–አወል አርባ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር
(ኢ ፕ ድ)
የትግራይ ወራሪ ቡድን ሚሌንና ጭፍራን ለመያዝ ያለ የሌለ ኃይሉን የተጠቀመው ሁለቱም ቦታዎች ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸው በመሆናቸው ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ገለጹ::
ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አወል ለብዙሃን መገናኛ በሰጡት ማብራሪያ እንዳሉት፤ የትግራይ ወራሪ ኃይል ጭፍራና ሚሌን መያዝ አራት ኪሎን እንደተቆጣጠርኩት ያህል ነው ብሏል::ይህን ያለውም እነዚህ ቦታዎች ከፍተኛ ስትራቴጂክ ቦታዎች በመሆናቸው ነው::
እንደእርሳቸው ማብራሪያ፤ ጭፍራ ወረባቦ ወረዳን በባቲ በማቋረጥ ኃይቅንና ደሴን ያገናኛል፣ የክልሉን አምስቱንም ዞኖች የሚያገናኝ ማከፋፈያ ስፍራ መሆኑን አመልክተው፤ የትግራይ ወራሪ ቡድኑ ጭፍራንና ሚሌን የሚፈልግበት ምክንያት በሁሉም አቅጣጫና በፈለገው አማራጭ እስከ አዲስ አበባ ያለውን መስመር የሚያገናኙ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ስለሆኑ ነው ሲሉ ገልጸዋል::
አሸባሪ ቡድኑ ሚሌን ለመያዝ በጭፍራና በቡርቃ ግንባሮች ባደረገው ሙከራ ከፍተኛ ኪሳራ አጋጥሞት ወደ ኋላ ማፈግፈጉን በማስታወስም፤ ሚሌን የመያዝ የአሸባሪ ቡድኑና ግብረ አበሮቹ እቅድና ቅዥት..
የዚህን ዜና ሙሉ መረጃ ለማንበብ ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው ወደ ድረገጹ ይግቡ