት የብሄርተኝነት በሽታዎች የጋራ ባህሪ
———-
1.ታሪክን በሀሰት እንደገና አጣሞ በመጻፍ ኢትዮጵያዉያን መሀከል ቅራኔን ለመዝራት በርካታ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳዎችን መንዛት
♦♦♦
ከአራቱም የብሄረተኝነት በሽታዎች ነጻ የሆንክ እዉነተኛ ሰዉና እዉነተኛ ኢትዮጵያዊ መሆንህን ለማረጋገጥ መመርመሪያ መስፈርቶች
———————
1.ምንም እንኳን ሰዎች በነገድ:በቋንቋ : በሀይማኖት ወይም በባህል ቢለያዩም የአዳም ልጆች አንድ ናቸዉ::ተዋልደዉ ተጋብተዉ እና ተፈቃቅረዉ በምድር ላይ አብረዉ ሊኖሩ ይችላሉ ብለህ ካመንክ
2.የኢትዮጵያ ህዝብ ጥንታዊ ህዝብ ነዉ::ሀገሪቱም ጥንታዊ ሀገር ነች ብለህ ካመንክ
3.የኢትዮጵያ ህዝብ የነገድ ልዩነትም ቢኖረዉ አንድ ህዝብ ነዉ ብለህ ካመንክ
4.የኢትዮጵያዉያን የወደፊት ተስፋ በጋር የተሳሰረ ስለሆነ ኢትዮጵያዉያን ደም እንዳይቃቡ የምትሰራ ከሆነ እና የሁሉም ኢትዮጵያዉያን ነገዶች ህልዉና እና ደህንነት የሚያሳስብህ ከሆነ
5.ከላይ የተጠቀሱትን አራቱንም አይነት የብሄረተኝነት በሽታዎች የምትጸዬፍ እና የምትጠላ ከሆነ
6.በኢትዮጵያ ዉስጥ የነገዶች እና የሀይማኖቶች እኩልነት መኖር አለበት ብለህ የምታምን ከሆነ
7.ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ሀገር ናት ብለህ የምታምን ከሆነ
8.የጎሳ/የብሄር ፖለቲካ በህግ መታገድ አለበት ብለህ የምታምን ከሆነ
9.አሁን ያሉት የጎሳ/የብሄር ክልሎች በህግ መታገድ አለባቸዉ ብለህ የምታምን ከሆነ
10. ኢትዮጵያ ዉስጥ ፖለቲካ በሀሳብ መር የሀሳብ ልዕልና ወይም የሀሳብ አምዶች ላይ (ለምሳሌ ሶሻሊስት:ሊበራል ዲሞክራት:ሪፐሊካን: ካፒታሊስት:ዲሞክራት: ዲኦንሄራዊ ዲሞክራሲ ወይም ሌላ አይነት የሀሳብ ልዕልና መር የፖለቲካ ፍልስፍና) ብቻ ተመርኩዞ የፖለቲካ ፓርቲ መቋቋም አለበት ብለህ የምታምን ከሆነ
11. አንተ በምትኖርበት በዚህ ዘመን ማናቸዉም ኢትዮጵያዉያን በነገዳቸዉ ወይም በሀይማኖታቸዉ የተነሳ ጭፍጨፋ ሲደርስባቸዉ:ሲፈናቀሉ:ሲገፉ ድምጽ ከሆንካቸዉ ደጋግመህም ከጮህላቸዉ
12.በነገዳቸዉ ወይም በሀይይማኖታቸዉ የተነሳ ላለፉት 30 አመታት የዘር ማጥፋት የተደረገባቸዉ/የተፈናቀሉ/የተገፉ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዉያን በመንግስት ደረጃ ይቅርታ ተጠይቀዉ:ካሳ ተከፍለዉ እንደገና መቋቋም እንዳለባቸዉ የምታምን ከሆነ
13.ኢትዮጵያ በህግ የበላይነት:በዲሞክራሲ እና በሰብአዊ መርሆዎች ብቻ መመራት ያለባት ሀገር ልትሆን ይገባታል ብለህ ካመንክ
14.ከላይ ከ1-13 ለተዘረዘሩት አስተሳሰቦች/መርሆዎች እዉን መሆን የምትታገል ከሆነ