>

ይድረስ ለፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እና ለዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ (ከጌታቸው ታፈረ)

ይድረስ ለፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እና ለዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ

ከጌታቸው ታፈረ


ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እና ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ህዳር 17/2014 ዓ.ም. ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ መጣችሁ መምህራንን በማናገራችሁ ደስ ብሎናል፡፡ በበፊት አጠራሩ ኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በርካታ ምሁራንን ያፈራ አንጋፋ ተቋም ነበር፡፡ እስካሁን ተቋሙ ባለቤት አጥቶ ቢቆይም አሁን የትምህርት ዩኒቨርስቲ መባሉ ተቋሙን ወደ ቀደመው ክብሩ ሊመለስ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህንንም ዓላማ ለማሳካት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እና ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አቅሙም፣ትጋቱም እንዳላችሁ እናውቃለን፡፡ በርቱ ከጎናችሁ ነን፡፡ ፈጣሪ ይርዳችሁ፡፡

ይህን ዓላማ ለማሳካት ግን የዩኒቨርስቲው አመራር መቀየር አለበት፡፡ ዶ/ር ብርሀነ መስቀል ጠናን የሚመስል ካድሬ ይዛችሁ ተቋሙን የትም ልታደርሱት አትችሉም፡፡  ዶ/ር ብርሀነ መስቀል ጠና የአቅም ውስንነት ያለበት ደካማ ሰው ነው፡፡ ኮተቤን የሚያህል ተቋም በእርሱ መመራቱ የሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት ለመውደቁ ትክክለኛ ማሳያ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰውየው ዘረኛ ነው፡፡ የዩኒቨርስቲውን መተዳደሪያ ደንብ ሳይከተል በትውውቅ እና በዘር በመሳሳብ በርካታ ደጋፊዎችን ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በውድድር ሳይሆን በዝውውር በማስመጣት ተቋሙን የዘመዶቹ መሰብሰቢያ አድርጎታል፡፡ ሰውየው ስልጣኑን ተጠቅሞ በተለያዩ የምርምር ስራዎች ላይ እየገባ እና የሚፈልጋቸውን ሰዎች ያለውድድር እንዲገቡ እያደረገ በሙስናም መጨማለቅ ጀምሯል፡፡ ያው ስብሰባው ላይ እንደሰማችሁት በስሩ የሚሰበስባቸው ሰዎች ለእርሱ የሚያጎበድዱትን እና የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑትን ብቻ ነው፡፡ ይህን ደካማ፣ዘረኛ እና ሙሰኛ ካድሬ ይዛችሁ ተቋሙን አይደለም የትምህርት ክፍልም አትለውጡም፡፡ በዶ/ር ብርሀነ መስቀል ጠና ላይ በርካታ መረጃዎችን ሰብስበን ልንሰጣችሁ እንችላለን፡፡

ቸር እንሰንብት!!

Filed in: Amharic