>

በወለጋ የተለያዩ አካባቢዎች አማራ ዓመቱን ሁሉ ሲደክምበት የከረመውን ሰብል እንዳይሰበስብ ተከልክለዋል...!!! (አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ)

በወለጋ የተለያዩ አካባቢዎች አማራ ዓመቱን ሁሉ ሲደክምበት የከረመውን ሰብል እንዳይሰበስብ ተከልክለዋል…!!!
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ

*…. ሁለት አማራዎች በማሳቸው ላይ በግፍ ተገድለዋል!
 
*…. በክልሉ መንግስት እና በኦነግ ሸኔ መካከል ያለውን ልዩነት ለማስቀመጥ የተቸገሩት ነዋሪዎቹ አሸባሪ ያሉት ኦነግ ሸኔ አዝመራችን ሸንሽኖ ሲያከፋፍል፤ መኪና ይዘው በጉልበት ሲዘርፉን፣ በማሳችን ላይ ጦርነት ከፍቶ ሲገድለን ምንም እንዳልተፈጠረ እያዬ እንዳላዬ በዝምታ የሚያልፈው መንግስትም ከቡድኑ የተለዬ አይደለም ብለዋል!
በሆሮ ጉድሩ ዞን አሙሩ ወረዳ ሲደን በርከሊ ቀበሌ ህዳር 18 ቀን 2014 ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ሁለት የአማራ ገበሬዎች የአማራው አዝመራ ተከፋፍሎ በተሰጣቸው በጽንፈኛ እና ተስፋፊ ኦነጋዊያን አማካኝነት በማሳቸው ላይ እያሉ በጥይት ተገድለዋል።
በተጨማሪም በምስራቅ ወለጋ ዞን ጎቡሰዮ ወረዳ አኖ አካባቢ ሁለት አማራዎች ታግተዋል፤ ሌላ አንድ አማራ ደግሞ በጽንፈኛ ኦነጋዊያን ተገድሏል።
በዝርፊያውም በትጥቅ ተደግፈው ብዙዎች እየተሳተፉ ነው፤ ቁጭ ብለው ከርመው ባለቤት አልባ የተደረገውን የአማራ አርሶ አደር ምርት እየዘረፉ ነው ተብሏል።
ሲደን በርከሊ በማሳቸው ላይ የተገደሉ አማራዎችም:_
1) ሰይድ ይመር እና
2) ሙስጠፋ መሀመድ ይባላሉ።
ህዳር 19 ቀን 2014 የአማራውን ቤት ሲያቃጥሉ ውለዋል ተብሏል።
“እኔ መብት የለኝም፤ አልችልም” በሚል ኃላፊነቱን ለመወጣት ያልፈለገው የአሙሩ ወረዳ መስተዳድርም በሲደን በርከሊ በሀምሌ 2013 ዓ/ም 37 የሚሆኑ የኦሮሞ ሚሊሻዎች ትጥቃቸውን በአካባቢው ኦነግ ሸኔ ላደራጃቸው ቄሮዎች ሲያስረክቡም ምንም ማድረግ ያልቻለ ሰው ነው ሲሉ ወቅሰውታል።
በክልሉ መንግስት እና በኦነግ ሸኔ መካከል ያለውን ልዩነት ለማስቀመጥ የተቸገሩት ነዋሪዎቹ አሸባሪ ያሉት ኦነግ ሸኔ አዝመራችን ሸንሽኖ ሲያከፋፍል፤ መኪና ይዘው በጉልበት ሲዘርፉን፣ በማሳችን ላይ ጦርነት ከፍቶ ሲገድለን ምንም እንዳልተፈጠረ እያዬ እንዳላዬ በዝምታ የሚያልፈው መንግስትም ከቡድኑ የተለዬ አይደለም ብለዋል።
በበርካታ የመንግስት አካላት ጭምር እየተደገፈ ዘር እያጠፋ ያለው የሽብር ቡድን ከህዳር 8 እና 9 ቀን 2014 ብቻ ከምዕራብ ወለጋ ባቦ ገምቤል ወረዳ የ3 ቀበሌ ነዋሪ ከ60 ሽህ በላይ አማራዎችን አፈናቅሎ ያደራጃቸውን አካላት በማስገባት እንዲዘረፍ አድርጓል።
በተጨማሪም ከተፈናቃዮች መካከል ሁለት መኪና ሙሉ ማለትም ከ95 በላይ ወደ አሶሳ የሚሄድ አማራ አግቶ በመውሰድ አድራሻ ጨፍጭፏል፤ አድራሻቸውንም አጥፍቷል።
በአሙሩ፣ በኪረሞ፣በጊዳ (በአንዶዴ ዲቾ እና በዶሮበራ)፣በስቡስሬ፣በሌቃ ዱለቻ፣ በጉቴ፣ በሊሙ፣በጎቡሰዮ፣ በቦኒያ ቦሼ እና በሌሎችም ወረዳዎች በሚገኙ በርካታ ቀበሌዎች ምርቱን እንዳይሰበስብ የተደራጁ እና የታጠቁ የዘር ማጥፋት ተባባሪዎቹን አሰማርቶ ያለማንም ሀይ ባይ በአማራ ገበሬ ላይ ዝርፊያ በማስፈጸምና በመፈጸም የግፍ ግፍ እየሰራ ነው።
Filed in: Amharic